ሕወሃት ኢትዮጵያውያንን የባብኤል መንደብ አድርጎ፣ ከተለያዩ ብሄረሰቦች ግለሰቦችን በጸጥታ ኅይሉ አካቶ እንዴት ከፋፍሎ እንደሚያጨፋጭፍ ከሟቾች ኮማንዶቹ ስም ዝርዝር ይመልከቱ!

19 Jul

በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)
 

e73419f2df118c8e86a369c577fef3d7_L

በሰሜን ጎንደር እና አካባቢው በተፈጠረው ሁከት ህይዎታቸው ያለፈ የፀጥታ ሃይል አባላት 

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 12 ፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ጎንደር እና አካባቢው የተፈጸመውን ህገ ወጥ ድርጊት ሁሉም ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች አውግዘዋል።

ክልሎቹ በድርጊቱ ንጹሃን ዜጎችና በጸጥታ ሃይል አባላት ላይ በደረሰው የህይወትና የአካል ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘንም ገልጸዋል።

በአካባቢው ባለፈው ሳምንት የተፈጠረውን ሁከት ተከትሎ የፀጥታ ሃይል አባላት ወደ ስፍራው በመንቀሳቀስ ደርጊቱን ለማስቆም ጥረት አድርገዋል።

በዚህ አጋጣሚ በተፈጠረ ሁከትም 11 የፀጥታ ሃይሎች ህይዎታቸው አልፏል።

Fallen-Hero-B
 

በግጭቱ ካለፉት የፀጥታ ሃይሎች መካከል 9 የፌደራል ፖሊስ አባላት፣

1 የመከላከያ ሰራዊት አባል እና 1 የአማራ ክልል ፖሊስ አባል ለህልፈት ተዳርገዋል።

የእነዚህ ሃይሎች ስም ዝርዝር ከዚህ በታች የሚከተለው ነው።

1. ኮማንደር ሃለፎም አዳነ እንደሻው (ፀለምት – ጎንደር)

2. ሳጂን አለሙ መላኩ እንኳንሆነ (ደባርቅ – ሰሜን ጎንደር)

3. ኮንስታብል ኤቢሳ ኢታና አብዲ (ቄለም ወለጋ)

4. ሳጂን ናስሮ ምሹሮ እስማኤል (ደባርቅ – ሰሜን ጎንደር)

5. ረዳት ኢንስፔክተር አህመድ ሁሴን አህመድ (ስልጤ – ደቡብ ክልል)

6. ምክትል ሳጂን አብዲሳ አለሙ ዳሮምሳ (ም/ሸዋ)

7. ምክትል ሳጂን አትሎግ አሰፋ አበራ (ታች ጋይንት – ደቡብ ጎንደር)

8. ረዳት ኢንስፔክተር አደም አብዱላሂ ማኦ (ሊበን – ሶማሌ ክልል)

9. ምክትል ሳጂን ብርሃኑ ሱሊቶ አበሜ (ሃድያ – ደቡብ ክልል)

ይህ በተፈጠረው ግጭት ህይዎታቸው ያለፈ የፌደራል ፖሊስ አባላት ስም ዝርዝር ሲሆን፥ ህይዎታቸው ያለፉ ዜጎችን ዝርዝርም እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።

%d bloggers like this: