በጎንደር የወደሙት ትግራዊ ንብረቶች “በወልቃይት የማንነት ጥያቄ ላይ እንቅፋት የፈጠሩ ናቸው … አንዳንዶቹ ለገዢው ፓርቲ የሚሰልሉ ናቸው ”: ወደመብን ካሉ ግለሰቦች ጋር የተካሄደ ቃለ-ምልልስ

20 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ
 

ባለፈው ሳምንት በጎንደር ከተማ በተቀሰቀው ቀውስና ብጥብጥ በርካታ የንግድ ድርጅቶች መውደማቸውን መንግስትና የከተማው ነዋሪዎች ገለጹ።

 


 
ዋሽንግተን — በርካታ ሆቴሎችን ጨምሮ ትክክለኛ መጠኑ ለጊዜው ያልታወቀ ንብረት እንደወደመና እንደተዘረፈ ንብረታችን ወደመብን ያሉ ግለሰቦች ይናገራሉ።

አቶ ተስፋይ በላይ የተባሉ የባህረ-ሰላም ሆቴል ባለቤት ሆቴላቸው መውደሙንና በውስጡ የነበረው ንብረት መዘረፉን የመኖሪያ ቤታቸውም በተመሳሳይ በኃይል ተሰብሮ ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ መዘርፉን ይናገራሉ። የቤተሰባቸውን አባላት የሚያሳርፉበት መጠለያ ማጣታቸውን አመልክተዋል።

ወ/ሮ ሸዊት አባዲ የተባሉ በሶስት ፈረቃ 115 ሰራተኞችን ቀጥሮ ይሰራ የነበረ ሆቴል ባለቤት በበኩላቸው የሆቴል ቤታቸው መስተዋት መሰባበሩንና በንብረት ላይም ላይ ጉዳት መድረሱን ይናገራሉ።

በሌላ በኩል በቅርቡ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ያነጋግራቸው “የወልቃይት የአማራ የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ ዋና ፀሃፊ አቶ አደራጀው ዋኜ በጎንደር ከተማ ንብረታቸው የወደመባቸው የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውንና በወልቃይት የማንነት ጥያቄ ላይ እንቅፋት የፈጠሩ ናቸው” ማለታቸው ተዘግቧል። ብለዋል።

“ንብረት እንደወደመባቸው ካስታወቁ ወገኖች የአሜሪካ ድምጽ ያነጋገራቸው ሁለቱ ግን “ፈጽሞ” ሲሉ ያስተባብላሉ።

የአሜሪካ ድምፅ ወደ ጎንደር እና ሁማራ ስልክ በመደወል ወ/ሮ ሸዊትን እና አቶ ተስፋዬን አነጋግሯል።ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
 

ተዛማጅ:

    Breaking News Gondar I: Sad & Emerging Picture of Today’s & Tomorrow’s Ethiopia Along TPLF’s Path of Destruction!

    ጎንደር ውስጥ ተኩስ እየተሰማ ነው! የሕወሃት ኮማንዶች ከመቀሌ ጎንደር በመምጣት ኮለኔል ዘውዱ ያሉበትን እሥር ቤት በመክበባቸው፡ የጎንደር ሕዝብ አትወስዱትም በማለት እንደገና በቁጣ ለመጋፈጥ ወጣ! ለስምም ቢሆን የአማራን መንግሥትነት ባይረግጡትስ! ምናለበት እነርሱ ሕግ አለመሆናቸውን አውቀው ሕዝቡን ባይፈታተኑት!

    TPLF’s arrogance of power pays it with further ethnic crisis in Gondar, confirms Jane’s IHS – renowned Country Risk Daily Reporter

 

%d bloggers like this: