በኦሮሚያ ምዕራብ አርሲ በተቀሰቀሰ ግጭት ሰባት ፖሊሶች ተገደሉ ይላል ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ               – ስንት ወጣቶች እንደተረሸኑ ግን አልገለጸም!

17 Feb

በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)

ከሕወሃት ቃል አቀባይ በአርሲ በመካሄድ ላይ ስላለው ሕዝባዊ አመጽ የራሱን ጥምዘዛ ጨምሮበት የተሠጠው መግለጫ፣ አርሲ ውስጥ በስፋትና በተለይም ኮፈሌ ውስጥ በአጋዚ ነሐሴ 3/2012 በግፍ የተረሸኑትን የኦሮሞ ወጣት ተማሪዎችና ገበሬዎች ጭፍጨፋና ግድያ ያስታውሰኛል። በወቅቱ ሕወሃት በወሰደው እርምጃ የተገደሉትና በገፍ የታሠሩት 1,500 ተቃዋሚዎች የእስልምና እምነት ተከታይ ሽብር ፈጣሪዎች አደጋ ሊያደርሱ ሲሞክሩ ተደርሶባቸው ነው ብሎ ነበር።

ጊዜው ብዙ ቢያልፍም፣ የሕወሃት አስተዳደር አስተሳሰብ እዚያው የነበረበት ላይ ተክንችሮ በመምቅረቱ፣ ችግራችን እየከፋ ቢሄድም፣ ሕወሃት የሚፈልገውን ማግኘት እንደማይችል ግልጽ የሚያደርግ መሆኑን ለማሳየት፣ ይህ ሁኔታ ምን መልክ ይዞ እንደነበር ያለፈውን ከአሁኑ ጋር በማያያዝ አንዳንድ ነገሮችን ለማመላከት ይሞከራል።

ለነገሩ በወቅቱ የአሜሪካው ሚዲያ CNN ስለዚያ ሁኔታ የሚከተለውን ዘገባ አቅርቦ ነበር፦

  “August 3, 2013 – Ethiopian government forces open fire on unarmed demonstrators throughout the country, killing 25 and injuring dozens more, according to Ethiopian activists who took part in the demonstrations.

  One witness says at least one child was among the dead. He also stated government security forces arrested over 1,500 protesters on Friday.

  For over a year, Ethiopian Muslims have been holding peaceful protests and mosque sit-ins over the regime’s human rights abuses against their community and interference in their religion.”

 

ዛሬም እንደተለመደው ሕወሃት በእጁ ያለውን ማናቸውንም ሚድያ በመጠቀም ካለፈው ስህተቱ ባለመማር፡ ቅጥፈቱን በመንዛት ላይ ይገኛል። ይህ የወንበዴዎች አስተዳደር ዛሬም በግድያና ዘረፋ ብቻ በመቀጠሉ የሃገሪቱ የወደፊቱ ዕጣ ፈንታ ያስፈራኛል!

ለዚህም ነው – የአውሮፓ ኅብረት ውስጥ እነፌድሪካ ሞገሪኒ የአካባቢውን የስደት መንሲዔ ችግር ላይ ማተኮር ሲገባቸው – በእኔ ግምት ከሕወሃት ጋር በመመሳጠርና በመሞዳሞድ – ችግሩ እንዲያመረቃ ማድረጋቸውን የምቃወመው!

ዛሬ ሪፖርተር እንደዘገበው፡ “ቁጥራቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች ተገድለዋል፤ የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት ተቃጥለዋል፡፡” ዝርዝሩን ከዚህ በታች ይመልከቱ፦

  ኮሚኒኬሽን ኃላፌ ጌታቸው ረዳ (ፎቶ ሪፖርተር)

  ኮሚኒኬሽን ኃላፌ ጌታቸው ረዳ
  (ፎቶ ሪፖርተር)

  “በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን በተቀሰቀሰ ግጭት ሰባት የፖሊስ አባላት ተገደሉ፡፡ በፖሊስ አባላትና በታጣቂዎቹ መካከል በተፈጠረው በዚህ ግጭት ግን የሞቱት የታጣቂዎች ቁጥር አልተገለጸም፡፡

  ግጭቱ የተቀሰቀሰው ሰኞ የካቲት 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ሲሆን፣ ከተገደሉት ሰባት የፖሊስ አባላት በተጨማሪ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት፣ ማሳዎች፣ ደንና የመንግሥት ተቋማት መቃጠላቸውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰበት ምክንያት እየተጣራ መሆኑን የገለጹት አቶ ጌታቸው፣ የታጠቁት ሰዎች መስጊድና ቤተ ክርስቲያን ሳይቀር ማቃጠላቸውን ተናግረዋል፡፡

  በምዕራብ አርሲ ዞን የተቀሰቀሰው ግጭት በተለይ ሻላ፣ ሲራሮና ሻሸመኔ ወረዳዎች ውስጥ በስፋት ተከስቶ ነበር፡፡ ሪፖርተር ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች የግጭቱ መንስዔ የፖለቲካ ይዘት ያለው ዘፈን መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት፣ በኦሮሚያ ክልል እንዳይዘፈን የተከለከለው የአጫሉ ሁንዴ ዘፈን በአንድ ሠርግ ላይ ይዘፈናል፡፡ ዘፈኑን ለምን አዘፈናችሁ የሚል ጥያቄ ካቀረቡት የፖሊስ አባላት ጋር በተፈጠረው አለመግባባት፣ ግጭቱ መከሰቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

  በምዕራብ አርሲ ዞን በተቀሰቀሰው ግጭት ሰባት የፖሊስ አባላት፣ ቁጥራቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች እንዲሁም ከፍተኛ የንብረት ውድመት የደረሰ ሲሆን፣ ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ወደ 12 የሚደርሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አቶ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡

  አሁን የተቀሰቀሰው ግጭት በቅርቡ በኦሮሚያ ተከስቶ ከነበረው ግጭት ጋር የሚያያዝ መሆኑን የተጠየቁት አቶ ጌታቸው፣ የግጭት ባህሪ የተቀየረና የሃይማኖት ተቋማት ላይ ሳይቀር ያነጣጠረ በመሆኑ ተከስቶ ከነበረው ግጭት ጋር እንደማይገናኝ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ነገር ግን የግጭቱ መንስዔ እየተጣራ በመሆኑ እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም፤›› ብለዋል፡፡ አቶ ጌታቸው አክለውም ግጭቱ የተከሰተበት የምዕራብ አርሲ ዞን በአሁኑ ወቅት መረጋጋቱን ገልጸው፣ የአካባቢው ሽማግሌዎችም ኅብረተሰቡ ወደ መደበኛ የዕለት ተዕለት ተግባሩ እንዲመለስ የማረጋጋት ሥራ እየሠሩ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
  የሪፖርተር ምንጮች ግን በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች መከሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

  በቅርቡ የአዲስ አበባና ዙሪያዋ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ማስተር ፕላን ተግባራዊ መደረግ የለበትም በሚል በኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ከ140 በላይ ሰዎች መሞታቸውን፣ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ገልጸዋል፡፡ ከዚህም ባለፈ ከሦስት ሺሕ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የገለጹት የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች የተደበደቡ፣ የቆሰሉና የደረሱበት ያልታወቀ ሰዎች መኖራቸውን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡ ይህ ግጭት ሞት፣ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ከማድረሱ በተጨማሪ በሕዝብ መገልገያዎች፣ በግለሰቦች ንብረት፣ በመንግሥት ተቋማት፣ በተሽከርካሪዎችና በመሳሰሉ ንብረቶች ላይ እስካሁን መጠኑ ያልታወቀ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል፡፡

  የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ከሕዝብ በደረሰበት ጫና የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የጋራ ማስተር ፕላን እንዲቆም የወሰነ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በራሱ ክልል የሚገኘውን የማስተር ፕላኑን ክፍል ብቻ ተግባራዊ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

  መንግሥት በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በደረሰው ግጭት የደረሰውን የጉዳት መጠን እስካሁን በይፋ አልገለጸም፡፡”

 

ሐምሌ 28/2005 ፋና ይህንኑ አስመልክቶ የሚከተለውን ዜና አስፍሮ ነበር፦

“በኦሮሚያ ክልል አክራሪዎች በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት አደረሱ

  Oromia policeOromia police አዲስ አበባ ሐምሌ 28፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ አርሲ ዞን በኮፈሌ ወረዳ ኮፈሌ ከተማ ውስጥ ሐምሌ 27/2005 አክራሪ ኃይሎች በፈጠሩት ፀረ ሰላም እንቅስቃሴ በሰው ህይወትና ንብረት ላይ አደጋ መድረሱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

  የሽብር እንቅስቃሴው በፖሊስና በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉንም የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጨምሮ አስታቋል፡፡

  ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ የእስልምና እምነትን ሽፋን በማድረግ ህዝብን የመከፋፈልና ሰላምን የማደፍረስ አጀንዳ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የቆዩ አክራሪና ፅንፈኛ ቡድኖች ሀምሌ 27 ቀን ከጧቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ በምዕራብ አርሲ ዞን ዋቤ ከተማ የጀመሩት ሁከት ወደ ኮፈሌ ከተማ በመሸጋገሩ ፀጥታ ለማስከበር በተሰማራው የአካባቢው የፖሊስ ኃይልና በሁከቱ ተሳታፊዎች መካከል በተፈጠረው ግጭት የሶስት ሰው ህይወት ማለፉና በሰባት የፖሊስ አባላት ላይ ከባድና ቀላል አደጋ መድረሱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

  በአክራሪ ቡድኖች ተቀናጅቶ የተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማወናበድና ለሁከት በማነሳሳት ኮፈሌ ከተማ ላይ ተቀስቅሶ በሰላም ፈላጊ የአካባቢው ህዝብና በፖሊስ ኃይል በቁጥጥር ስር የዋለው ይህ የሁከት ድርጊት አክራሪ ኃይሎች ከዚህ ቀደም በ2004 ዓ.ም በዚያው ዞን ገደብ አሳሳ ላይ ጁሃድ በማወጅ ሞክረውት ከነበረው የጥፋት እንቅስቃሴ የቀጠለ ነው፡፡

  ምንም እንኳን የሁከት እንቅስቃሴው በሰላም ፈላጊው የአካባቢው ህዝብ ትብብርና በክልሉ ፖሊስ ኃይል በቁጥጥር ስር የዋለ ቢሆንም ጽንፈኞች ኃይሎቹ ህገ መንግስቱን በመጻረር የህዝብን ፀጥታ ለማወክና በሰላማዊ ዜጎች ላይ ጉዳት ለማድረስ የጀመሩትን እንቅስቃሴ ለማምከንና የጥፋቱ አቀናባሪና ፈጻሚ የወንጀል ተጠርጣሪዎችን ለህግ ለማቅረብ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከመቼውም በላቀ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግሯል።

  ሰላም ወዳዱ ህዝብ ከመንግስት ጋር በመሆን አጥፊዎችን በማጋለጥና የአካባቢውን ሰላም በመጠበቅ የተለመደ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል፡፡”

 

በወቅቱ ይህ ብሎግ የሚከተለውን አስተያየት ሠንዝሮ ነበር፡

  “…[I]mmediately after the TPLF forces mowed down the victims in the town of Kofele, Arsi, in Oromia Regional State – without even warning shots into the air – the regime put out a news item on its news agency Fana page that “Moslem extremists” that tried to undermine peace and order were dealt with by Oromia Police, with support from the public.

  The title of this news item clearly speaks to what the government needed Ethiopians and people around the world to think: “Extremists caused damages to life and properties in Oromia Zone“. It would not also be farfetched to assume that the government had pre-planned this massacre.

  It would be recalled that on Thursday August 1, 2013, before the Friday Mosque prayers came the National Police Commission issued a statement warning that it would take action if Moslem extremists continued their protests around Mosque, as they have been doing for the last 19 months.

  In that statement, the commission said: “በመሆኑም እነዚህ ወገኖች በዛሬው እለት በሀይማኖት ሽፋን በመስጊዶች ውስጥ የሚያካሂዱትን የጥፋት ድርጊት ለማስቆም ፖሊስ ተገቢና አስፈላጊውን እርምጃ የሚወስድ መሆኑን በመግለጫው በጥብቅ አሳስቧል።” TRANSLATION: “Therefore, to end once and for all destructive actions in and around mosques by those that masquerade in the name of religion, the police would like to make it known that it would take the requisite action.”

  Since the protestors in Addis Abeba did not want to give the opportunity to the regime it was fishing, none of the religious celebrants attended prayers rites and their protests in mosques in Addis Abeba on Friday, August 2nd.

  Therefore, the action moved to towns outside Addis Abeba, where many protests had taken place.

  The Kofele Massacre from an eyewitness account

  As far as the Kofele incident is concerned, an eyewitness to whom ESAT has spoken from Kofele stated, the commandos used heavy weapons, including tanks and personnel carriers, when they came and directly charged against the people. He said there was not even warning shots fired into the air.

  This witness also underlined that the people were peacefully protesting, when they were suddenly attacked. The government was accused of behaving as terrorist, instead of the peaceful protestors, as could be heard from the video below.

  The number of the dead was reduced to eleven, while numerous people have been injured. There is concern that the number of the dead could rise in the days to come.

  It is also reported that a very significant number of people have been arrested, mostly young people. The cause of this latest protest is the regime’s arrest of an elderly Mosque leader. People were demanding his release.

  The protest has spread to adjoining rural towns, people suffering similar fates in those areas too.”

 

ምነው ብዙ አማራጮች ሲኖሩ፡ ድብ ይመስል ሕወሃት አጥፍቶ መጥፋትን መረጠ?
 

ተዛማጅ ጽሁፎች:

የተፈራው አልቀረም! ሕወሃት በቅጥፈቱ ለመሸፋፈን ቢሞክርም፡ ሃገራችን በሕዝባዊ ተቃውሞ እየተናጋች ነው!

State intervention in religion in Ethiopia deepens anti-regime sentiments; tensions, sporadic clashes commonplace

CPJ says crackdown will not resolve dispute with Moslems

Authoritarianism & state violence: Major causes of Ethiopia’s political crisis & resulting human tragedies
 

%d bloggers like this: