ተጠያቂነት በሌለበት የሕወሃት አስተዳደር በሕወሃት መሃንዲሶች ከቅጠል የሚሠሯቸው ሕንጻዎችና መንገዶች እየተደረመሱ፣ ሕዝብና ንብረት እየፈጁ ነው — አሳፋሪው የቦሌው ሰሚት ሕንጻ ጉዳይ!

27 Apr

የአዘጋጁ አስተያየት፡
 

  ተጠያቂነት በሃገራችን ቢኖር ኖሮ፣ የሕንጻው ሥራ በሚገባ አስካልተጠናቀቀና ለስዎች መኖርያነት በላይስንስድ መሃንዲሶች (licensed engineers) ብቃቱ እስካልተረጋገጠ ድረስ፣ ሕንጻው ለኪራይ ባልዋለ ነበር!

  ከሁሉም የሚገርመው፡ ስለ አደጋ (risk awareness and analysis) በሥራ ባህሪው ምክንያት ጥሩ ግንዛቤ ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቅ ባንክ የመጀመሪያው ተከራይ መሆኑ ነው!ለባንኩ ደንበኞችስ የሚሰጠው ምን ያህል በዕውቅትና ምርምር ላይ ያልተመሠረተ ሃሣብና ምክር መሆኑን መገንዘብ አያዳግትም!

  በዘመነ ሕወሃት ሃገራችን እንዲህ መረን ሆና ሕጻናትና ሌላውም ያልተጠራጠረ ሁሉ እንዲህ በአደጋ ከመኖር ሲገደድ፥ እነደብረጽዮንና ዐባይ ጸሃዬ ስለመልካም አስተዳደር ባለሙያ ሆነው ሲቀላምዱ እስከ መቼ ነው ኢትዮጵያውያን አንገታቸውን ደፍተው የሚያዳምጡት — ልክ አለመሆኑን ቢያውቁም!

  በሃገራችን እኮ ‘ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት፣ ገብቶ ይፈተፍታል’!የሚለው ዛሬ በተደጋጋሚ በሃገራችን ያለማቋርጥ እየታየ ነው!

  እስከ መቼ ነው ሃገራችን ቀጣፊዎች፥ መንግሥታዊ ክብር በማይገባቸው ዘራፊዎችና ነፍሰ ገዳዮች መጫወቻ ስትሆን ኢትዮጵያውያን አንገታቸውን ደፍተው የሚመለከቱት?

============
 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ባለ 5 ፎቅ ህንፃ ተደርምሶ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ።

የአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደገለጹት፥ የህንፃ መደርመስ አደጋው ዛሬ ማለዳ 12 ሰአት ላይ ነው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሰሚት አካባቢ የተከሰተው።

ባለ 5 ፎቅ ህንፃው ሙሉ በሙሉ ያልተጠናቀቀ ቢሆንም ከታችኛው ወለል ላይ ሁለት ባንኮች አገልግሎት መስጠት ጀምረው እንደነበርም አቶ ንጋቱ ጠቁመዋል።

የመደርመስ አደጋው በስራ ሰዓት ቢደርስ በሰው ላይ ከባድ አደጋ ሊያደርስ ይችል እንደነበርም ነው ባለሙያው ያነሱት።

በምሽት የተደረመሰው ባለአምስት ፎቅ ሕንጻ (ከፋና የተወሰደ ምሥል)

በምሽት የተደረመሰው ባለአምስት ፎቅ ሕንጻ (ከፋና የተወሰደ ምሥል)

የባንኮቹ የጥበቃ ሰራተኞች ህንፃው ከመድርመሱ በፊት ከባድ ድምፅ በመስማታቸው ከአደጋው ሊያመልጡ ችለዋል።

በከተማችን ያልተጠናቀቁ ህንፃዎች አገልግሎት በመስጠት ህብረተሰቡን ለአደጋ እያጋለጡ በመሆኑ የህንፃ ባለንብረቶች ከዚህ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡም አቶ ንጋቱ አሳስበዋል።
 

ተዛማጅ:

  በአዲስ አበባ ቡልጋሪያ አካባቢ ለህንፃ ግንባታ የተቆፈረ ጉድጓድ ተደርምሶ በ6 ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ

  በስድስት ወር ውስጥ 41 ሰዎች በመንገድ ጉድጓዶችና ኩሬዎች ውስጥ ገብተው ሞተዋል

  የአንድ ት/ቤት አጥር ተደርምሶ 11 ተማሪዎች ላይ ጉዳት ደረሰ

  በሻሸመኔ ከተማ መጸዳጃ ቤት ላይ የተሠራው ቤተ አምልኮ ተደርምሶ የ10 ሰዎች ሕይውት አለፈ – ሕወሃት መንግሥት መሆን አቅቶት ዘረፋው ላይ ሲያተኩር፥ በሃገሪቱ ስታንዳርድ ጠፍቶ የዜጎች ሕይወት በከንቱ እየተቀጠፈ ነው!

  በዘመናችን ከሚታዩት መንግሥታዊነት ብቃት ማነስ የተከሰቱ የአስተዳደር ጉድለቶችና ለሕይወትና ንብረት ተጠያቂነት አለመኖር ተጠቃሽ መሆን ከሚገባቸው የአዲስ አበባ ምሣሌዎች መካከል

  የፋብሪካዎች ዝቃጭ በአካባቢና በማኀበረሰብ ደህንነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ ነው

  Unregulated elevators pose eminent danger on safety

 

%d bloggers like this: