ተራ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በየሥፍራው የሚገደለው፣ በሃገረ ሶማሊያ የሚሞቱት የኢትዮጵያ ወታደሮችም ክብርና ቀባሪ አጥተው ሬሣቸው በረሃ ላይ እየረገፈ ነው፤ አሁን ደግሞ ገዳዮቹ ላይ አልሞ ገዳዮቹን በተከታታይ መልቀም ተጀምሯል! ማን ይሆን እያነጣጠረ የሕወሃትን ሰላዮች የሚለቅማቸው?

17 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

እነማን ይሆኑ? ማን ይሆን? የሃገር ደህንነት ሳይሆኑ፥ የሕወሃት ሰላዮች ላይ እያነጣጠረ ላለፉት አራት ወራት ሲለቅማቸው የከረመው/ሙት? እኛም ለጥይቄው መልሱን አናውቅም። ምን ውጤት እንደሚያስከትል አናውቅም – ለውጥ መምጣቱን ባንጠራጠርም!

አንድ አበክረን የምናውቀው ሃቅ ግን፥ በሕወሃት አስተዳደር ኢትዮጵያ ውስጥ በዜጎች እኩልነት ላይ ያልተመሠረተ አመራር ባለበት ሁኔታ፡ ሃገሪቷ ልማቷም አርኪ ሰላምና ደህንነቷ የተረጋገጠ ይሆናል ብሎ ማሰብ ቀድሞውንም ተላላነት ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለማን ደህንነት ነው ይህቺን የጋራ ሃገራችንን መንከባከብ የሚገባው? ለዘረኛው ሕወሃትና አቃጣሪዎቹ?

ከታሪክ እንደምናስታውስው፥ ባሪያ ለፈንጋዩ የራሱን ደህነንትና ነጻነት ወደጎን ገፍቶ፡ ቀንና ሌሊት ለፈንጋዩ ምቾትና ደህነንት ብቻ ሲኳትን ዘላለም ይኖራል ብሎ እንደማሰብ የሚቆጠር ነው! አይታሰብም!ከሁሉም የከፋ ደግሞ፥ ወያኔዎች ኢትዮጵያዊ ለከትና ምን ይሉኛል የሌላቸው የቀን ጅቦች ናቸው፤ በዞን ዘጠኝ ሴቶች እህቶቻችን ላይ የፈጸሙትና ማናችን ነን የምንዘነጋው። በኦሮሞ ተቃውሞ እንደተጀመረ ሕዝቡን ለማሳቀቅ በቅድሚያ ሴቶችና የ12 አና የ13 ዓመት ልጆች ነው የጨፈጭፉት! ነፍሰጡሯን ነው ጫክ ውስጥ ደፈረው ጉድጓድ ቆፍረው ቀብረው የሄዱት – በኋላ በሐኪም ምስክርነት እንደተሰጠበት…

ስንቱ ክፋታቸው በመላ ሃገሪቷ የፈጸሙት የእነዚህ የሽድሽተ ዜሮ ሰዎች ግፍ ተዘርዝሮ ይቻላል? እስቲ የሕወሃት ሰዎች የሃገር መሪዎች ሆነው (ድንቄም አመራር)፥ ሱፍ ለብሰው ስታዩዋችው፡ ቪላ ውስጥ እየኖሩ፡ መርሰዴስና ቢ.ኤም. ደብልዩ… ይዘው ምናቸው ነው የትላንትናም የዛሬም አሠቃዮች (torturers) የሚመስለው?

ዛሬ ጎልቶ ለኢትዮጵያውያን የወጣው አሳፋሪ ክፋታቸው፡ ዘራፊነታቸው፣ ሃሰተኛነታችው… ብልሹ ድርጊታቸው ብቻ ነው!

የኢትዮጵያ ሕዝብ በኤርትራ ተወረርን ተብሎ ከሃምሳ ሺህ በላይ ሕይወቱን ሰጥቷል! እነርሱ በነፍሱ ያዳናቸውን ጦር የኤርትራን መሸነፍ ሲያይ በተኑት ያለጡረታ መብት … ሃገራችንን እያንዳንዳችንን እንደዜጎች አዋረዱን!
ይህ የሚታሰብ ባለመሆኑ ነው አሁን ይህ ጥፋት በሕወሃት ሰዎች ላይ ያንዣበበው!

ዛሬም ሆነ ነገ፣ መረሳት የሌለበት አንድ ሃቅ አለ? የኢትዮጵያን ሕዝብ ሕወሃቶች ናቁት።

እርሱም እነርሱ እንዳደረጉት፡ በቀሉን ለማግኘት በአሁኑ የፈተናቸው ሰዓት ጽዋችሁን ተጋቷትብሏቸዋል፤ ከእንግዲህ ወያኔዎችን በሚረዳ መንገድ አይተባበራቸውም። የሃገር ደህንነትና ልማት የሚሠምረው እኮ ሕዝብ ተባባሪና ተሳታፊ ሲሆን ነው።

ሃገሪቷ ደህነቷ ሊረጋገጥ የሚችለው፡ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እኩል ሲሆኑና በሃገሪቷ ደህነንትና ብልጽግና ውስጥ ድርሻ አለን ብለው ሲያምኑ ብቻ ነው!

የፖሊሲና የአመራሩን ነገር ወደ ጎን አንተወው — አንድ ምሳሌ እንጥቀስና፤

ሕወሃቶች በከሠረ አስተሳሰባቸው የዕድገት መሠረትና ምስክር አድርገው የሚወስዱት ትላልቅ ኮርፖሬሽኖችን እንጂ በኅብረተሰብ ደረጃ መካከለኛው መደብ የሚወጣባችውን ኢንተርፕራይዞች ስላልሆነ፡ ሃገሪቱ ጠብ የማይልላት ለዚህ ነው።

አርብ ወደማምሻው ገደማ ከዚሁ ጋር በተያያዘ አንድ ዜና በጣም አስገርሞን ነበር።

ባለሁለት አሃዝ የኤኮኖሚ ዕድገት አላት ብሎ ሕወሃት በየቀኑ በሚያናፋላት ኢትዮጵያ ውስጥ፥ በአዲስ አበባ ከተማ የጥቃቅንና አነስተኛ የኢንተርፕራይዞች የመጀመሪያው ምዕራፍ ቆጠራ ከዓመት በጥቂት ወራት በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ 3,884 ኢንተርፕራይዞች ውድም ብለዋል – ድርቅ እንደመታው ሰብል።

ከሁሉም የሚገርመው፡ ከዚሀ በተጨማሪ ቆጠራው ያጋለጠው፡ “የ1,599 ኢንተርፕራይዞችን አባላትና ባለቤት ማግኘት” አለመቻሉን ነው። እነዚህ መናፍስት የሆኑት (ghosts) ቢዝነስ ባለቤቶች፣ መጀመሪያ ፈቃዶቻቸውን እንዴት አወጡ? ግብርስ እንዴት ከፈሉ? የአገልግሎት ክፍያዎችስ? የቤት አከራዮቹስ ምን አሉ? የቢዝነሶቻቸው ደንበኞችስ ምን አሉ…?

ለእነዚህም ጥያቄዎች መልስ አይኖረነም! እነርሱ ግን ምን እንደሆነና እነማን እንደሆኑ እርስ በእርስ ይተዋወቃሉ!

በሕወሃቶች የተሞላው የስለላ ድርጅቱ፡ ቁልፍ የመንግሥት አስተዳደሩ፤ የውጭ ምንዛሪ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ውጭ በሻንጣ የሚልኩትና የሚያስልኩት እነርሱው ናቸው። ዋና ዋናዎች ባለሥልጣኖች ተባባሪዎች ናቸው – በሚስቶቻቸውና ልጆቻቸው ጭምር!

የአራቱን ወራት በሰላዮች ላይ የተቃጣውን ዒላማ በተመለከተ – የሕወሃት ይሁን የባዕድ ጥቃት ከሆነ ዋና ዋናዎቹን መልቀሙ – ጥቃቱ የተጀመረው ኢትዮጵያውያን ለወራዳ ወያኔ ከሃዲዎች በር የከፈቱ ዕለት ስለሆነ፡ ምናልባትም ሁሉም ዜጋ እነርሱን አሰቀድሞ ጽዋውን መጠጣት ይኖርበታል – የተሻለ ትውልድ የተሻለች ሃገር እንዲረከብ!
 

ተዛማጅ:

  የተለያዩ የጸጥታ ሃይሎችን ሙሉ መረጃዎች የሚያሳዩ ሰነዶች ኢሳት ውስጥ ገቡ

  ‘የመንግስት ቤቶች’ ላይ የሠፈነው ምዝበራ: ‘የዓሣ ግማቱ ካናቱ’ ስለሆነ ነገሩ ‘የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አንተም…’ ነው!

  In TPLF-run Ethiopia, Oromo athletes complain about ethnic discrimination – Audio transcript

 

One Response to “ተራ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በየሥፍራው የሚገደለው፣ በሃገረ ሶማሊያ የሚሞቱት የኢትዮጵያ ወታደሮችም ክብርና ቀባሪ አጥተው ሬሣቸው በረሃ ላይ እየረገፈ ነው፤ አሁን ደግሞ ገዳዮቹ ላይ አልሞ ገዳዮቹን በተከታታይ መልቀም ተጀምሯል! ማን ይሆን እያነጣጠረ የሕወሃትን ሰላዮች የሚለቅማቸው?”

 1. ashu-ka June 20, 2016 at 11:35 #

  i’m live in this country and i’m safe more than anything now…..but people like want to put us again in a mess….just to recover ur bullshit fathers dynasty…full of autocratic and dictatorship…whose killed people for nothing….so…don’t waste ur time and do sth. valuable thus, we might forgive you for what you think….b/c you born for this pls. re-born yourself again…………………………..believe me you need this!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

  Like

Comments are closed.

%d bloggers like this: