‘የመንግስት ቤቶች’ ላይ የሠፈነው ምዝበራ: ‘የዓሣ ግማቱ ካናቱ’ ስለሆነ ነገሩ ‘የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አንተም…’ ነው!

13 Jun

የአዘጋጁ አስተያየት፡

  ዋና ተሿሚዎች እነርሱው፣ ዘራፊዎቹዎ እነርሱው – የሕወሃት ሰዎች – መሬት መዝባሪዎቹ፡ ቤት ሠባሪዎቹ፤ አሁንም አጋላጮቹ እነርሱው! ፋና አልነበር እንዴ በ1997 ምርጫና ከዚያም በኋላ በሕወሃት ወረራ የተዘረፉት መሬቶችን ሕጋዊ ለማስደረግ አልነበር እንዴ በ1997 ምርጫና ከዚያም በኋላ በሕወሃት ወረራ የተዘረፉት መሬቶችን ሕጋዊ ለማስደረግ በካዳስትራል ስም በግንባር ቀደም ዝግጅቱን ሲያስተባብር የነበረው?

  በግንባር ቀደምነት ዝግጅቱን ሲያስተባብር የነበረው – ለምሣሌ ብሩክ ከበደ (የፋና ምክትል ኃላፊ)፣ ይትባረክ መንግሥቴ (ከተማ ልማት)፣ እንዲሁም የስለላ ድርጅቱ (INSA)? ይኸው የኛ ነገር ሆኖ፡ ዛሬ ፋና ብሮድካስትም የመንግሥት ቤቶችን ምዝበራ አጋላጭ ሆኗል!

  መቼ ይሆን ያ ሁነኛው የፋት ቀን የሚመጣውና ኢትዮጵያ የምትገላገለው?

 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት የስራ ሃላፊ በመሆናቸው ምክንያት የመንግስት ቤት ከኪራይ ነጻ ወይም በአንስተኛ ኪራይ ተስጥቷቸው እያለ የራሳቸውን አከራይተው የሚኖሩ ግለሰቦች እንዳሉ በስፋት ይነገራል።

ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ካሁን ቀደም በዚህ ጉዳይ ላይ ትዝብታቸውን እንዲያጋሩ ተጠይቀው ይህንኑ በአንደበታቸው አረጋግጠዋል።

ለአብነት በአንድ መስሪያ ቤት ውስጥ ፀሃፊ ሆና የምትሰራ አንዲት ግለሰብ በፅሃፊነት ዘመኗ የተፈራረቁ ሶስት ሹመኞች ኑሯቸው በመንግስት የኪራይ ቤቶች ቢሆንም ሶስቱም በየወሩ ብዙ ሺህ ብር ኪራይ የሚቀበሉበት የራሳቸው መኖሪያ እንዳላቸው መስክራለች።

በአዲስ አበባና በድሬድዋ ከተማ 11 ሺህ የግል መኖሪያ ቤቶችን የሚያስተዳደረው የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ በህግ ወጥነት የተያዙ ቤቶችን ማስለቀቅ ባለመቻሉ ዘንድሮ በአዲስ መንግስት ምስረታ ለተሾሙ ከ100 በላይ ሹመኞች ቤት ማቅረብ አልቻለም።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃብታሙ ሲሳይ ከፍላጎቱ ጋር ሲነፃፀር የቤት አቅራቦቱ ክፍተት እንዳለበትና ዘንድሮ እስከ ግንቦት ወር ድረስ ከ144 የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የቤት ጥያቄ ቢቀርብም ይህን ማሟላት አለመቻሉን ተናግረዋል።

ምን አልባት ቀድመው ቤት የያዙ ሃላፊዎች ስላለቀቁት፣ የራሳቸው ቤት ያላቸውም ቢሆኑ የተከራዩትን የመንግስት ቤት ርስት ስላደረጉት አዳዲሶቹ የስራ ሃላፊዎች ቤት ማግኘት ሲሳናቸው ተስተውሏል።

ችግሩን የበለጠ አሳሳቢ የሚያደርገው የአዳዲሶቹ ተሿሚዎች ቤት ማጣት ሳይሆን፥ ቤት ላልተገኘላቸው ከ100 በላይ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ነነብስወከፍ በወር በትንሹ 5 ሺህ ብር ለኪራይ ቢከፈል ፤ በአመት ከስድስት ሚሊየን ብር በላይ ከህዝብና ከመንግስት ካዝና ወጪ ይደረጋል ማለት ነው።

በህግ ወጥ መንገድ የተያዙ የመንግስት ቤቶች ቢለቀቁ ግን ይህን ያህል ገንዘብ ማውጣት ባላስፈለገ ነበር።

አቶ ሃብታሙ ይህን ችግር ለማቃለል በቅርብ ጊዜያት ወስጥ ሳይገባቸው የመንግስት ቤቶችን ይዘው የተቀመጡ 156 ግለሰቦች ቤት እንዲለቁ ሲደረግ፥ 14 የድርጅት ቤቶችንም ለማስለቀቅ እንደተቻለ ተናግረዋል።

በመንግስት ቤቶች ላይ የሚታየው ከቤቶች አስተዳደር የህዝብና የመንግስት ንብረት ሆኖ ሳለ የግለሰቦች መጠቃቀሚያ እስከመሆን የደረሰውን ችግር ለመቅረፍ ግን እርምጃ መውሰድ ብቻ በቂ አይደለም።

ይልቁንስ ኤጀንሲው ቤቶቹንና ነዋሪዎቹን መንጥሮ ለመለየት የሚያስችል ስርዓት ቢዘረጋ የተሻለ ነው የሚል ሃሳብ ይደመጣል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ አቶ ሃብታሙ ይህንን ለማድረግ የሚያስችል በኮምፒውተር የታገዘ የቤቶች አስተዳደር ስልት በቅርቡ ስራ እንደሚጀምርና 11 ሺህ ቤቶችም ወደ መረጃ ቋት እንዲገቡ መደረጉን አንስተዋል።

40 አመታትን ያስቆጠረው የቀድሞው የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት የአሁኑ የመንግስት ኪራይ ቤቶች ኤጀንሲ በቤት እድሳት ላይም ብዙ ክፍተት ሲነሳበት ይሰማል።

ይሁንና ዋና ዳይሬክተሩ ከሌላው ጊዜ በተሻለ ባለፉት ሰባት ወራት ብቻ ከ1 ሺህ 100 በላይ ቤቶች መታደሳቸውን ይናገራሉ።

በድምሩ 20 ሺህ ቤቶች የነበሩት ኤጀንሲው ዛሬ ላይ የድርጅትን ጨምሮ በስሩ ያሉት ቤቶች 17 ሺህ ደርሰዋል።

በቀጣይም አዳዲስ ቤቶችን ለመገንባትም ቦታም ሆነ የፋይናንስ አቅም መኖሩን ነው አቶ ሃብታሙ ያስረዱት።

የመንግስት ንብረት ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ ለግል መጠቀሚያነት ሲውል የፍትሃዊነት ጥያቄን ያስነሳልና ኤጀንሲው የመንግስት ኪራይ ቤቶችን ህዝብን ለሚያገለግሉ እንጂ በህዝብ ስም ቤቱን በግል ለሚገለገሉ እንዳይሰጥ ጥንቃቄ ይደረግ የሚለውም የህዝብ ድምፅ ነው።
 

ተዛማጅ:

  በምርጫ ማግሥት: ሕገወጥ መሬት ባለይዞታዎች ሕጋዊ ካርታ ተሰጣቸው – የሕወሃት ሰዎች ከ97 ጀምሮ በሕገ ወጥነት፥ ተንኮልና ነጠቃ የያዟቸውን እንደሚጨምር ታውቋል፤ እሪ በይ ኢትዮጵያ!

  በምርጫ ማግሥት: ሕገወጥ መሬት ባለይዞታዎች ሕጋዊ ካርታ ተሰጣቸው – የሕወሃት ሰዎች ከ97 ጀምሮ በሕገ ወጥነት፥ ተንኮልና ነጠቃ የያዟቸውን እንደሚጨምር ታውቋል፤ እሪ በይ ኢትዮጵያ!

  በዕጦቶችና የሥልጣን ብልግና የተፈጠረው የኢትዮጵያ ምሬቶች የዛሬው ሥዕልና የነገው ሥጋት*

  መንግሥታዊ አስተዳደር በሃገራችን አለመኖር! በአዲስ አበባ የኦዲት ችግር ተስተውሎባቸው እንዲያስተካክሉ ከተነገራቸው 125 መስሪያ ቤቶች ምላሽ የሰጡት 9 ብቻ መሆናቸው ተነገረ!

 

%d bloggers like this: