የአጋዚ ጦር መከማቸት ሳያግደው በኦሮሚያ ተቃውሞው በተጠናከረ መንገድ እያገረሸ ነው!

20 May

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 


 

በኦሮምያ ህዝባዊው ተቃውሞው አገረሸ

ግንቦት 11 2008 ዓ/ም (ኢሳት ዜና):- ለሳምንታት ጋብ ብሎ የነበረው የኦሮምያ ክልል ተቃውሞ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መጠነኑን እያሰፋ በመምጣት ላይ ሲሆን፣ ዛሬ በምእራብ ሃረርጌ የማሳለ ከተማ ነዋሪዎች ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞ አሰምተዋል። ከሁለት ቀናት በፊት በአሰቦ ከተማ ተመሳሳይ ተቃውሞ የተካሄደ ሲሆን፣ ትናንት ምሽት ደግሞ በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የፈደራል ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ እርምጃ ወስደዋል። በርካታ ተማሪዎችም መጎዳታቸው ታወቋል።

መንግስት የአዲስ አበባ አዲሱን ማስተር ፕላን መተውን በይፋ ካስታወቀ በሁዋላ፣ የአርሶ አደሩን መሬት መልሶ የሚወስድበትን አዲስ እቅድ ይፋ አድርጓል። እቅዱን አርሶ አደሮች አጥብቀው በመቃወም ላይ ናቸው።
 

%d bloggers like this: