አባ ዱላ ገመዳ፡ “ሠራዊቱ ሃገርንና ሕገ መንግሥትን ለማስጠበቅ ተጨባጭ ዕቅዶችን ነድፏል!”             – አፈ ጉባዔው በዚህ የሕዝቡ የለውጥ ስሜት ይገታል ብለው ከሆነ ካሰብነው በላይ ተሳስተዋል!

4 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሰራዊቱን የአገር ሉአላዊነትና ህገ መንግስታዊ ስርአት የማስጠበቅ አቅም ለመገንባት የተያዘው እቅድ ለልማትና ዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መፋጠን የሚኖረው ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ አባዱላ ገመዳ ገለፁ፡፡

Foto Fana

Speaker Aba Dula Gemeda (Foto Fana)

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመከላከያና የደህንነት ጉዳዮች ልዩ ኮሚቴ የሀገር የመከላከያ ሚኒስቴርን የ2ዐዐ8 በጀት አመት እቅድ ገምግሟል፡፡

የ2008 በጀት እቅድ ህገ መንግስታዊ መርሆዎች ላይ በማትኮር ቁልፍና አበይት ተግባራትን ለይቶ ያስቀመጠ ነው ያሉት ሚንስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፣ መመሪያዎችና አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመልካም አስተዳደር ችግር በር የሚከፍቱ በመሆኑ ችግሩን ለመፍታት በቁልፍ ተግባራት ተለይቷል ብለዋል።

በሚኒስቴሩ የተለያዩ የአመራር እርከኖች ያለውን የማስፈፀም አቅም ችግር ለመፍታትም የነባሮቹን አመራሮች አቅም ከማሳደግ ጎን ለጎን አዲስና ተተኪ አመራሮችን ለማፍራት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ለዚህም ተብሎ የተገነባውን ማሰልጠኛ ማዕከል ወደ ኮሌጅ የማሳደግ እቅድ ተይዟል ብለዋል።

የልዩ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ በበኩላቸው፥ ሰራዊቱ የሀገሩን ሉዓላዊነትና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመጣበቅ በሚያስችል ቁመና ላይ እንዲገኝ በእቅድ ተይዞ የሚከናወኑ ተግባራትን አድንቀዋል።

አቶ አባዱላ አክለውም በሚኒስቴሩ የሚታየውን የሙስናና ብልሹ አሰራር ምንጩን ለይቶ በመፈትታት የመልካም አስተዳደር ችግር መነሻ እንዳይሆን ትኩረት እንዲሰጠው አሳስበዋል።

    Speaker of the Ethiopian Parliament on January 2, 2016 said that the Ethiopian army is equipped with functional plans and strategies to ably defend the nation and the constitution.

The Speaker made this remark following the defense and security committee’s review of the 2015/16 budget of the ministry of defense.

At the same time, Speaker Aba Dula did not refrain from reminding Defense Minister Siraj Fergesa that there was an imperative need to properly identify the source of the widespread corruption in his ministry, about which  Auditor-General Gemechu Dubiso has been outspoken in recent years.

%d bloggers like this: