የተፈራው አልቀረም! ሕወሃት በቅጥፈቱ ለመሸፋፈን ቢሞክርም፡ ሃገራችን በሕዝባዊ ተቃውሞ እየተናጋች ነው!

16 Feb

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)
 

ጥበበኛው ሕወሃት በመላ ሃገሪቱ – ብጥብጥ በተነሳባቸው አካባቢዎች ከጋምቤላ እስከ ኦሮሚያ፣ ከጎንደር እስከ ደቡብ – “ሰላም ሠፍሯል” ብሎ ጥር 8/2008 በስብሃት ነጋ የተመለመለው የሕወሃት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ አማካይነት ቢደሰኩርም ፣ ከዚያ በኋላ በተደጋጋሚ በተለያዩ ክፍሎች የሕዝብ ግጭቶች ተካሂደዋል።

በዚያን ወቅትቃል አቀባዩ ያለው፡ “በኦሮሚያ ክልል በተለይም በሶስት ዞኖች ሕዝቡ ያነሳቸውን ትክክለኛ ጥያቄዎች አቅጣጫውን በማስቀየር የተፈጠረው ሁከት ሙሉ በሙሉ ከስሟል” ብሎ ነበር። እንዲሁም “ሁከቱ እንዲከስም ሕዝቡ ያደረገው አስተዋፅኦ ከፍተኛ ነው” ያሉው ቃል አቀባዩ፥ “ጥቂት ወገኖች ያነገቡት ሴራ ግን ከሽፏል” ማለቱ ይታወሳል።

ለነገሩ ከዚያ በኋላ ነው የጋምቤላ እሳትም ሕወሃት ላይ መንደድ የጀመረው! አሁንም በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ግጭቶች በመካሄድ ላይ ናቸው!

ስለሕወሃት ባህሪና አሠራር የማይገቡን ብዙ ነገሮች አሉ፤ ከነዚህም መካክል ዋነኛው፣ ለምን ይሆን ይህ ሁሉ ቅጥፈት ያስፈለገው?

ይኸው ዛሬ ደግሞ ከአንድ ወር በኋላ ስለዚሁ ጉዳይ ለመናገር በቴሌቪዥን መስኮት ሳይቀር ብቅ ብሎ፣ ሕወሃት የሃገራችን ጥፋት መንስዔ ሆኖ ሳለ፡ የሚከተለውን በሃሰት የታጀለ ክስ አሰምቷል፦
 

Com Minister Getachew Reda“አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምእራብ አርሲ ዞን ሁከት የመፍጠሩ እና የሰው ህይወት የማጥፋቱ ድርጊት በታጠቀ ሀይል የተፈፀመ የአመፅ ተግባር መሆኑን መንግስት ገለፀ።

በዞኑ ሻላ ወረዳ ፀረ ሰላም ሃይሎች ሃይማኖት እና ብሄርን መሰረት ያደረገ ሁከት ለመፍጠር መሞከራቸውን የአካባቢው ምንጮች ገልፀዋል።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሸን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ዜና መፅሄት እንደተናገሩት፥ በሁከቱ የተወሰኑ የታጠቁ ቡድኖች ተሳታፊ ሆነዋል።

ታጣቂ ቡድኑ በመንግስት ተቋማት ላይ ጥቃት ለመሰንዘርም ሙከራ አድርጎ ነበር።

በሁከቱ ወቅት ጥቃት ከደረሰባቸው የመንግስት ደን እና ማሳ በተጨማሪም የሀይማኖት ተቋማትም ኢላማ ተደርገው እንደነበር የጠቆሙት አቶ ጌታቸው፥ በድርጊቱ ምናልባትም የአክራሪዎች እጅ ሊኖር እንደሚችል ምልክቶች እንዳሉ የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል።

ሁከቱን ለማስቆም በአካባቢው የፀጥታ ሃይሎች መሰማራታቸውን አንስተው፥ የታጠቀው ቡድን ግን ተኩስ በመክፈት በተወሰኑ የፀጥታ ሃይሎች ላይ ግድያ መፈፀሙን ጠቅሰዋል።

በአሁኑ ወቅት አካባቢው ወደተለመደው ሰላማዊ እንቅስቃሴ መግባቱንና በዚህ የአመፅ እና ሁከት ወንጀል የተሰማሩ ሃይሎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ተግባርም መጀመሩን ነው የገለፁት።

ቀሪዎቹን ተጠርጣሪዎች ለይቶ በቁጥጥር ስር ለማዋልም መንግስት ጥብቅ ክትትል እያደረገ እንደሚገኝም አቶ ጌታቸው ገልፀዋል።

ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት በማድረግ እንዲህ ዓይነቱን ድርጊት ከማውገዝ አልፎ እንዲከላከል ለማስቻል ስራዎች መጀመራቸውንም አቶ ጌታቸው ተናግረዋል።

መንግስት በድርጊቱ የአክራሪነት ምልክት ታየ ይበል እንጂ ሙሉ በሙሉ መነሻው እሱ ነው ብሎ አይደመድምም ያሉት ሚኒስትሩ፥ ሆኖም ህብረተሰቡ ከእንደዚህ ዓይነቱ ጠባብ የፖለቲካ እና አክራሪነት ዓላማ ራሱን እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

መንግስትም ከህዝቡ ጋር በመሆን በፅንፈኛ የፖለቲካ ሀይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ መውሰዱን ይቀጥላልም ነው ያሉት።”

መረጃ የሕወሃት ሞኖፖል  ብቻ ባለመሆኑ፡ በፌስ ቡክና በሌሎችም መገናኛ መሣሪያዎች በተሰባሰበ መረጃ ከኦሮሞ ተቃውሞ ወገኖች እንደምንሰማው ከሆነ፣

  *   There has been an overnight protest in east Shawa and West Arsi towns such as Bulbula, Shashemene, Batu & Siraro towns.

  *  “ደቡብ ኢትዮጵያን ከአዲስ አበባ የሚያገናኘው መንገድ መቋረጡ” ተዘግቧል!

  *   An oil tanker owned by TPLF’s Trans-Ethiopia has reportedly been burned down in Batu town, East…

  *   There was an “intense demonstration underway in Kofale town, West Arsi. The protest erupted in response to…”

 

ከጥቂት ሰዓታት በፊት፡ ኢሣት እንደዘገበው ደግሞ፡

  *   “ኦሮሚያ ማለት የሰው መታረጃ ቦታ ሆኗል። ሻሸመኔ ቄራ ሆኗል፣ ቄራ ሆኗል አሁን አጄ… ሕገ መንግስት የሚባል የለም። ሰላማዊ ሰው በሰላም ውሎ ቤቱ መመለስ አይችልም። ሰው ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይታሰራል፣ በየቦታው ይገደላል…ፍትሕ የለም”

  *   ዛሬ ከሦስት በላይ ፌደራል ፖሊሶች ተገደሉ ከተባለበት አርሲ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች የተናገሩት ነው። ሕዝባዊ ተቃውሞን ለማስቆም መንግስት በወሰደው እርምጃ ሠርገኛ ተገድሏል። ግድያው ሕዝብዊ ንቅናቄውን ቁጣ አላብሶታል።

  *   በኢትዮጵያ ያለውን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ሸሽተው ወደ የመን የተሰደዱ ዜጎች በሳውዲ ዐረቢያ ድንበር ጠባቂዎች፣ በሁቲ አማጺያን እና በሕገወጥ ሰው አዘዋዋሪ ሽፍቶች በጅምላ ሲታሰሩ በሌላ በኩል ከዚህ የተረፉት የሳውዲ ጀቶች የሚያዘንቡት ቦምብ ሰለባ እየሆኑ ነው።

  *   ዶክተር መረራ ጉዲና በኦሮሚያ ክልል ስላለው ተቃውሞ እና በቁም እስር ላይ ስላሉት አቶ በቀለ ነጋ እና ሌሎች እስረኞች ይናገራሉ!

የንጹሃንን ደም በከንቱ ማፍሰስና ለፖለቲካ ግብ በሕዝብ መካከል ደም መፋሰስ እንዲፈጠር ችፍግሮንና መቃቃሮችን መፍጠር ተጠያቂ ያስደርጋል! ስለዚህ፣ ለሕወሃቶች ጥቅም ሃገራችን የዝሕብ መጨፍጨፋና መጨፋጨፍ እንዳይደርስባት፡ ሕዝብ አንቅሮ የተፋው ሕወሃት በጊዜና በሰላም ስልጣኑን ቢያስረክብ ተጠቃሚ ይሆናል!

ሕዝብ የሚቀጣው ነፍሰ ገዳዮችንና ዘራፊዎችን ብቻ ነው!
 

%d bloggers like this: