ለሕግ ባላቸው ታማኝነት ታዋቂ የሆኑ ዳኛ ግዛቸው ምትኩ ከሃገር ሸሽተው መሰደዳቸው ታወቀ! ከሃኪሞች ቀጥሎ ኢትዮጵያ ለዓለም በስደተኛ ዳኞች አበርካችነት ልትታወቅ ይሆን? ዳኛውስ ለምን ወጡ? አዳምጧቸው!

17 Jul

Editor’s Note:

    Ethiopian judge runs away for his life from minority dictatorial regime of TPLF in Ethiopia!

 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 


 

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከዳኝነት ስራቸው የተሰናበቱት ዳኛ ግዛቸው ምትኩ ከሀገር ወጡ። የአቶ መላኩ ፈንታን ጨምሮ የጉምሩክ ባለስጣናትን የክስ ሂደት ከሚመሩት ዳኞች አንዱ የሆኑት ዳኛ ግዛቸው ሕገ መንግስቱ እንዲሻሻል ጠይቀዋል፡ የብሄረሰቦች መብት አልተከበረም ብለዋል፡ የሚሉና ሌሎች ክሶች ቀርበውባቸው ነው ምክር ቤቱ ከስራ ያሰናበታቸው።

በሌላ በኩል በ2006 ዓ.ም. ክረምት ወራት በፓርላማ አዳራሽ በተደረገ ሥልጠና፣ በተለይ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የወንጀል ፍርድ ቤት ፈራሚ አባል ያልሆነችው የኢትዮጵያ የመንግሥት አመራሮች የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስለሚፈጽሙ መሆኑን፣ በ1997 ዓ.ም. ከምርጫ ጋር ተያይዞ በተደረገው አመፅ የአንድ ብሔር ጥቅም ለማስከበር ብዙ ሰዎች መገደላቸውንና መንግሥትም ሊጠየቅበት ሲገባ አለመጠየቁን ሲገልጹ ነበር የሚል ክስም ቀርቦባቸዋል፡፡

ዳኛ ግዛቸው ለሕይወታቸው አስጊ ሁኔታዎች በመፈጠራቸው ከሀገር ወጥተዋል።
/ኢሣት
 

%d bloggers like this: