የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ያለውን ዘር ላይ የተመሠረተ ግድያና አፈና እንደገና ተቃወመ፤ የታሠሩት እንዲፈቱና ውይይት እንዲካሄድ ጠየቀ – ሰሞኑን ይህንን ዐይነቱን እርምጃ ማዕደ ኢሣት ክፉኛ ያጣጣለው ቢሆንም!

15 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የአሜሪካ መንግሥት ጥር 14/2016 ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ ውስጥ በሕወሃት መሪነት የሚፈጸመውን የኦሮሞ ሕዝብን ጭፍጨፋ እንደሚቃወም እንደገና አሰማ። በዚሁ መግለጫ በሃገሪቱ ሕገ መንግሥት መሠረት ኢትዮጵያውያን በሰላማዊ መንገድ የመቃወም መብታቸው መረጋገጡን አስታውሶ፡ መብቶቻቸውን ተግባራዊ ያደረጉ ሰላማዊ ዜጎች በግፍ መገደላቸው ክፉኛ እንደሚያሳስበው በዚሁ መግለጫ ውስጥ አሥምሮበታል።

የሕውሃት አሰተዳደር በታህሳስ ወር ሕዝቡን በሚገባ በማወያየት ችግሩን ለመፍታት እርምጃ ይወስዳል ተብሎ ቢጠበቅም፡ እስካሁን ይህ ባለመሆኑ ኦሮሚያ ውስጥ ችግሩ መቀጠሉን አመልክቷል። ሕዝቡም እምነቱንና አስተሳሰቡን በነጻነት ለመግለጽ የሚያስችለው ሁኔታ ይፈጠራል ብሎ የአሜሪካ መንግሥት ተስፋ አድርጎ እንደነበር መግለጫው አስታውሷል።

በዚሁ መግለጫ አሜሪካ የሕወሃት አስተዳደር ሕዝቡን ከማፈን እንዲቆጠብና በሕግ መንግሥቱ የተፈቀዱትን ሕዝብ በነጻነት መብቱን ለማስከበር በሰላማዊ መንገድ መሰብሰቡንና ድምጹን ማሰማቱ እንዲከበርለት ጠይቋል። ኢትዮጵያ የአንድ ወገን ሳይሆን የብዙኃን ድምጽ በነጻነት ሊሰማባት የሚገባት ሃገር ናት ብሏል።

በተጨማሪም፡ በዚህ ተቃውሞ ሁኔታ ድምጻቸውን በማሰማታቸው የታሠሩ ዜጎች፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላትና ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ጥያቄውን እንደገና አቅርቧል።

ይህን አጋጣሚ በመጠቀም፡ እንደዚህ ዐይነት ሃሣቦች ሲቀርቡ በኢሣት በኩል አንድ ቅር ያሰኝንን ነገር ለማንሳት እንወዳለን። ኢሣት በኢትዮጵያውያን መዋጮ የሚተዳደር ሆኖ ሳለ ታህሳስ 31/2015 በተላለፈው የማዕደ ኢሣት ፕሮግራም ላይ የተረጨው ኃላፊነትና ግንዛቤ የጎደለው አባባል፣ “የታሠሩት እንዲፈቱ፡ ለተጎዱት ካሣ እንዲከፈላቸው…” በተለያዩ ዜጎች የተደረጉትን ጥሪዎች “የሞኝ ለቅሶ ደግሞ ደጋግሞ” ብለው ማሾፋቸው ከኢሣት ሚዲያ የሚጠበቅ አልነበረም። እንደ አንድ የኢሣት ደጋፊና አባል እጅግ አሳዝኖኛል፤ አስቆጥቶኛል፤ አሳፍሮኛልም።

እንደሚገባኝ ከሆነና በአባልነትም መብቱን እስከ ሐምሌ እንዳስከበረ አድማጭ፡ የኢሣት የሚመሰገነው አሰተዋጾ መረጃ በማቅረብ የሥራ ድርሻ እንጂ የፕሮግራሙ አባላት የራሳቸውን የግል ስሜት የሚያሠራጩበት ሚዲያ መሆን የለበትም። በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ይህንን ለማንሳት የተገደድነው፡ በተለያዩ ጉዳዮች በግል ግንኙነት ማድረጉ ሳይሞከር ቀርቶ ሳይሆን፡ ውጤት አልባ በመሆኑ ነው – ለምሣሌ ኢሣት ወያኔን እየደጋገመ “የኢትዮጵያ መንግሥት” ማለቱ – ምንም እንኳ በግለሰብ ጥሩ ግንኙነት ለመመሥረት ቢቻልም።

ዜጎችም ሆኑ ወይንም ለምሳሌ የአሜሪካ መንግሥትም ትላንት የሠጠውን መግለጫ ዐይነቱን አንዱ ወይንም ሌላው የኢሣት ክንፍ በዘፈቀደ የራሱን የሥራ መመሪያ አውጥቶ የፈለገውን ዐየር ላይ ያውላል ማለት ነው! ታህሳስ 31 የማዕደ ኢሣት ፕሮግራም አዘጋጆቹ ያሰሙት ድምጽ – ሚዲያው ካለው የሥራ ድርሻ ኢትዮጵያ ነክ የሆኑ ዕውቀቶችን ማስፋፋት፡ ለምሳሌ ታሪክ ከታሪክ ገጾች መጭለፍና ማዝናናት ሲሆን ወያኔን ለመጣል የፖለቲካ ስትራቴጂ መንደፍ ግን የእነርሱ ሥራ አለመሆኑ ግንዛቤ ውስጥ ሊገባ ይገባል! ይህን ከፈለጉ፡ ሙያው ያላቸውን ግለሰቦች ጠርተው ሊያነጋግሩ ይችላሉ።

ይህም ግልጽ እንዲሆን በጥር 14/2016 ጽህፍ ከዚሁ ከኦሮሞ የፖለቲካ ትግል ጋር በተያያዘ ለማብራራት ሞክረናል።

ሚዲያው ባወጣውና ሲያካሄድ በነበረው ፕሮግራሙ መሠረት፡ በኢትዮያውያናን በድርጅቱ መካከል ያለው ትሥሥር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቢደረግ ኢሣት እስከዛሬ እንዳሳየው፥ ለሃገራችንና ሕዝባችን ለሁላችንም ጠቃሚ ይሆናል!

%d bloggers like this: