የሃገር ድንበር የማያስከብረው የሕወሃት ጦር ደቡብ ሱዳን አቋርጦ መግባቱንና የታገቱትን ልጆች ያሉበትን እየተከታተልኩ ነኝ ብሎ (ያላደረገውን) ሲቀባጥር፣ ደቡብ ሱዳን 32ቱን ከ125 ማስለቀቋን ካሳወቀች በኋላ፥ የአንድ አራተኛዎቹን መገኘት ዜና እንኳ መዘገብ አሳፍሮት ሕወሃት ድምጹን አጠፋ!

1 May

በከፍያለው ገብረመድኅን፥ The Ethiopia Observatory (TEO)
 

አሶስየትድ ፕሬስ ቅዳሜ እንደዘገበው ከሆነ፣ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ከ125 ታጋች ኢትዮጵያውያን መካከል 32ቱን ቦማ ውስጥ ማግኘቱን ገልጿል።

የቦማ ግዛት ተጠባባቂ አስተዳዳሪ ኦጋታን ቻን ልጆቹን ሊኳንጎሌ አስተዳደር (Likuangole County) ሥር ባሉ ሶስት መንደሮች ውስጥ ያገኟቸው ያካባቢው ሃገር ሽማግሌዎችና ባህላዊ አስተዳዳሪዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። እነዚህም ከታጋችነት ነጻ የተደረጉት ዜጎች ከስሞኑ ከፒቦር ወደጆባ ተውስደው ወደ ኢትዮጵያ እንደሚላኩ አስተዳዳሪው አስታውቀዋል። ቀሪዎቹን ታጋቾችም እንደ ሚያፈላልጓቸው የሃገር ሽማግሌዎቹ መግለጻቸው ተጠቅሷል።

ስለዚህ ሁኔታ የጋምቤላ አስተዳዳሪ ጋትሉክ ቱት ማንም እንዳልነገራቸው ለአሶስየትድ ፕሬስ ገልጸዋል። የሕወሃት ጦርም ታግች ልጆቹ ያሉበትን ሥፍራ አግኝቸዋለሁ በማለት የሃሰ ዜና በተደጋጋሚ ቢያስተጋባም፣ ለአፍታ እንኳ ኢትዮጵያውያን እመኔታ ሊሠጡት አልፈለጉም!

Credit: GOSS

አሁን አሳሳቢ የሚሆነው፣ የሃገሩን ዳር ድንበር መጠበቅ አቅቶት ባለቤት እንደሌው ቤት፣ የባዕድ ጦር በተደጋጋሚ ድንበር ጥሶ ገብቶ አያሌ ዜጎቻችን ገድለው፡ ሕጻናት አፍነውና ሁለት ሺህ ያህል ከብቶች ነድተው ሲሄዱ ባየር እንኳ መከታተል ያልቻለው በንግድና ዘረፋ ላይ ያተኮረው የሕወሃት ጦር ተመልሶ – ብቸኛ ሙያው ወደ ሆነው – የጋምቤላዎችን ቤት እየፈተሽና እያሸበረ ዜጎችን ማንገላታትና ማሰርና ላይ አተኩሮ ከርሟል። ለወደፊቱስ ሃገሪቱ ምን ዋስትና አላት?

በተለምዶ ይደረግ እንደነበረው ዜጎች እንኳ መሣሪያ ታጥቀው ድንበራችውን እንዳያስከብሩ፡ አብዛኛውን የጋምቤላን መሬት የዘረፉት የሕወሃት አባሎችን ለመጠበቅ ሲባል፡ የአካባቢውን ተወላጆች ትጥቅ አስፈትተው፡ ሕወሃቶችን በማስታጠቃቸው፡ እነርሱ ለሃገሪቱ ደንታ ስለሌላቸው፣ ጠላትና ዘራፊ ገብቶ ግድያ ሲፈጽም ፊታቸውን አዙረዋል!

ታዲያ እንደ ወጣ የቀረውን የሕወሃት ጦርን ለማስመለስ፡ ሕወሃት ሌላ ሠራዊት በመላክ ስም በጀት ሊጠይቅ ይሆን? ከዚህ የከፋ ውርደት ሃገራችንን ያጋጥማታል ብዬ አልገምትም!

የሕወሃት አስተዳደር ጭንቅላቱን ካስተካከለ በኋላ፥ ይህ እንዳያደገም፣

    (ሀ) የዜግነት ስሜት ያለው የሃገር ድንበር የሚያስከብር ጦር በአካባቢው እንደሚመድብ

    (ለ) እስካሁን ለተፈጸመው ውርደት የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዲጠይቅ

    (ሐ) የአካባቢው የጦር ኃላፊዎች ላይ አስፈላጊው ወታደራዊ ቅጣት እንዲፈጸም

    (መ) ጉዳት ለደረሰባቸው ጋምቤላውያን ቤተሰቦች የሕወሃት አስተዳደር አስፈላጊውን ካሣ እንዲከፈላቸው እርምጃ እንደሚወስድ ለኢትዮጵያ ሕዝብ መግለጽ

    (ሠ) ፓርላማው በዚህ ጉዳይ ላይ አስፈላጊውን ውይይት ካደረገ በኋላ፣ ዜጉቹ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ይህንን መፈጸማቸውን በማስገንዘብ፡ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲቀበልና አስፈላጊውን ይቅርታ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲገልጽ፡ ይህንን የፈጸሙትን ለፍርድ እንዲያቀርብ፡ ኅላፊነቱን በመሸከምም አስፈላጊውን ካሣ እንዲከፍል ንግግር እንዲጀመር የሚጠይቅ ውሳኔ ሊያስተላልፍ ይገባል!

ደቡብ ሱዳን በኢትዮጵያ ጋምቤላ ክልል ድንበር ሰብረው በመግባት ንፁሃን ዜጎችን በመግደል ሕፃናትን አግተው የወሰዱ የሙርሌ ታጣቂዎችን ሕግ ፊት ለማቅረብ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ ወታደራዊ ዘመቻ እንደምታካሂድ ማስታወቋ ይታወሳል
 

The story as released by the Associated Press is hereunder:

South Sudan: 32 Kidnapped Ethiopian Children Recovered

Authorities in South Sudan said they have recovered 32 of the 125 Ethiopian children who the Ethiopian government said were abducted from its Gambela region two weeks ago during a deadly cattle raid blamed on a South Sudanese militia.

Ogato Chan, acting governor of South Sudan’s Boma state which borders Gambela, told Associated Press Saturday that local chiefs collected the children from three villages in Likuangole County where the raiders had dropped them off. Chan said the recovered children will be brought to state capital Pibor then sent to Juba to be repatriated to Ethiopia.

“The chiefs are looking for the rest of the children,” he said.

Ethiopia’s government said 208 people died in the April 15 raid and blamed the attack on an ethnic Murle militia from South Sudan.

In Ethiopia, Gambela regional president Gatluak Tut told AP he has not been notified about the recovery of the children.

Deadly cattle raids and abductions of children are common along the border of South Sudan and Ethiopia between the Murle in South Sudan and the Nuer and Anyuak tribes who live in both countries. Children are sometimes kidnapped to look after stolen cows.
 

%d bloggers like this: