የኢትዮጵያውያን ባለቤትነትና ግልጽ ተሳታፊነት በሌለበት በኢትንዱስትሪ ፓርኮችና የኤኮኖሚ ዞኖች መስፋፋት ስም ሕወሃት አሁንም የመሬት ዘረፋውን አስፋፍቶ ሊቀጥል ነው!

8 Feb

የአዘጋጁ አስተያየት፡

ገና ከመጀመሪያውም የመሬት ዘረፋውን የመሩት የሕወሃት ሰዎች፣ በተለይም መለስ ዜናዊ፡ አርከበ ኦቁባይና ዐባይ ፀሐዪ ወዘተ መሆናቸው ይታወቃል። አሁም የኢንዲስትሪ ፓርክና የኤኮኖሚ ዞኖችን የሚስያስተባብሩት እነዚሁ ግለሰቦችና በግብርናና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተሰገሰጉት የሕወሃት ሰዎች ናቸው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ የመሬቱና ንብረቱ ተዘራፊ በመሆኑ፡ ባለፉት 25 ዓመታት ያየያውን ካየ በኋላ በምን ምክንያት ነው አመኔታውን ዘራፊዎች ላይ አሳርፎ፣ ስለግብርናው መሻሻል ሆነ ኢንዱስትሪ ግንባታው ሆ ብሎ ደጋፊ እንዲሆን የሚጠበቀው?

እስቲ ልብ ብለን እንመልከት – ሌላው ቀርቶ – የኦዲተር ጄኔራሉን ምርመራ ግኝቶችና የውሳኔ ሃብቶች በአደባባይ እያጣጣሉ የፈለጋቸውን እያደረጉ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴርስ ሥር ይህንን የሚመሩት እነማን ናቸው?

አሁንም ከነአርከበ ኦቁባይና ዐባይ ፀሐዬ አዋላጅነት ለኢትዮጵያውያን የሚተርፈው የኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ መገሥገሧ ሳይሆን፥ የሕወሃቶች መበልጸግ፡ በሥልጣን መቆናጠጥና የዜጎቻችን መርራቆት ናቸው።

ሕወሃት ያልተገነዘበው ነገር ይህ በአራቱም ማዕዘናት ለሚገኙት ኢትዮጵያውያን ግልጽ መሆኑን ነው። በዚህም ምክንያት፥ በሃገራችን እንደሚባለው፡ የሕወሃት ሰዎች ፖለቲካ ከሥሮ “የነቃ ብርሌ” ሆኗል!

=======
Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
አዲስ አበባ፣ ጥር 30 ፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአራት ክልሎች የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ሊቋቋሙ ነው።

ከሚቀጥለው ዓመት መስከረም ወር ጀምሮ ግንባታቸው የሚጀመረውና በአራት ዓመታት ውስጥ የሚጠናቀቁት ፓርኮቹ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውን ሽግግር ያፋጥኑታል ተብሏል።

የእርሻና ተፈጥሮ ሃብት፣ የዓሳና እንስሳት እንዲሁም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በጋራ ያዘጋጁት እና በጉዳዩ ላይ የሚመክር ውይይት እየተካሄደ ነው።

ፋብሪካዎቹ በኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይ እና ደቡብ ክልሎች ነው የሚገነቡት።

አዳማ፣ ቢሾፍቱ፣ መቀሌ፣ ባህርዳር፣ ድሬዳዋና ኮምቦልቻም በቀጣይ ግዙፍ የኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚገነቡባቸው ከተሞች ናቸው።

ለኢንዱስትሪ ፓርኮቹ ግንባታም መንግስት ከ1 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ መመደቡም ተጠቅሷል።

ባለፉት 10 አመታት ውስጥ አገሪቱ የ10 ነጥብ 5 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘገበች ሲሆን፥ ለዚህም ግብርናው ቁልፍ ሚና ተጫውቷል።

ይህን ግብርና መር ኢኮኖሚም በተገቢው ፍጥነት ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለማሸጋገርም የኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታን ማፋጠን ወሳኝ እንደሆነ ነው የሚነገረው።

በዚህም በኢትዮጵያ በአጠቃለይ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን 17 የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ለማቋቋም መታቀዱን ነው የኢንዱስትሪ ሚንስቴር ሚንስትር ድኤታ ዶክተር መብራሃቱ መለስ የተናገሩት።

የፓርኮች ግንባታ በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ብቻ ተወስኖ ያለውን የአግሮ ፕሮሰሲንግ ፋብሪካ በክልሎችም እንዲስፋፋ እና አገሪቱ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ የምታደርገውን ሽግግር የሚያፋጥን ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ከፍተኛ የገበያ ትስስር እና ለበርካታ ዜጎችም የስራ እድል እንደሚፈጥር ነው የተጠቀሰው።

ከአገሪቱ እየተገነቡ ካሉ ፓርኮች መካከል በ350 ሄክታር መሬት ላይ እየተገነባ ያለው የሀዋሳ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ ፓርክ የፊታችን ሰኔ እንደሚጠናቀቅ መገለፁ ይታወሳል።
ተዛማጅ ጹፎች:

Agri economic zone: Ethiopia to tweak farmland renting policy

Ethiopia attains sustainable peace only in owning its problems

 

%d bloggers like this: