በእርግጥ ዓሊ ሱሊማንና ኮሚሽኑ ፀረ-ሙስና አቋም አላቸው ወይ፣ ወይንስ ለሕወት ከለላ ሰጭዎች?

18 Mar

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

ሃይማኖተኛ ይመስል ፓትሪያርኩ የሕወሃት መልዕክት ይዘው፡ ኦርሞችን ለመክሰስ ወደ ሮማው ፓፓስ ፍራንሲስ ዘንድ ግንባር የመፍጠር አቤቱታ ይዘው ቀረቡ። ለነገሩ የካድሬው ፓትርያርክ ተል ዕኮ ሳይሳካ መቅረቱ ብቻ ሳይሆን፣ ፓፓ ፍራንሲስ ሃገሪቱ እየተራበች ስለሆነ በምግብና ውሃ አቅርቦት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዕርዳታ እንደምታደርግ ቃል በመግባት የሕውሃት ካድሬውን አባ ማትያስን አሰናበቷቸው።

የሚያስገርመው ነገር፡ የጸረ-ሙስና ኮምሽኑ ዓሊ ሱሊማን ሰሞኑን አንድ ሃሣብ አቅርቧል – ፋና እንደዘገበው። ከመላ ሃገሪቱ ከተወጣጡ የሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች ጋር ሙስና በመከላከል ረገድ ስነ ምግባር ያለው ትውልድ ለማፈራት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ምክክር መካሄዱን ጠቁሟል።

በእኔ እምነት፣ የጸረ-ሙስና ትግሉን ደብዝ ያሳጡት እነዓሊ ሱሊማን ራሳቸው ተልኮዋቸው የሕወሃትን ጥቅም መጠበቅ ስለሆነ፡ የሃገር ዘረፋው አካል ናቸው!

የሃይማኖት ተቋማት በርካታ ተከታዮችን ያቀፉና በማህበረሰቡ ተቀባይነት ያላቸው በመሆኑ ሙስናን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ሚናቸው የጎላ ነው ተብሏል።

በኮሚሽኑ የስነ ምግባር ትምህርትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አሰፋ እንዳሉት፥ የሃይማኖት ተቋማቱ ከምን ጊዜውም በላቀ ደረጃ ለታዳጊዎች የሚሰጡትን ትምህርት ማሳደግ ይገባቸዋል።

የምክክሩ ተሳታፊዎችም በስነ ምግባር የታነፀ ትውልድ ማፍራት ሃይማኖታዊም ሃገራዊ ግዴታችን በመሆኑ ሙስናን የሚጠየፍ ትውልድ ለመቅረፅ እንደሚሰሩ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በስንትና ስንት ቢሊዮን በሚቆጠር ብርና ብዙ የሚከራዩ ቤቶች ሃብት የዳበረች ብትሆንም፡ በዘመነ አባ ማትያስ ም ዕመኑ ገንዘብ ማዋጣቱ ላይ ቆጠብ ማለቱን፡ እንዲሁም ብዙዎቹ ከቤተ ክርስቲያኗ መሸሻቸውን ፓትርያርኩ ለአዲስ አድማስ መግለጻችው ይታወሳል።

ታዲይ ራሷ በሙስና የተበላሸች ቤተ ክርስቲያን እንዴት ነው በሥነ ምግባር የታነፀ ትውልድ ለማፍራት ሃይማኖታዊም ሃገራዊ ግዴታው በመሆኑ ሙስናን የሚጠየፍ ትውልድ በመቅረፅ ረገድ እነ አባ ጳውሎስና ማትያስ ያበላሿት ቤተ ክርስቲያን የዚህ ዐይነት አስተዋጾ የሚኖራት?

በመስጊድም በኩል ያለው ችግር ተመሳሳይ ነው። የራሳችውን የእምነት ወገኖች ያሳሰሩና ያስገረፉ ግለሰቦች በቤተ መስጊድ መሪነት ደህንነቱና ሕወሃት ሲያስቀምጧቸው፡ ስብሃት ነጋና እንኳ በእርሱ ደረጃ ታዝቧቸው የተናገረውን ማስታወሱ ይጠቅማል።

ታዲያ አሁን ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ማጠፊያው ስላጠረው የቀረው አማራጭ፡ እምነትን በማስታወስ የኢትዮጵያን ሕዝብ ዐይኖች ከሕወሃት ዘረፋ ለመሸበብ የሚደረግ ጥረት ንው!

ዓሊ ሱሊማንና ሌሎችም የኮሚሽኑ አባሎች እጆቻቸው የጸዱ ስለመሆናቸው መጠራጠር ተገቢ ነው!
 

ተዛማጅ:

    Vatican Radio: Pope conveys to TPLF patriarch importance of promoting “peaceful coexistence based on reciprocal respect and reconciliation, mutual forgiveness and solidarity”!

    Ethiopian Orthodox Synod warns patriarch to respect rule of law & institution; rejects plaintiff’s pol. decrees, ‘rules’, solicited-travels

%d bloggers like this: