ወጣቱ ፖለቲከኛ ዮናታን ተስፋዬ በአሸባሪው የሕወሃት አስተዳደር የሽብርተኝነት ክስ ተመሰረተበት! ለኢትዮጵያዉያን አሳዛኝና አሳፋሪ ዕለት! የሕወሃት ግፍ መች ይሆን የሚያበቃው?

5 May

በከፍያለው ገብረመድኅን፣ The Ethiopia Observatory (TEO)

የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወጣት ዮናታን ተስፋዬ በተለያዩ ድረ-ገጾች ላይ በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ ለእስር ተዳርጎ የነበረው የጻፋቸው ጹሁፎችና አስተያየቶች በማስረጃነት ቀርበውበት የሽብርተኛ ወንጀል ክስ ተመስርቶበታል።

Yonatan Tesfaye protesting against injustice (Credit: Befekadu Z. Hailu)

ሰው በዘሩ ብቻ ሽብርተኛ ተብሎ ሊፈረጅ ይገባልን? Yonatan Tesfaye protesting TPLF injustices committed against the Ethiopian people, including its ‘policy of land grab & suppression of media freedom & free flow of information (Credit: Befekadu Z. Hailu)

በቀረበበትም ክስ ተከሳሹ የማኅበራዊ ድረ-ገጾችን በመጠቀም አመጽና ብጥብጥን የሚያነሳሱ ጽሁፎች አሰራጭቷል እንዲሁም መንግስትን የሚተቹ ጽሁፎች ጽፏል ተብሎ በከሳሽ አቃቢ ህግ ራሱ እንደተመሰረተበት ታውቋል። በዚህም መሠረት፥ የደብዳቤው መክፈቻ ዐረፍተ ነገር ራሱ ዘግናኝና ከእውነት የራቀ በመሆኑ እንዲህ ሲል ይጀምራል፦

    “ተከሣሽ የፖለቲካ፥ የአይዲዮሎጂ ዓላማን ለማራመድ በንግሥት ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ብረተሰቡን ወይንም የኅብረተሰቡን ክፍል ለማስፈራራትና የሃገሪቱን መሠረታዊ፡ ፖለቲካዊ፡ ሕገ መንግሥታዊ፡ ኤኮኖሚያዊ ወይም ማኅበራዊ ተቋማትን ለማናጋትና ለማፈራረስ አስቦ እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ብሎ በሚጠራው አሸባሪ ቡድን በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖችና ወደአዎች ኅብረተሰቡን የአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ልዮ ዞኖች የተቀናጀ ማስተር ፕላን ሽፋን በማድረግ ከኅዳር 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በሚጠቀምበት ድህረ-ገጽ በተለይም በፊስቡክ ተጥቅሞ በሽብር ቡድኑ የተጀመረውን ዓመጽና ብጥብጥ ለማስቀጠል…”በማለት ይዘረዝራል

የክሱን ይዘት ከፍርድ ቤት ደብዳቤው እዚህ በመጫን ይመልከቱ

የኢትዮጵያ ዋነኛው ችግር፡ ስለሕግና ሉዓላዊነት ምንም ዐይነት ግምትና ግንዛቤ የሌለው የሕወሃት አስተዳደር ራሱን ከሕዝቡ በላይ አድርጎ – እንደ ቱርኩ ሬሲፕ ታይብ ኤርዶጋን ሁሉ – አክብሩኝ ብሎ ሚድያውን ሲዘጋና ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞችን ሲያስር መሣቂያ ከመሆኑ ባሻገር፣ የቱርክን ሕዝብ ለሽብር አጋለጠው እንጂ ምንም ያተረፈው ነገር የለም።

በተመሳሳይ መንገድ፣ ኢትዮጵያ ውስጥም አሸባሪው ሕወሃት እንጂ ኢትዮጵያ የአሸባሪዎች ሃገር አይደለችም! ኢትዮጵያ ውስጥ የዘረፋና የሥልጣን ዘመኑን ማራዘም የሚሻው፣ እርሱ ነፍሰ ገዳይ ሆኖ፣ ሰላማዊ ኢትዮጵያውያንን እያሠረና በሕግ የተከለከውን ሠቆቃ የሚፈጽምባቸው የወንበዴው የሕወሃት ቡድን ነው!

አንድ ኢትዮጵያዊ ዜጋ – ዘላለም ወርቅ አገኘሁ – በሕወሃት አላግባብ ታስሮ፡ ተገርፎና ሰብዓዊነቱ ተዋርዶ ሽንቱን እንዲጠጣ እንደተደረገ የሚከተለውን ሲነግራችሁ፡ ጭንቅላታችሁን የሚመታው ምንደነው?

ዮናታንን በግለሰብ አላውቀውም፤ ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጥ በሰማኋቸው ግን ጥሩ የፖለቲካ ሰው ሊሆን እንደሚችል ዕምነት ያሳደረብኝ ሰው ነው። ስለሆነም፡ የሕወሃት ሥራ እንደርሱ ያሉትን ወጣቶች ለማጥፋት የማይፈበርከው ወንጀል አይኖርም አልኲ ለራሴ!

ስለሆነም፥ ረቡዕ ጥዋት የዮናታንን መታሠር እንዳነበብኩ፡ የሽብርተኝነት ክስ በኢትዮጵያ ውስጥ የሃገር አስተዳደር ክስረትና የፖለቲካ ባለሥልጣኖች ክስረት ምልክት አድርጌ ስለምወስድ፥ የሕወሃት ሰዎች ውድቀታቸው እንደታያቸው ስለተሰማኝ፥ የሚከተለውን ነበር ቲዊት ያደረግሁት

    @befeqadu @wdavison10The TPLF at the height of #arrogance of power, signaling it’s approaching demise! #Popular anger is #getting more sensible!

ከዘራፊነቱ ውጭ፡ ሕወሃት ጥሩ የሃገር አስተዳዳሪ ቢሆን ኖሮ፡ ሃገራችን በጋምቤላና በጎንደር ደግሞ በኦሜድላ በኩል በሁለቱ ሱዳኖች ስትደፈር፡ ሕዝባችን ሲገደልና ልጆቻንና እንዲሁም ገበሬዎች እየታፈኑ ተውሰደው ሱዳን ውስጥ የደረሱበት አለመታወቁን ችላ ማለት አልነበረበትም! ይህም የከፋ በሃገር ላይ የተፈጸመ ወንጀል በመሆኑ፡ ሕወሃት በሽብር ፈጻሚነትና አስተባባሪነት ሊጠየቅ እንደሚገባው የሚያሳይ – ለመጀመሪያ ጊዜ ሳይሆን – በተደጋጋሚ የተፈጸመ ሽብርተኛነት መሆኑን ኢትዮጵያውያን ግንባሩን ሊፋረዱትና ሊፋለሙት የሚገባ ነው!

ዛሬ ሃገር ወዳዱ ወጣቱን ዮናታን የቆመበት ላይ ነገ የሕወሃት አሸባሪዎች ጽዋቸውን እንደሚጎናጩ አልጠራጠርም!
 

%d bloggers like this: