በኦሮሚያ ሕዝባዊ ትግል የራስን መብት በማስከበር፣ በሰንዳፋ በአንድ ቢሊዮን ብር የተገነባው ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጥቅም ላይ እንዳይውል ሕዝቡ ከለከለ! አዲዮስ አዲስ አበባ ማስተር ፕላን እነበሪሁን ተወልደ መድኅን እስካልነገሡ ድረስ!

20 Jul

በከፍያለው ገብረመድኅን፣ The Ethiopia Observatory (TEO)
 

በሕወሃት አስተዳደር ጋጠ ወጥነት፣ የሥልጣን ብልግናና ማን አለብኝነት ያላግባብ ሰንዳፋ የባከነው የሃገር ሃብት የሚያሳዝን ቢሆንም፡ የኦሮሚያ ሕዝብ የመሬት ዘራፊው የሕወሃት ቆሻሻ መጣያ ላለመሆን የወሰደውን እርምጃ ቆራጥነትን ከልብ እንደግፋለን!

ዛሬ ትምህርት የሚማርና የሚገባው አስተዳደር በኢትዮጵያ ካለ፣ በኦሮሚያና በጎንደር እየጋሙ ያሉት ሕዝባዊ ተቃውሞዎች የሚያሳዩት ነገር ቢኖር፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ከእንግዲህ ሕወሃት ለምቾቱ ሲል የፈለገውን የሚያደርግበት ዘመን ማክተሙን ነው!

እጅግ የሚያሳዝነው ግን በትናትናው ዕለት ያነበብነው ዜና የሚያሳየው በቅርቡ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆኖ የተሾመው በሪሁን ተወልደመድህን የጀመረውን የሰላም አደፍርስ አሻጥር በቅርብ መገምገም ያስፍልጋል። ግለሰቡ በሕወሃት አባልነቱ ብቻ የተሾመ በመሆኑ፡ አጠቃላይ የሕግ መርህ ላይ ብቻ በመንጠልጠል፡ ስለ ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ተከሰው በሚመጣው ሣምንት ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ለአለቆቹ ሃሣብ ማቅረቡ፣ እንደመለስ ዜናዊ ሁሉ ኢትዮጵያን ወደጥፋት ጎዳና የሚገፋ ነው!

በሕገ መንግግስቱ አንቀጽ 74 -77፣ 81፡ 93፣ 101-103 ከተሠጡት ሥልጣኖች ባሻገር፣ ዲክቴተሩ መለሰ ዜናዊ በተኮልና ደባ የራሱን ሥልጣን ከሕግ ውጭ በማድለቡ፡፣ በሂደት ፓርቲና መንግሥታዊ መዋቅሮች እንድዋሃዱ በማድረግ፣ በሃገራችን የሕግ አውጭውና የሕግ ተርጓሚው ክፍሎችና አስፈጻሚዎችም በተግባር አንድ ሆነው ኢትዮጵያ አንድ ፓርቲ (ሕወሃት) ብቻ የሚገዛት፡ ሕግ የማይከበርባት ሃገር ማድረጉ ማንም አይስተውም! አሁንም የእርሱ ግርፎች ይህንኑ ሥራ በሠፌው ተያይዘውታል።

የዳኝነት ካባ ተከናንቦ በሪሁን ተወልደመድኅንም ተመሳሳይ ተግባር እየፈጸመ ነው – ትግራይ በነበረበትም ወቅት ይህንኑ ሥራ ሲያስፈጽም እንደነበር ከዚያ የመጡ መረጃዎች ያሳያሉ! አሁንም ቀጣዩ ተልዕኮው በታላቋ ትግራይ ስም የወልቃይት ኮሚቴ አባሎችንንና ደጋፊዎችን በማጥፋት፡ እነዚህ የሆድ ፖለቲከኞች ራሳቸውን በሥልጣን ለዘላለም ለመትከል እየሞከሩ ናቸው።

ይህ ብዙ ደም የሚያፋስስ መሆኑ አያጥራጥርም። ኦሮሚያም አገርሽቶበት እንቅስቃሴው እየተቀጣጠለ ነው። የሕወሃት ነፍሰ ገዳዮችም ፡ በዘር ማጥፋት ለፍርድ እስኪቀርቡ፡ ከሁሉም ወገን ብዙ አላስፈላጊ የሆነ ደም ይፈሳል፤ ንብረትም ይወድማል!

ለነገሩ ከእንግሊዝ ኢንተሊጀንስ ጋር የተያያዘው Jane’s IHS (Country Risk Daily Reporter)ከሰሞትኑ እንደተነበየው፣ በጎንደር የታየው ሕዝባዊ ተቃውሞ ተጀመረ እንጂ ሕወሃት እስካለ ድረስ፡ የመሬት ዘረፋውና የመብት ረገጣው በአንድ በኩል በሌላ በኩል ደግሞ የብሔረ ሰባዊነት ስሜት እንዲጋጋም በመደረጉ ኢትዮጵያ በአደገኛ አቅጣጫ እያመራች መሆኗን በሚገባ ማጤን እንደሚገባ ምልከታውን መጠቆም አይዘነጋም!በአሁኑ ወቅት የእርሱ ዋናው የቤት ሥራ አባይ ወልዱ የኢትዮጵያ መሪ የሆነ ይመስል፡ ትግራይም የኢትዮጵያ አስተዳዳሪ – በመንግሥት ወጭ – የትግራይ ሚሊሺያዎቹን ጎንደር አሠርጎ በማስገባት የሕወሃትን የመሬት፣ ግለሰባዊና ማኅበረሰባዊ ማንነትን ዘረፋ የሚቃወሙትን ለመምታት ያደረገውን የማዕከላዊ መንግሥት ሥራ ለማሰመሰል በዳኝነት ስም የተኮፈሰው ካድሬው ግለሰብ ይህንን በመጎንጎን ላይ ይገኛል!

የችግራችን ምንጭ ሕወሃት፡ መለስ ዜናዊና የራስ ጥቅም ያሠከራቸው ቡችሎቻቸው ናቸው። ከእንግዲህ ኢትዮጵያ ልትፈወስ የምትችለው፡ በኦሮሚያና በጎንደር በተካሄዱት ሕዝባዊ ትግሎች ዐይነት በመሆኑ፣ አሁን ያለው ስታተስኮ – የቢሊዮን ብር የፈሰሰበትን የሠንዳፋን ቆሻሻ መጣያ ጨምሮ – ለወራሪና ሕዝብን አላከብርም ላለ የወንበዴ አስተዳደር መልሱ ኃይል ብቻ ነው!
 

ተዛማጅ:

የሕዝባዊ ትግል ውጤት፡ በሰንዳፋ በአንድ ቢሊዮን ብር በተገነባው ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ መጠቀም ተከለከለ!
 

%d bloggers like this: