በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ 10 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ

24 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ ሚያዝያ 16/2008 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ ትናንት ምሽት በደረሰ የእሳት አደጋ ግምቱ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት መውደሙን የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ባለሥልጣን አስታወቀ።

ባለሥልጣኑ ለኢዜአ እንዳስታወቀው በአንድ የእንጨት መጋዘንና መሰንጠቂያ ፋብሪካ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ 10 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ሲወድም በሁለት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።

የባለሥልጣኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ካሳሁን ደሳለኝ እንደገለጹት የእሳት አደጋው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ በተለምዶ የካቲት 23 ትምህርት ቤት አካባቢ ከምሽቱ 6 ሰዓት ከሩብ ላይ ነው የተነሳው።

የአደጋ ሠራተኞች ባደረጉት ርብርብ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ከቃጠሎ ማዳን ተችሏል ብለዋል።

አደጋውን ለመቆጣጣር በተደረገው ጥረት 197 ሺህ 600 ሊትር ውኃ ጥቅም ላይ ውላል።

የአደጋው መንስኤ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን ፖለሲ የማጣራት ሥራ እየሰራ መሆኑን ነው ባለሥልጣኑ የገለጸው።
 

%d bloggers like this: