ቤተ እምነቶች የሰው ሕይወት ጭፍጨፋና የንብረት መውደም እንዲቆም የጠየቁ አስመስለው በኦሮሚያ የእኩልነት ትግል ላይ የተነጣጠረ አቋም አንጸባረቁ!

25 Feb

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)
 

የሕወሃት ፋና ረቡዕ የካቲት 24/2016 ባወጣው ዜና “የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በሰው ሕይወት፣ በእምነት ተቋማትና በሕዝብ ሃብት ላይ የደረሰውን ጥፋት አወገዘ” በማለት ያቀረበውን አንብቤያለሁ።

ሪፖርተር እንደ ዘገበው ከሆነ ደግሞ፡ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ፣ “ለዘመናት የተመሰከረልን አብሮ የመኖርና የሃይማኖት መቻቻልን ጥላሸት የሚቀቡ አጋጣሚዎችን በመጥቀስ፣ ሽማግሌዎች የሌሉበት አገር የሚባልበት ጊዜ ላይ ተደርሷል” የሚል ሃሣብ ሲሰነዝሩ የተጨቆኑና የተረገጡ ዜጎች ለመብታቸው የሚያደርጉትን፡ ሕይወታቸውን የሰውለትን ትግል የሃይማኖት ግጭት አድርገው አቅርበውታል። እርሳቸው እንደሚሉት አንዱ ወገን በሌላው ሃይማኖት ላይ ጥቃት ሠንዝሮ ከሆነ አጥብቀን እንቃወማለን።

ነገር ግን የእምነት ሰዎቹ በተናጠል በዚህና በንብረት ጥፋት ላይ ብቻ ማተኮር፡ በሌላ በኩል በሕዝቡ ላይ እየፈጸመ ያለውን መንግሥታዊ አሸባሪነት (state terrorism) ችላ ያለና፥ እንደውም በከፋ መንገድ ለማደባበስ የሚሞክር መስሏል።

ረቡዕ ተሰበሰቡ የተባሉት ከሰባቱ ሃይማኖት ክፍልቾ የተውጣጡት ግለሰቦች፣ አባዛኞች በሃገራችን የተለያዩ ክፍሎች የሚገኙት ተወካዮቻቸውና በዛሬው ስብሰባ ተካፋይ የሆኑት ሁሉ፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ውስጥ በሚገኙ የደኅነነት ሰዎችና በፓትርያርኩ አማክይነት ከዚህ በፊት ለእምነት ነጻነት እንደተከራሩት እስላሞች ላይ እንደተፈጸመው ሁሉ – ለሕወሃት ተገን ለመሆንና ኅብረተሰቡን ለመከፋፈል ብለውም በኦሮሚያ ውስጥ የሚካሄደው ትግል አጋር እንዲያጣ የሚጎነንጎን ሴራ ነው!

ለማንኛውም ይህ አካል የዛሬ ስድስት ዓመት ሲቋቋም፡ በእስልምና እምነት ተከታዮች ላይ ተጸዕኖ ለማሳደርና የተሳካለትም በመሆኑ፡ አሁም ሕወሃት የሃገሬውን ሕዝብ ልብ ወደ ራሱ ለመሳብና ለሚፈጽማቸው ግድያዎችና ዘረፋዎች ሽፋን እንዲሰጡት የተጠራ ጉባዔ ነው የሚለውን ጥርጣሬ አጠናክሯል።

የዚህ ጉባዔ አባላት ለሃገሪቱና ለሕዝቡ ተቆርቋሪ መስለው፡ አሁን የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ለእነርሱ ለራሳቸው የሕዝቡን ቁጣና ተጠያቂነት እንዳያመጣባቸው ፈራላቸዋለሁ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ገና ቡድኑ እንደተቋቋመ የተሠራውን ያስታውሳልና፡ እንዳለፈው ጊዜ እንደማይሳካላቸው ገምታለሁ! ስብሃት ነጋ በተለይ የእስላሞቹን ተወካዮች አስመልክቶ ነው፡ የእንቅስቃሴው መሪዎች ከታሠሩና አዲስ አካል ከተቋቋመ በኋላ “አተረፉን” ሲል የመሠከረላቸውን ማስታወሱ ብቻ ይበቃል!

ይህም ኮሚቴ የሚገባው መልስ፣ ክርስቶስ በስቅለቱ ወቅት ላዘኑት የሱ ለሆኑት ሰዎች – በሉቃስ ወንጌል 23: 29-31 – የተናገረውን ነው – “እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች፥ ለእኔስ አታልቅሱልኝ፤ ዳሩ ግን መካኖችና ያልወለዱ ማኅፀኖች ያላጠቡ ጡቶችም ብፁዓን ናቸው የሚሉበት ጊዜ እነሆ ይመጣልና ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ።”

ዜጎችም ሆን የውጭ ታዛቢዎች ዛሬ ሃገራችንን ስለሚያመሳቅለው ሕዝባችንን ስለሚያሠቃየው በሥልጣን ላይ ስላለው ወንበዴ ቡድን አንድ ነገር ያውቃሉ – ዛሬ ሳይመን አሊሰን (Simon Alison) ባቀረበው ጽሁፍ እንዳስቀመጠው፡ “የኢትዮጵያ መንግሥት የሚወደው ነገር ቢኖር ዋና ተቆጣጣሪ መሆንን ነው – ኤኮኖሚውን፣ ተቃዋሚ ኃይሎችን፣ ነጻውን ሚድያ…” ትክክለኛ ግንዛቤ ነው። የችግራችንም ምንጭ ኢትዮጵያው ውስጥ ዋና ተቆጣጣሪውን የሚቆጣጠር ኃይል – ሕግ፡ ፍርድ ቤት፡ መንፈሳዊ አካል፡ ወዘተ ደግሞ እንዳይኖር መደረጉ ነው!

መረሳት የሌለበት ነገር ግን፥ በሃገራችን ሃይማኖት ይከበራል። ኅብረተሰብም የሃይማኖት አባቶች የሚሠጡትን ምክር ያዳምጣል። ሕወሃት ሥልጣን ከያዘበት ጀምሮ ግን፡ ቤተ ክርስቲያኗ ያ ክርስቶስ ጸሎት ቤት ውስጥ ገንዘብ መንዛሪዎችና አራጣ አበዳሪዎች የሚዳሩበት ሆኖ ስላገኝው – በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 21 እንደተመሠከረው – እነርሱን አባሮ ቤተ እምነቷን ሰለ ማጽዳቱ የተነገረው በየግል ጭንቅላታችን ውስጥ መመላለሱን አይገታውም!

ሕወሃት ቤተ ክርስቲያን ራሷ በዘር እንድትደራጅ አድርጎ፣ ላለፉት ዓመታት በተከታታይ ታዋቂ የፖለቲካ ካድሬዎች የሆኑ፣ ዐይኖቻቸውን በጨው አጥበው፣ ከሕዝብ አገልግሎት ርቀው ሃብት በመዝረፍ፥ ለሥጋቸውና ለምድራዊው ጣዕመ ሕይወት ቅድሚያ ሠጥተው የኖሩ ግለሰቦች ጳጳሶች አድርጎ መሾሙን አናስታውሳለን! አቡነ ጳውሎስም የሰው ሚስቶች ጭምር አስጠግተው የኖሩ መሆናቸውን በቅርብ ያሉት የሚያውቁት ሃቅ ነው።

የሰባቱም የሃይማኖት ተቋማት ተጠሪዎች፣ የጉባዔው የቦርድ አባላትና የበላይ ጠባቂዎች በተሰየሙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ሊቀመንበር ሼክ መሐመድ ኡመር አሚንና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፌል (ፎቶ ሪፖርተር)

የሰባቱም የሃይማኖት ተቋማት ተጠሪዎች፣ የጉባዔው የቦርድ አባላትና የበላይ ጠባቂዎች በተሰየሙበት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ሊቀመንበር ሼክ መሐመድ ኡመር አሚንና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ካርዲናል አቡነ ብርሃነየሱስ ሱራፌል (ፎቶ ሪፖርተር)


 

በውቅቱ የአቡነ ጳውሎስ ዓለማዊነት ፈጸሙ የሚባለውን ሥጋዊ ተግባር፡ አስመልክተንና ዛሬም ያለውን አገናኝተን በቅርቡ ብዙ መጻፋችንን አንባብያን ያስታውሳሉ። የጻፍነው ውስጥ ውስጥ የሚከተለው ይገኝበታል፦:

  “የዝሙት ርሃባቸው [የአቡነ ጳውሎስ] ከከፍተኛ በመሆኑ፣ ከሆሊውድ እንጂ ከኢትዮጵያ እምነት ቤት የመጣ አይመስልም! በተለይም አስከፊው በሽታቸው ደግሞ የሚያውቋቸው ግለሰቦች ምሽቶች መሆናቸው፡ አሥርቱ ዕዛዛትን ምን ያህል አርቀው እንዳሽቀነጠሩ የሚያመላክት ነው! ታዲያ አቡነ ጳውሎስ በትዳር ያሉ ሴቶችን ሲያቀያይሩ የነበሩት ቤተ ክርስቲያኗን በመድፈር አልነበረምን?”

በቤተ ከርስቲያኗ ላይ የደረስውን ውርደት ሩስያ ታሪክ ውስጥ ተጠቃሽ ስለነበረው የእምነት ፈዋሹ፡ የቤተ ክርስቲያንና የቤተ መንግሥት ስብዕ የነበረው ‘እብዱ’ ጊዮርጊ ራስፑቲን ጋር አመሳስለን ቅሬታዎቻችን ጥቅምት 25/2015 በዚሁ አምድ ላይ ማቅረባችን ይታወሳል።
==========
 

ዓሣ ግማቱ የሚጀምረው ከአናቱ እንደሚባለው፣ አኩሪ ረዥም ታሪክ ያላትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ለውድቀት የዳረጋት ወንበዴው ሕወሃት ነው። በአንድ ወቅት አስታውሳለሁ፥ የሕወሃት አመራር ላይ የነበረው ዶ/ር አረጋዊ በረሄ ሕወሃት ካድሬዎቹን የካህናት ልብስ እያለበሰና መሣሪያ እያስታጠቀ በየደብሩና በሕዝቡ ውስጥ ማሠማራቱን አስታውሶ ለኢሣት ሲናገር አዳምጫለሁ።

የአሁኑ ካድሬው ጳጳስ ማትያስ ሥልጣኑን ከተረከበ ወዲህ፥ በዙርያው ያሰባሰባቸው የራሱ ብሔር ሰዎችና ብቃታቸው በደኅንነቱ ጌታቸው አሰፋ፡ ስብሃት ነጋና በጥጋበኛና ጉበኛው ዐባይ ፀሐዬ አማክይነት ምስክርነት የተሠጠላቸው የሌላ ብሄረስብ ግለሰቦች በሁለተኛ ደረጃ ከሩቁ እንዲጠጉ መደረጉ፣ ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ በድጋሚ ከቤተ ክርስቲያኗ ውስጥም ውጭም የሕዝብን ትዕዝብት ያተረፈ ነገር እንደሆነ ይታወቃል።

ከዚህ አልፎ ተርፎ፡ በሃይማኖት ሳይከፋፈል ተከባብሮና ተፋቅሮ የኖረውን የኢትዮጵያን ሕዝብ በሃይማኖትም ለመከፋፈል ከፍተኛ ያልተሳካ ጥረት ተደርጓል፤ ዛሬም እየተደረገ ነው – አልተሳካላቸውም እንጂ!

ይሁንና፣ ዛሬ ቤተ ክርስቲያኗ ለስም አለች እንኳ ቢባልም፣ ሕልውናዋ በሰዶምና ጎሞራ ከነበሩት ዓለማውያን አሳሂ መሲሆች የተለየ ባለመሆኑ፡ ሕወሃት የሚሚመራት የዛሬይቱ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለምንም ነገር – እንደ ሕወሃት ሁሉ – የመንፈሳዊና ሞራላዊ፡ እንዲሁም ኅብረተሰባዊ መተሳሰብና ብቃት ስለሚጎድላት፣ ሃገራችን በሥጋ ፍቅራቸው በተሳከሩ ደናቁርት ግራ መጋባቷ፥ በየወቅቱ ንፋስ እንደመታት ጀልባ ከአንድ ችግር ወደ ሌላው ስትደነቃቀፍ ትታያለች።

ለዚህም አይደል እንዴ፣ ሲኖዱ ባለፈው ዓመት ስብሰባው ከፍ ዝቅ አድርጎ የካድሬ አቡነ ማትያስን የዘር ፖለቲከኛነትና ለሕወሃት አስተዳደር የቅርብ አቀንቃኝነት ችግር በመገንዘብ፡ የሚከተለውን የባህሪና ሥራ መመሪያ ለመዘርዘር የተገደደው:

  * “ተጠሪነትዎ ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ በቤተ ክርስቲያን ሕግ ቢመሩ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱን ቢያከብሩ ይሻልዎታል፤ ሕግ አይገዛኝም ካሉ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንሔዳለን፡፡” /ቅዱስ ሲኖዶሱ/

  * “በቅ/ሲኖዶስ ከተወሰነው በተፃራሪ ማኅበሩ ለልዩ ጽ/ቤታቸው ሳያሳውቅ አንዳችም መርሐ ግብር እንዳያከናውንና ከስብሰባው መጠናቀቅ በኋላ የሚወስዷቸውን ሕገ ወጥ ርምጃዎች መከላከልን በተመለከተ መመሪያ እንዲሰጥ ብፁዕ ዋና ጸሐፊው እና ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጠይቀዋል፡፡

  * “ማኅበራት ገንዘባቸውን ወደ ማእከላዊ ካዝና ያስገቡ ይላሉ፤ የማኅበራት ዓላማ ገንዘብ ማሰባሰብ አይደለም፤ ገንዘብ አሰባሳቢ አይደሉም፤ ለተቋቋሙበት ዓላማ ያሰባሰቡትን ገንዘብ ግን እንዴት ሥራ ላይ እንዳዋሉት መቆጣጠር ይገባል፡፡”

  * “ዓላማዎ ማኅበሩን መዝጋት ነው፤ አይደለም? አይዘጋም!”

የኢትዮጵያ ሕዝብ አስተዋይ በመሆኑ፡ ሁሉንም ነገር በጸጥታ ይታዘባል። በመሆኑም፥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሃገራችን ውስጥ እጅግ ሃብታም ብትሆንም፣ ዘመነ ካድሬዎች ጳውሎስና ማቲያስ ለቤተ ክርስቲያኗ አልተመቻትም። አማንያኑም በብዛት ቤተ ክርስቲያኗን እርግፍ አድርገው ትተዋል፣ በራሱ በካድሬ ጳጳስ ማቲያስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዳለው – “ብዙ ቢሊዮኖች ብር አገኘን ግን አማንያን ሸሹን”!

ታዲያ በምን ሂሣብና ተዓምር ነው ‘ጳጳሱ’ ካድሬው ማትያስ ስለ የኦሮሞ ኢትዮጵያውያን ደም በከንቱ መንፈስ ዛሬ ተቆርቋሪ የሚሆነው?
===========
 

የጉባዔው ዋና ጸሃፊ መጋቢ ዘርይሁን ደጉ ባለፈው ሣምንት በምዕራብ አርሲ ዞን በአብያተ ክርስቲያናትና ንብረት ላይ ጥፋት መፈፀሙን ገልፀዋል። እኛም ይህ ተደርጎ ከሆነ ከላይ ነካ እንዳረግነው፥ ትክክል አይደለም እንላለን። እናወግዘዋለን!

በአማራና በጋምቤላ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች ስለተፈጠሩት ችግሮችና ሁኔታዎች ዋና ጸሐፊው አንስተዋል – ፋና እንደዘገበው። የእምነት ሰዎች እስከዛሬ ይህ ሁሉ ግድያ፡ ጭቆናና ዘረፋ ሲካሄድ ጸጥ ብለው ከርመው፡ አሁን ከሳሽና ፈራጅ ሆነው መቅረባቸው ግን ስላምን ለማስፈን ሚና መጫወታቸውን ድጋፍ አልባ ያደርገዋል። የሚል ሥጋት አለኝ። ምናልባትም እነርሱ በፈጠሩት ቀዳዳ ጦረኛው ሕወሃት ገብቶ ጭፈጭፋውን ሊያባብስ መንገድ ከፍቶለት፡ እነርሱም ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ!

“በእነዚህ አካባቢዎች የተፈጸሙና እየተፈጸሙ ያሉ አፍራሽ ተግባራትን ሁሉም የዕምነት ተቋማት የሚያወግዙት እንደሆነም አስታውቀዋል” ይላል ፋና። ነገር ግን ነፍሰ ጡር በአጋዚ ጥይት ስትደፋ፡ የ10 ዓመት ልጅ ሲረሸን፡ ወታደሮች ትምህርት ቤቶች ቅጥር ግቢዎች ውስጥ ገብተው አርፈው የተቀመጡትን ከ12-15 ዓመት ዕድሜ የማይበልጡት ላይ (ፎቶ) እግር በመጫን ማርበድበዱ፡ የፋሽስት ሥራ ነው እንጂ የሕዝብ ጠባቂ ሠራዊት ድርጊት አይደለም!

የዛሬይቷ ኢትዮጵያ ችግር ሕወሃት ነው። ሕዝቡን በሃገሩ በሃገሪቱ ፖለቲካ፥ ኤኮኖሚና ማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ የሰላምና የእኩልነት ድርሻ የነፈገ አስተዳደር፡ በኃይልም ቢሆን ተገዶ ከሥልጣን እንዲወርድ መደረጉ ባርነትን ከመዋጋት ተለይቶ የሚታይ አይደለም!

ስለሆነም፡ ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና ሌሎቹም በተመሳሳይ አመለካከት መድረክ በጉባዔው የተገኙትን ሁሉ መጀመሪያ መፈሳቸውን፡ ከአሁኑ ከጥረታቸው በስተጀርባ ያለውን ፍላጎታቸውንና ድርጊታቸውን በጥሞና ሊመረምሩ ይገባል።

አስታራቂ ንፋስ እንደገፋው ዛፍ ያጎበደደ ወይንም የሚያጎበድድ ሳይሆን፣ ያለውን ችግር በጸዳ መመልከት የሚችል መሆን ይጠበቅበታል!
============
 

እምነትና አስተዳደር በምክክር ላይ (ፎቶ ፋና)

እምነትና አስተዳደር በምክክር ላይ (ፎቶ ፋና)

አሁን ላለው የኦሮሚያ ችግርም ሆነ በሌሎቹ የኢትዮጵያ ክፍሎችች እየተባላላ ላለው ችግር መፍትሄው አንድና አንድ ነው! የሕወሃት ፈላጭ ቆራጭነት ተወግዶ ኢትዮጵያውያን በሰላም፡ በነጻነትና በዲሞክራሲያዊ አስተዳደር በእኩልነት ሊኖሩባት የሚችሉባት ሃገር ማድረግ ብቻ ነው!

የሃይማኖት አባቶቹ ጉባዔ በተገባደደ ማግሥት፣ ከጠቅላይ ሚኒስተር ተብየው ጋር “መምከራቸው በየካቲት 25/2016 ዜና ላይ ተዘግቧል። እዚያ ዜና ውስጥም የሚከተለው ይገኘብታል፦

  “ችግሮቹ ሥር ሳይሰዱ እንዲፈቱና በሃገሪቱ የተጀመረው ልማት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሃይማኖት አባቶች ተከታዮቻቸውን እንደሚያስተምሩ ነው የገለፁት። የሃይማኖት መሪዎች በሰላም ግንባታና ሕዝብን በማረጋጋት ሥራዎች ላይ ውጤታማ ተግባር እንዲያከናውኑ ከመንግሥት አካላት በቂ ድጋፍ ሊደረግላቸው እንደሚገባም የበላይ ጠባቂዎቹ ጠይቀዋል።”

ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየውም “የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰላም እሴት ግንባታ ላይ ጠንካራ ተግባር እያከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፥ ይህንኑ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ነው የጠየቁት። መንግሥት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ የሃይማኖት አባቶች በህብረተሰቡ ዘንድ ያላቸውን ተሰሚነት በመጠቀም የማስተማር ሥራውን አጠናክረው [የኃይማኖት አባቶችም] ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።”

ኃይማኖትም ራሷ መሣሪያ ታጥቃ ወደ ማሰተማር ከገባች ከክርስቶስና ከደቀ መዛሙርቱ ምን ያህል እንደ ተስፈነጠረች፡ ይሀ ኃይማኖትና መንግሥት ያደረጉት ምክክር ያረጋግጣል!

ምነው የዚህች ሃገር ችግሯ መባባሱ እንዲህ እንዲቀጥል ብቻ ሆነ ሥልጣን ላይ ያሉት የሚጥሩት?
 
*Updated; title edited.
 

ተዛማጅ ጽሁፎች:

  የሽፍታ/ወንበዴ መንግሥት በኢትዮጵያ

  የኦርቶዶክስ ገቢ በቢሊዮን ቢቆጠርም የምዕመናኑ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን ካድሬው ፓትሪያርክ በተሰበረ ልብ ለሕዝብ ይፋ አደረጉ

  አፍንጫን ሲመቱት ዐይን ያለቅሳል ዐይነት ሆኖባቸው ፓትሪያርኩ የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ አገዱ

  ኦርቶዶክስ ክርስትና በካድሬው ፓትሪያርክ ቅጥረኛነትና ከቤተ መንግሥት በሕወሃት ሲታመስ

  የሕወሃት አገዛዝ ከደህንነቱ፡ ወታደሩ፡ ዳኞችና ፓትርያርኩ ውጭ የቀረ ወዳጅ ይኖረው ይሆን?

  የሕወሃት መለዕክተኞች “ጠብ ያለሽ በዳቦ” ተንኮል: ቤተመንግሥቱን የከበበው መስቀል በሃይማኖት እኩልነት ስም ለእስላሞች መተናከሻ ተደረገ

  ኢትዮጵያ ወደ አደገኛ አግጣጫ እያመራች ነው

 

%d bloggers like this: