ልማት ባንክ ብድር የሚወስዱ “ደንበኞች ስኬታማ እስኪሆኑ የወለድ ምጣኔ ማበረታቻዎችን አልሰጥም አለ”! ገንዘቡም የለም! እንዲጠቀሙ የሚፈለጉት ግለሰቦችና ትሥሥሮች ብቻቸውን በልተዋል! ከእንግዲህ በሌለ ገንዘብ በዝርያ በመጠቃቀም ሕወሃቶችን ማድለቡን ማቆሙ ከሆነ ግልጽ ይደረግ፤ ኢሣይያስ ባህረም ያዘረፈው ሃብት ይመለስ!

14 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) በወጪ ንግድ ላይ ተሰማርተው የውጭ ምንዛሪን ለማምጣትና ከውጭ የሚገባን ምርት ለመተካት ብድር የሚወስዱ ደንበኞቼ ስራቸው ስኬታማ እስኪሆን የወለድ ምጣኔ ማበረታቻዎችን መስጠት አቆማለሁ አለ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ።

ላለፉት አምሰት አመታት መንግስት ከወጪ ንግድ የሚገኝ የውጭ ምንዛሬን ለማሳደግ በአምራች ኢንዱስትሪም ላይ ሆነ በሌሎች ዘርፎች ላይ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ማበረታቻዎችን ሲያደርግ ቢቆይም፥ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ግን ላለፉት አምስት አመታት በተከታታይ እየቀነሰ ነው የመጣው።

በ2003 ዓ.ም በተለያዩ አለም አቀፍ ሁኔታዎች ከወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ ከ4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ከመሆኑ በቀር ለተከታታይ አመታት ገቢው ሲቀንስ ነው የቆየው።

ለአብነት በ2006 ዓ.ም ከወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ 3 ነጥብ 25 ቢሊየን ዶላር ሲሆን፥ ይህ ገቢ በ2007 ከ3 ቢሊየን ዶላር በታች ነው የተመዘገበው።

በዚህኛው በጀት አመት የስድስት ወራት አፈጻጸምም 1 ነጥበ 3 ቢሊየን ዶላር መገኘቱ የተገለፀ ቢሆንም ቁጥሩ ለአመቱ የተያዘው እቅድ መሳካት ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬን የሚፈጥር ነው።

ለዚህ እንደ ምክንያት ሁሌ የሚጠቀሰው የግብርና ምርቶች አለምአቀፍ ዋጋ መውረድ ሲሆን፥ በሀገር ውስጥ እየታየ ላለው የገቢ ማሽቆልቆል ግን ምክንያቶች ከዚህም ይዘላሉ።

የግብርና ምርቶች አለም አቀፍ ዋጋ ቢቀንስም መንግስት ይህን ለማካካስ የአምራች ኢንዱስትሪው የውጭ ምንዛሬ እንዲያመጣ ለማስቻል ባነሰ የሊዝ ዋጋ መሬት ከማቅረብ እና ከቀረጥ ነፃ ማሽን ከማስገባት አንሰቶ በርካታ ማበረታቻዎችን ያደርጋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደግሞ የውጭ ምንዛሬን ለሚያመጡና የውጭ ምንዛሬ ወጪን ለሚያስቀሩ በገበያው ካሉ ንግድ ባንኮች በታች በሆነ ወለድ ብድርን ይሰጣል።

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ባህረ ባለሀብቶች በወጪ ንግድ እንሰማራለን ብለው ከወለድ ማበረታቻ ጋር ብርድ ይወስዱ እንጂ ባሉት መሰረት የማይሄዱበት ሁኔታ መኖሩንና በሀገር ውስጥ ገበያ ላይ የሚያተኩሩትም ጥቂት መሆናቸውን ተናግረዋል።

ብዙ ጊዜ በኢትዮጵያ ያሉ ንግድ ባንኮች እስከ 12 በመቶ በሆነ ወለድ ቢያበድሩም ልማት ባንክ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው እንደ ጨርቃጨርቅና ቆዳ ያሉ ዘርፎች በተለይም በወጪ ንግድ ላይ የሚሰማሩ ከሆነ የወለድ ምጣኔውን እስከ ዘጠኝ በመቶ ባስም ሲል እስከ ስምንት በመቶ ዝቅ ያደርገዋል ።

ይህም አንድ ባለሀብት በዚህ ባንክ ለሚበደረው እያንዳንዱ 1 ሚሊየን ብር ከሌላው የንግድ ባንኮች አንፃር ከ30 እስከ 40 ሺህ ብር በየአመቱ ከወለድ ነጻ ያስገኝለታል ማለት ነው።

ይህ ከሌሎች ማበረታቻዎች ጋር ሲደመር ብዙ ውጤት ማስገኘት ነበረበት ነገር ግን እየታየ ያለው ተቃራኒው ነው ።

በመሆኑም አቶ ኢሳያስ ከአሁን በኋላ ተበዳሪዎች ባሉት ልክ በወጪ ንግድ ላይ የማይሰማሩ ወይም የውጭ ምንዛሬን ማዳናቸው እስካልተረጋገጠ ዝቅ ባለው ስምንት እና ዘጠኝ በመቶ ወለድ ሳይሆን በ12 በመቶ ነው ብድር የሚያገኙት ብለዋል።

ከአሁን በኋላ ባለሀብቶች ፋብሪካ ለማቆም ሲበደሩ መጀመሪያ ብድራቸውን በ12 በመቶ ወለድ እየከፈሉ ይቆያሉ።

ከዚያም በውላቸው መሰረት ከምርታቸው ለውጭ ገበያ እያቀረቡ የውጭ ምንዛሬ የሚያመጡ ከሆነ በጭማሪ ሲከፍሉት የነበረው ሶስት በመቶ ወለድ እንደ ብድር ምላሽ ይወሰድላቸዋል፤ በቃላቸው ካልተገኙ ግን ሲከፍሉ የነበረው ወለድ እንደ ዋና ወለድ ሆኖ ይቀጥላል ነው ያሉት አቶ ኢሳያስ ።

የልማት ባንኩ ይህን አመት ጨምሮ ለሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ 106 ቢሊየን ብርን ለብድር ለማቅረብ ሲያቅድ፥ የግል ባንኮች ከሚፈፅሙት እያንዳንዱ ብድር 27 በመቶ የሚሆነውን ከብሄራዊ ባንክ ቦንድ እንዲገዙ ተደርጎ መሆኑ ተመልክቷል።

ፕሬዚዳንቱ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ለማምረት ከባንኩ ከሚበደሩ ባለሀብቶች ግማሽ የሚሆኑት ቃላቸውን አይጠብቁም፤ ስለሆነም የወለድ ምጣኔ ማበረታቻ የሚደረግላቸው ተበድረው ምርታቸውን ለውጭ ገበያ ካቀረቡ በኋላ ነው ብለዋል።

ባንኩ የነበረው ቁጥጥር እጅጉን አናሳ መሆኑን ተከትሎም በርካታ ባለሀብቶች ላለፉት ጊዜያት ቃላቸውን ሙሉ ለሙሉ ሳይተገብሩ በወለድ ማበረታቻ ሌሎች ንግድ ባንኮች ሊከፍሉ የነበረውን ሚሊየን ብሮችን ሲያተርፉ ቆይተዋል።
 

Related:

  ለመለስ መታስቢያ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከ5 ሄክታር በላይ ፓርክ በጉለሌ ሊያስገነባ ተቋረጠ: ለልማት ብድር ከተያዘ ገንዝብ ላይ – የሕወሃት ወይንስ የመንግሥት ውሳኔ? የባንኩ ግንኙነት ምንድነው?

  በሕወሃት ሰዎች የኢትዮጵያ ሕዝብ በየቀኑ ይብጠለጠላል፣በጥላቻ ዐይን ይታያል፤ በየቀኑም ያስሩታል፣ ይገርፉታል፤ ምሥጋና ቢስ በሆነ መንገድ ይዘርፉታል፤ መለስ ዜናዊ የጀመረው ከባንኮቻችን እየተወሰደ በማይከፈል ገንዘብ ታላቅ የማሽን ፋብሪካ በትግራይ እየተገነባ ነው!

  ሕወሃት የቴፒ ቡና ተክል ልማት ድርጅትን ለታደለ አብርሃ “ግሪን ኮፊ” በብድር ሸጠ: ከለገሬጂና ለገደንቢ አለመማር ወይንስ ጎሣዊ የጥቅም ትስስር?

  ሕወሃት መራሹ ኢሕአዴግ መቀሌ ላይ በወሰደው የፖለቲካ ውሳኔ ምክንያት ሃገራችን አንድ ግዙፍ እርምጃ ወደኋላ ትራመዳለች

  TPLF’s greed for power & resources results in Abobo now belonging to Tigreans & Saudis; Al-Amoudi doles out free tractors; MeTC offers easy tractor ownership with public funds

  FINELINE: Bravo PM for just waking up to MeTEC’s corrupt ways

  Payback time ? Angry residents in Gambella set Indian-owned farm on fire, destroying farm properties

  ANDM, member of the ruling coalition in Ethiopia, begins to produce beer malt in Gondar

  Opening parliament, president tells members regime recognizes Meles’s monetary policy has been wrong and harmful

 

%d bloggers like this: