“ዶሮን በመጫኛ…” እንዲሉ ዘራፊዎቹና ሕገ ወጦቹ ሥልጣን ላይ ተቀምጠው በመልካም አስተዳደር ስም ሕወሃት ሶስት ፌዴራል ዳኞችን አንስቶ የራሱን ተከለ

7 Feb
አዲስ ተሿሚ የፌዴራል ዳኞችና ኃላፌዎች (ኢብኮ)

አዲስ ተሿሚ የፌዴራል ዳኞችና ኃላፌዎች (ኢብኮ)

በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)
 
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አርብ፤ የሥነ ምግባር ጥሰት የፈፀሙ በድምሩ ሶስት ዳኞችን – ሁለት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና አንድ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛን – ሹመቶች ማንሣቱ በሃገሪቱ ዜና ማሠራዎች ጥር 28 ቀን 2008 ተገለጿል።

ከዳኝነት ሹመታቸው የተነሱት ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ግዛቸው ምትኩና አቶ ኣብርሃ ተጠምቀ ኃይሌ፤ ከፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቶ ሃብታሙ ሚሊኬ ናቸው።

ምክር ቤቱ ይህንን እርምጃ የወስደው በዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የቀረበውን ውሳኔ ሃሳብ መርምሮ እንደሆነም በዜናው ተገልጿል – ፓርላማው በራሱ የሚሠራ ለማስመሰል ሕወሃት የራሱ ውሳኔ መሆኑን ሳያሳይ ማለት ነው።

በሥነ ምግባር ጉድለት ከሃላፊነት መካከል ክስ ለማቋረጥ ከተከሳሽ በእጅ መንሻነት ጃኬት የተገዛላቸውና በ2005 ምርጫ ወቅት መረሸንና ለዘመናት መታሠር ስለሚገባቸው በ129 ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ መንግሥታዊ ኃይል አጠቃቀምን ለፍርድ ቤቱ ሲያራምድ የነበረው አቶ አብርሃም ተጠምቀ ኃይሌ ረዘም ያለ ጸረ-ስብዓዊ መብቶች ከመሆናቸውም ባሻገር ለተቃዋሚ ፖለቲካ ያላቸው ጥላቻ፡ በተቻላቸው ሁሉ የሕወሃትን ዕድሜ ማራዘም ፖለቲካ መመሪያቸው መሆኑ ይታወቃል።

አቶ አብርኃ ተጠምቀ ከቀረቡባቸው አምስት የስነ ምግባር ጥሰት መካከል ከተከሳሾች ጋር ተመሳጥሮ ተከሳኞችን ሊጠቅሙ የሚችሉ ውሳኔዎችን ማሳለፍ ይገኝበታል። ግለሰቡ የተዘዋዋሪ ችሎት ዳኛ ሆነው በሚሰሩበት ወቅት፤ ከተከሳሽ ወገን በሆነ ግለሰብ መጋበዛቸው እና እንዲሁም ከላይ እንደተጠቀስው ከተከሳሽ ክሱን ለማቋረጥ በእጅ መንሻነት ጃኬት እንደተገዛላቸው ፋና ዘግቧል።

አቶ ሃብታሙ ሚሊኬም በተመሳሳይ ተከሳሽን ሊጠቅም የሚችል ውሳኔ ማሳለፍ በሚል የሥነ ምግባር ጥሰት ነው ከዳኝነታቸው የተነሱት።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዚሁ ውሎው የፌድራል ከፍትኛ ፍርድ ቤትና ለፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ድርድ ቤት ፕሬዝዳንቶችን ሹሟል። በዚህም መሰረት አቶ በላቸው አንሺሶ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት፤ ወይዘሮ ሌሊሴ ደሳለኝ እና አቶ በሪሁ ተወልደብርሃን ደግሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል።

ስለ ወ/ሮ ሌሊሴ ምንም ዐይነት ዜናም ሆነ መረጃ አልተገኘም።

አቶ በላቸው በዲፕሎማ በመምህርነት የሠለጠኑ ሲሆን፣ ቀጥሎም በሕግ ትምህርት ከሲቪል ሰርቪስና አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዲግሪዎችን ተቀብለዋል። የሥራ ልምዳቸውን በተመለከተ በደቡብ ክፍልና በፌዴራል ፍርድ ቤት ዳኝነት፡ እንዲሁም ሃድያ ውስጥ ሠርተዋል።

አቶ መሃመድ አሕመድ ደግሞ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተሹመዋል። ትምህርታቸውንም ያጠናቀቁት ከአዲስ አበባና ከሲቪል ሰርቪሽ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ትምህርት መሆኑ ታውቋል።
 

ተዛማጅ ጽሁፎች፡

አብርሃም ተጠምቀና የ2005 ምርጫ ወንጀል ሲያሳድደው

ቅንጅት መበላት አለበት ሲል የነበረውን አብርሃም ተጠምቀን ውርደቱ አሳደደው

Ethiopian opposition leaders face death penalty in show trial

Ethiopia seeks death penalty in opposition case

Charges filed against Ethiopian opposition activists

5 VOA journalists charged in Ethiopia press clampdown

የመላኩ ፈንታና ገብረዋህድ ወልደጊዮርጊስ እሥርና ክስ ላይ በሪሁ ተወልደበርሃን ክስ ሰሚና ወሳኝ ነበር

የዞን ዘጠኞች ፈተናና ዳኛ በላቸው አንሺሶ

መንግሥት የፍርድ ቤቶችን ሥልጣን አዝማሚያው ጠንካራ ነው
 

%d bloggers like this: