በወልቃይት ሕዝብ ፊርማ የተደገፈ አቤቱታ ይዘው ወደ ፌዴሬሽን ም/ቤት ከሄዱት ባየው ካሰኝ ዛሬ ታሠሩ፤ በሕወሃት ግፊት ገሚሶች ጸገዴ ሠልፍ አድርገው በአስተዳዳሪው ‘ትግሬዎች ናችሁ’ ተባሉ!

24 Feb

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

በወልቃይት የሕዝብ ፊርማ የተደገፈ ደብዳቤ ይዘው ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሄደው ከነበሩ መካከል የነበሩት አቶ ባየው ካሰኝ ዛሬ ከቀትር በኋላ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል።

ዋሽንግተን ዲሲ — በወልቃይት የሕዝብ ፊርማ የተደገፈ ደብዳቤ ይዘው ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሄደው ከነበሩ መካከል የነበሩት አቶ ባየው ካሰኝ ዛሬ ከቀትር በኋላ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገልጿል።

አቶ ባየኝ የተያዙት ከጎንደር ወደ ሚኖሩበት ቀበሌ እየተጓዙ ሣሉ ዳንሻ ከተማ ከመግባታቸው በፊት ባለው መከዞ የሚባል ኬላ ላይ መሆኑን የኮሚቴው አባል የነበሩት አቶ አታላይ ዛፌ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

ከአቶ አታላይ ዛፌ ጋር ለተደረገው ሙሉ ቃለ-ምልልስ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ቀደም ሲልም የአቶ ባየው የአራት ዓመት ልጅ ተጠልፎ እንደነበረ የገለፁት አቶ አታላይ በሌሎችም የኮሚቴው አባላት ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሚሰማ፤ የማይ ካድራ ነዋሪ የሆኑት አቶ ፀጋዬ ውብነህ የሚባሉ የኮሚቴው አባል የሆኑ ሰው በሌሊት በደረሣቸው ማስፈራሪያ ከሚኖሩበት መፈናቀላቸውን፤ አቶ መብራህቴ ታከለ የሚባሉ ሰው በአንድ የቀበሌ ሊቀመንበር በጠርሙስ ፊታቸው ላይ መመታታቸውንና ሌሎችም የወከባ አጋጣሚዎችን ዘርዝረው አስረድተዋል።

ቀደም ሲል ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት የገባውን ፊርማ የፈረሙ ሰዎች በፖሊስና ሲቪል በለበሱ ሰዎች እየተጠሩ ወይም ወደ ፖሊስ ጣቢያ እየተወሰዱ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሚደርስባቸው፤ “… በነጭ ወረቀት ላይ ወይም አበል ተቀበሉ ተብለው መልዕክቱን በማያውቁት ወረቀት ላይ ወይም አሳስተው ነው ያስፈረሙን እያሉ…” እንዲፈርሙ እንደሚደረጉ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለቪኦኤ ተናግረዋል።
 
______________________________________________________________________________________________________________________________

በወልቃይት ጉዳይ ሕወሃት ፀገዴ ወረዳ ውስጥ “ትግሬዎች ነን ባዮች” ባደረጉት ሰልፍ ድሉን መቀዳጀቱትን በዜና አዘገበ!

ጸገዴ ውስጥ በሕወሃት ሰዎች ገፋፊነት መንደርተኛው ተሰልፎ – ለነገሩ ከሁለት የሕወሃት ባንዲራ በስተቀር የተቀረው መሃሉ ኮከብ የሌልው የኢትዮጵያ ባንዲራ ነው! (

ጸገዴ ውስጥ በሕወሃት ሰዎች ገፋፊነት መንደርተኛው ተሰልፎ – ለነገሩ ከሁለት የሕወሃት ባንዲራ በስተቀር የተቀረው መሃሉ ኮከብ የሌልው የኢትዮጵያ ባንዲራ ነው! (

በትግራይ ክልል የፀገዴ ወረዳ ነዋሪዎች የማንነት ጥያቄያችን ተመልሷል አሁን ላይ ይህን የሚያነሱ እኛን አይወክሉም በማለት ሰልፍ ወጡ – የፀገዴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ግደይ አዘነም የሕዝቡን ትግራዊነት ማንም እንደማይነጥቀው እነርሱም ትግሬዎች እንጂ አማሮች አለመሆናንቸውን አረጋግጠውላቸዋል።

የአንድ ሃገር ሕዝብ በማንነት ጥያቄ ላይ ገሚሱ ደጋፊ ገሚሱ ተቃዋሚ ሲሆን፥ በማንነት ስም በረሃ ገብቶ የተዋጋ ኃይል እንዴት ይህንን ድሉ አድርጎ ሰላማዊ ሠልፍ ሕዝቡ እንዲያደርግ ይገፋፋል ለሚለው ጥይቄ ከሕወሃት መልስ ማግኘት አልቻልንም! በየትኛውም አቃጥጫ ቢታይ የውንብድና አስተዳደር በመሆኑ፡ በመንፈሳዊነትና ስለነጻነትና ዲሞክራሲ ትምህርት በመስጠት ትግሉ መቀጠል አለበት እንላለን።

ኢየሱስም ኢየሱስም መሰቀል ላይ ተስቅሎ ሳለ፣ ተቃዋሚዎቹ ሲሳለቁበት እንዲህ በማለት ጸሎት አደረገ፡

“አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ።”
የሉቃስ ወንጌል 23:34
==============
 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል በፀገዴ ወረዳ ፀረ ሰላም ሃይሎች የማንነት ጥያቄአቸው አልተመለሰም በሚል የሚያነሱትን ጥያቄ ለመቃወም ዛሬ ሰልፍ አካሂደዋል።

የፀረ ሰላም ሃይሎች የጀመሩት ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት ዓላማ በጥብቅ እንደሚቃወሙ ሰልፈኞቹ ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ ከዓመታት በፊት የተመለሰውን የህዝብ የማንነት ጥያቄ እና አብሮና ተስማምቶ የሚኖርን ህዝብ ለማጋጨት በአሁኑ ወቅት እንደ አዲስ እያነሱ የሚገኙትን የፀረ ሰላም ሃይሎች እንቅስቃሴን በጥብቅ እንደሚቃወሙም ነው ዛሬ ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ የገለፁት።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው አንዳንድ የወረዳው ነዋሪዎች ከዚህ በፊት በነበሩት ስርዓቶች ማንነቱን ተነጥቆ የነበረው ህዝብ አሁን ላይ ማንነቱ ተመልሶለት በልማት ስራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል ብለዋል።

አሁን ላይ የማንነት ጥያቄ እንደተመለሰ የተናገሩት ነዋሪዎቹ የህዝቡ ዋንኛ ጥያቄ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ እንደሆነም ነው በመፈክሮቻቸው የገለፁት።

ነዋሪዎቹ በቀጣይም እነዚህን ፀረ ሰላም ሃይሎች በመፋለም ለወረዳቸው ልማት እንደሚተጉም አረጋግጠዋል።

የፀገዴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ግደይ አዘነ በበኩላቸው፥ በወረዳው የሚካሄደው የልማት እንቅስቃሴ እና መልካም አስተዳደርን የማስፈን ስራው ጥረትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

በሰልፉ ላይ በሺዎች የሚቆጠሩ የወረዳው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

______________________________________________________________________________________________________________________________
*Updated.
 

    በትግራይ ክልል የፀገዴ ወረዳ ነዋሪዎች የማንነት ጥያቄያችን ተመልሷል አሁን ላይ ይህን የሚያነሱ እኛን አይወክሉም በማለት ሰልፍ ወጡ

 

%d bloggers like this: