ከጎንደር ሕወሃት በዘረፈው መሬት ምክንያት በኢትዮጵያ የጦርነትን ማገዶ ማቀጣጠል የሚሻው አውሮፓ ነኝ የሚለው የትግራይ ማኅበር ጸረ-ኢትዮጵያዊነት

23 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ተቀማጭነቴ በአውሮፓ ነው የሚለው የትግራውያን ማኅበር በአውሮፓ (Union of Tigreans in Europe፣ Amsterdam, Netherlands)፣ ሐምሌ 15/2016 በተበተነ መግለጫ፡ “በቅርቡ በጎንደር ከተማና አካባቢዋ በተከሰተው አውዳሚ ሁከት አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ” በሚል ርዕስ፣ ይህ ማኅበር ትግራይንና ትግሬዎችን ተበዳይ፣ የጎንደርን ሕዝብ በዳይ አድርጎ አቅርቧል።

የመግለጫውንም ይዘት ኢትዮጵያውያን እንዲያመለከቱትና አስፈላጊውን ግንዛቤ እንዲወስዱ፥ የዚሁ ባለሁለት ገጽ ሊንክ እዚህ ስለተቀመጠ፡ ለማንበብ አንድ እና ሁለትን ይጫኑ።

ሕወሃት ሲያካሄድ በኖረው ፊውዳላዊ ወታደራዊ የግዛት ማስፋፋት (feudal military expansionism) ሥራና አፈና መሬቱ ተቆርሶ የተወሰደበት የጎንደር ሕዝብ አቤቱታውን ሰሚ አጥቶ እነ ዐባይ ወልዱ በማን አለብኝነት፣ የክልሉን መንግሥት ስምምነት ወይንም ትብብር እንኳ ሳይጠቁ ወራሪ አፋኝ ሚሊሺያዎች ልከው የወልቃይትን ጥያቄ የሚነሱትን ሰዎች አፍነው ወደ ትግራይ ለመውሰድ መመኮራቸው ይታወሳል።

ትግራይና ጎንደር የፌደራል መንግሥቱ አካልና የሃገሪቱ አጎራባች ክልላዊ መንግሥታት ሆነው ሳለ፣ የመቀሌ አስተዳደር የአማራን ክልላዊ መንግሥት ዕርዳታ/ትብብር/ዕውቅና ሳይጠይቅ – ሌላ ስም ስለሌው – ከውንብድና ውጭ በሌላ መልኩ ሊተረጎም የማይችል – የመቀሌ አስተዳደር በጎንደር ሕዝብ ላይ ውንብድና ፈጽሟል።

በሕወሃት ሊቀመንበር የሚመራው የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ለምን የዚህ ዐይነት የውንብድና ሥራ ውስጥ መግባት እንደፈለገ፡ እንኳን ለተራው ዜጋ ሥነ መንግሥትንና ሕግን ጠንቅቀው ለሚያውቁ ምሁራን ግንዛቤም የፖለቲካው ከርዳዳነትና ኋላ ቀርነትን በውሉ መለየት ቀላል ሊሆን አልቻለም።
አስገራሚው ነገር፣ ይህ አውሮፓ ሠፋሪ ነኝ የሚለው የትግራይ ማኅበር ከአውሮፓ ያሰማው አቤቱታ፡ ዐባይ ወልዱ ከላከው ሕገ ወጥ ወራሪ የኮማንዶ ኃይል የበለጠ አቁሳይ ሆኖአል። የሚከተለው የውንጀላ ስሞታቸውን በጽሁፍ ያቀረቡት ግለሰቦች ስለጉዳዩ ከስሜትና ቆዳ ጠለቅ ትግራዊ ብሄርተኝነ ውጭ ተገቢው ግንዛቤ እንደሌላቸው፡ ወይንም የተጀመረው የኃይል እርምጃ ደጋፊ መሆናቸውን ለማሳወቅ ከመሆን ውጭ፡ የሚታየው ግንፈላና ያቀረቧቸው የውሳኔ ሃሣቦችም ቅዠት ወይን ከገራፊ ጩኸት ያልተለየ መሆኑን ለመመልከት፣የሚከተለውን ጥቅስ የመልከቱ፦

“ሰው አክባሪ፣ ኩሩና ታጋሽ የትግራይ ህዝብ ለዓመታት ሲጠነሰስ የቆየ ጥላቻ በቅርቡ በጎንደርና አካባቢዋ በሕይወቱና ንብረቱ አሳፋሪና አሳዛኝ የሆነ ከባድ የጥፋት ድርጊት ለመለከት በቅተናል” ይላል።

(Credit: Ethiopian Review)

(Credit: Ethiopian Review)

ሕወሃት የአማራን መሬቶች ማለትም ከጎንደርና ከወሎ፣ ኢትዮጵያን ለዘለቄታው በበላይነት እገዛለሁ ብሎ አሁም በልቡም ሆነ በጠብመንጃው የሚያስብ ከሆነ ተሳስቷል!

በብሔራዊና ዓለም አቀፍ ሕግጋት ለዘመናት ተቀባይነት ያለውን ራስን የመከላከል መብት በመጠቀም፡ የጎንደር ሕዝብ ራሱን ከወራሪ በመከላከል ሞክሮ፡ የረካበትን እርምጃ ወስዷል። አሁን ይህ የፖለቲካና የግጭት ሁኔታ ከቁጥጥር እንዳይወጣ የተፈጸመውን ስህተተኛ የሕወሃትን ድርጊት አውግዞ ከማረም ይልቅ፡ የአማራ መንግሥት ላይ ቅጣት እንዲጣል መገፋፋቱ ስህተተኛ አካሄድ ነው። የጎንደር ሕዝብ የአማራ መንግሥት በስሙ ቅጣቱን እንዳይቀበል ቢወስን፣ አውሮፓ ነዋሪዎቹ ወይንም የኢትዮጵያን የጦር አውሮፕላኖች መቀሌ ያሰባሰበው ሕወሃት አማራን በታንክና አሮፕላን ሊደበድብ ነውን? ወይንስ፣ አንብቶ የማያባራ ምድራዊ ወረራ በትግራይና በሱዳን በኩል ለማካሄድ ይሆን? በነገራችን ላይ ሲቪል ሕዝብን በጦር ኃይል ማስደብደብ በዓለም አቀፍ ወንጀለኛ ያስደርጋል!

ሌላውስ ቢቀር፡ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህንን የትዕቢት እርምጃ ተኝቶ ይመለክታል የሚል አስተሳሰብ ካለ፡ በሃገሪቱ ውስጥ መተላለቅን እንደመጋበዝ ነው የሚቆጠረው!

መፍትሄው መሬት ነጣቂው፡ የዘረፈውን መሬት መመለስ ነው። የወልቃይትንም ማንነት በተመለከተ በግድ ዝርያህ ትግራዊ ነው መባሉ፡ የሕወሃትን ድርጊት በመካከለኛው ምሥራቅ በእስልምና ስም ግለስቦችን በግድ እያጠመቀ ‘ከዛሬ ጀምሮ እስላም ካልሆናችሁ’ እያለ ዓለምን እያሸበረ ካለው ISIS ድርጊት ተለይቶ የሚታይ አይደለም!

የአብዬን ለእምዬ እንደሚባለው፣ የትግራይ ማኅበር በአውሮፓ ነገሩን ለማብራራት የሠጠው የታሪክ ምሣሌ የሕወሃትን የጎንደር መሬት ዘረፋ ምን ሊሉት እንዳሰቡ፡ ከቅጥፍነቱ ባሻገር ስለምን እንደሚተረኩ ለመገንዘብ ስለሚያስቸግር ሁሉም በየፊናው በኢትዮጵያ ላይ መጭውን እንዲገነዘብ በሙሉ እንደሚከተለው እንጠቅሰዋለን፦

“የአሁኑ ዘመን ለኢትዮጵያ ዘመነ ህዳሴ፡ ልማት እንጂ ዘመን ጽንፈት፡ እንደዘመነ መሣፍንት ብሄር ላይ ያነጣጠረ ኋላቀር አስተሳሰብ ዘመን አይደለም። በመሆኑም ኢትዮጵያንና ክልሎች እያሰተዳደሩ ያሉ መንግሥታት ውስጣቸው ያሉእ መንግሥታት ውስጣችውን እንዲፈትሹና አስፈላጊ እርምጃ እንዲወስዱ አበክረን እንጠይቃለን!”

የአማራ መንግሥት ካሣ እንዲከፈል ጥያቄያቸውን ካቀረቡ በኋላ፡ የፈዴራል መንግሥት (ሕወሃት) በትግራይ ዜጎች ላይ ምንም አደጋ እንዳይደርስ “ዋስትናና ጥበቃ እንዲሰጥ በአጽንዖት እንጠይቃለን” ይላል።

በእኛ ግምት ይህ በአውሮፓ ነዋሪ የሆኑ የትግራውያን ማኅበር – እንዲህ የሚባል ነገርም ካለ – በገሃድ ራሱ ሕወሃት የሚይምንበትንና እያደረገው ያለውን በኢትዮጵውያን መካከል ፍትሃዊ አስተዳደርና እኩልነት እንዳይኖር የጀመረውን ሥራ ይበልጥ ለማድራት የታሰበ ደባ ይመስለናል!

በነገራችን ላይ አውሮፓ ብዙ የኖሩ ትግራውያን እንዲህ የሚባል ማኅበር ስለመኖሩ በፊስ ቡክ ላይ ጥያቄ ያቀረቡ መኖራቸውን መገንዘብም ያስፈልጋል! ሌሎችንም ማስቆጣቱ ልብ እንዲባል እንመክራለን! ጉልበተኛነትና ጦርነት (የባዕድም ሆነ የብሄርተኝነት) እነኢራክን፣ ሶማልያን፣ ሊቢያንና ሲሪያን ወዘተ ሲያፈርስ እንጂ – ደንፊዎች እንደሚያስቡት – በተለይ በ20ኛውና በ21ኛው ክፍለ ዘመን ማንንም ሲገነባ አላየንም!

ከሁሉ የሚከፋው ደግሞ በብሄር ላይ የተመሠረተው ሕወሃት ሃገራችን ውስጥ የተከለው የዘረኝነት ከኮብራ የከፋ መርዘኛነት ነው!
 

%d bloggers like this: