የጎንደር ሕብረት ልዩ መግለጫ:                      የፍርሃት ከፈን በጎንደር ተቀደደ፤ የጎሕ ብርሃን በኢትዮጵያ ፈነጠቀ!

3 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
የጎንደር ሕብረት ልዩ መግለጫ፣ ሐምሌ 26፣ 2008
 

በቅድሚያ የአምባ ገነኖችን ፉከራ ደፍሮ፤ ከፊት ለፊቱ የተደገነውን መሳሪያ ተረማምዶ፤ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ላዉለበለበዉ ጀግናዉ የጎንደር ህዝብ ያለንን አድናቆት በደስታ እና በከፍተኛ ክብር ልንገልጽ እንወዳለን። የትግራይ ነፃ አዉጭ ግንባር በማስፈራራት ለዘመናት ቀፍድዶ የያዘውን የፍህራት ጨለማ ዘመነ ሐምሌ 24 ቀን 2008 ዓ/ም በጎንደር ህዝባዊ ሃይል ተገፈፈ። ትግራይ ላይ ተወልዶ፤ የሕዝብ ደምን በከንቱ እያፈሰሰ፤ ጎንደር ላይ አድጎ፤ ምኒልክ ቤተ መንግሥት የገባው የወያኔን ሥራዓት የዉድቀት፤ ግባ ከመሬቱ ጎንደር ላይ ተቆፍሮ፤ ሊቀበር የአንድ ጀምበር ያክል ጊዜ ቀርቶታል። ወያኔ ቀበርኩት ያለው አንድነታችን፤ በዳግማዊ ቴውድሮሶች፤ ዛሬም እንደገና ሁለተኛውን ምእራፍ በጥንታዊት ጎንደር ከተማ ላይ መፃፍ ጀምሯል። ከህዝቡ አብራክ የወጣው መደበኛ ሰራዊት፤ ፖሊስና ልዩ ሃይል፤ ህዝባዊ ሚሊሻ የህዝቡ ደስታ ተካፋይ መሆኑን፤ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ሥንታዘብ ደግሞ፤ የአገራችን ኢትዮጵያ ታሪካዊ ክብር ቀጣይነትና፤ የነ ስብሐት ነጋ “እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” ከንቱ ቅዠት መሆኑን እና ለዉጥ የተጠማዉ የህዝብ አንድነት አስተማማኝ ደረጃ መድረሱን ስናረጋግጥ ደስታችን መጠን የለዉም። ትግሉ ያለማቋረጥ ይቀጥላል። “የነብርን ጅራት አይዙም፤ ከያዙም አይለቁም” እንዲሉ ከዚህ በኋላ፤ ለዚህ ዘረኛ እና ቂመኛ ቡድን ጊዜ መስጠት እጅግ አደጋ ነዉ።

በመሆኑም፤ የወያኔው ቡድን በተፈጥሮው፤ እውነትን መቀበል የማይችል፤ ከራሱ ጥቅም በቀር ለኢትዮጵያችን የሚያስብ ቡድን ሥላልሆነ፤ ሁሉም የትዮጵያ ህዝብ የጎንደር ወንድም /እህቱን የትግል ቆራጥነት ፈለግ ተከትሎ ሳይዉል ሳያድር፤ በመላ አገራችን፤ ከዋና ከተማ እስከ ወረዳ እና ቀበሌ ድረስ በአን ድምጽ ለህዝባዊ ትይንት በመዉጣት ከመለዮ ለባሹ ጋር ተባብሮ ይህን ዘረኛ መንግስት ለደቂቃ ያህል ፋታ ሳይሰጥ፤ የጥፋት እጆቹን በመቁረጥ፤ አዲሱን ዓመታችን፤ ሁሉም ዜጋ በነፃነቱ፤ ኮርቶ እና ተከባብሮ የሚኖርባትን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንድንመሰርት፤ ጥሪያችን እናስተላልፋለን። ከአሁን በፊት በተግባር፤ እንዳየነው፤ የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር ጊዜ ለመግዛት የእርቀሰላም ጨዋታ ሊጠይቅ ይችላል። ብዙ ድርጅቶችንም በመድረክ ወጥታችሁ አረጋጉ፤ ካሃናትንም ይህን ጨዋ ህዝብ አስታርቁን፤ ገዝቱልን ማለቱ አይቀርም። የኢትዮጵያ ህዝብ የተማመነበት አንድ ሃቅ ግን አለ። ያም! ወያኔ ሰላም የሌለዉ፤ ሊጠገን የማይችል፤ የበሰበሰ የሳር ጎጆ መሆኑን ብቻ ነዉ። ይህን ቂመኛ ቡድን አምኖ የሚደራደር ሁሉ፤ በአንገቱ ላይ ገመድ እንደማስገባት የሚያስቆጥር ሲሆን፤ ለማደራደር፤ የሚሞክሩ ደግሞ ኢትዮጵያዊነታቸውንም ሆነ፤ ኢትዮጵያችን ቆፍረው እንደቀበሩ ይቆጠራል። የወያኔ ሥርዓት የህዝብ አመኔታ አቶ ያከተመ ዘረኛ ስርዓት ነዉ። በየአካባቢ ተደራጅተህ ጀግና መሪህን መርጠህ ኢትዮጵያዊነትህን እና ታሪካዊ ፍቅር ያለህ ህዝብ መሆንህን አሳይተሃል እና ማንም ዓላማህን ወደኋላ እንዳይጎትት በቆራጥ ጀግንነትህ አረጋግጥ።

በጎንደር አደባባይ ያውለበለብከውን፤ የኢትዮጵያዊነት ምልከት የሆነዉ ሰንደቅ ዓለማንን በሌሎች ሁሉም የኢትዮጵያ አደባብዮች፤ አዉለብልብ። ወያኔን አስወግደን ህዝባችን መክሮ ያመነበት መንግስት በእርግጠኛነት ይቋቋማል። በመቶ የሚቆጠሩ ድርጅቶች ባንዲራ አንግቦ “እኛን ተከተሉን መሪያችሁ ነን” ማለት ለ82 ነገዶች ለተዋበችው ብርቅየ ኢትዮጵያችን ምንም አይነት ፋይዳ የለዉም። መላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተባብሮ እጅና ጓንት ሁኖ ሳይዉል ሳያድር የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባርን ስርዓት ለማስወገድ በቆራጥነት የጎንደር ህዝብን ተጋድሎ አጋዥ መሆን ችላ የማይባል የትግል ጥሪ ነዉ። በዚህ የነጻነት ትግል መሃከል ለስልጣንና የግል ጥቅማቸውን ለማራመድ የሚስበደበዱ ሁሉ፤ የትግሉ አጋር አይደሉም እና በመንገድህ ላይ ደንቃራ እንቅፋት እንዳይሆኑህ፤ እየጠራርክ፤ ወደ ድል አጥቢያህ ገሥግሥ።

በሌላ በኩል፤ የትግራይ ተወላጆች፤ በወያኔ ግዳጅም ይሁን፤ ነገርን አርቆ ካለማዬት፤ ከእውነት በራቀ ድርቅና፤ የወልቃይት መሬት የኛ ነው በሚል፤ የምታደርጉት ሰላማዊ ሰልፍ እና ወያኔያዊ ድጋፍ፤ አገራችንን ወደ ባሰ ቀውስ የሚከት ከመሆኑም በላይ፤ በመላ አገሪቱ ኮራ እና ዘና ብለው፤ ሰርተው ለሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች፤ ችግር እየፈጠራችሁ መሆኑ ተገንዝባችሁ፤ በአስቸኳይ፤ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን እንድትቆሙ፤ ልናሳስብ እንወዳለን።

አስቸኳይ አገራዊ ጥሪ፦

አገር ውስጥ ያላችሁም ይሁን፤ ውጭ አገር ያላችሁ፤ ለአገራችሁ አንድነት፤ ለሕዝባችሁ መብት የቆማችሁ፤ የፖለቲካ ድርጅቶች፤ የስባዊ መብት ተከራካሪ ብዙሃን ድርጅቶች፤ የሃይማኖት እና የሙያ ተቋማት፤ ለአገር ተቆርቋሪ የሆናችሁ ሁሉ፤ ያላችሁን ጥቃቅን ልዩነቶች ወደ ጎን ትታችሁ፤ ኢትዮጵያችን ካለችበት ተረክበን፤ በተረጋጋ ሁኔታ እንድናስቀጥል፤ በፍጥነት፤ ወያኔን ሊተካ የሚችል፤ ብሄራዊ እርቅን መሰረት ያደረገ የሽግግር መንግሥት እንድታቋቁሙ፤ በኢትዮጵያ አምላክ እንማፀናለን።

በመጨረሻም፤ እ. ኢ. አ በ07/24/2016 ዓ.ም በጎንደር ከተማ በተደረገው፤ ሰላማዊ ሰልፍ፤ እናቶች ለተሰላፊው ውሃ በማቅረብ፤ መለዮ ለባሹ፤ ከአብራኩ ለወጣው ህዝብ ያሳየውን ክብር፤ ተሰላፊው፤ ያሳየውን ጨዋነት እና አገራዊ ፍቅር፤ ያነገባቸው መፈክሮች እና የተሸከመው ዓላማ ፍጹም ኢትዮጵያዊነት፤ ከመሆኑም በላይ፤ ወያኔን ከትግራይ ወገኖቻችን ለይቶ ማየቱን፤ እያደነቅን፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ሊከተለው የሚገባ ቀጣይ ፈለግ መሆኑን ልናሳሥብ እንወዳለን።
 
የዘረኛው ሥራዓት በሕዝባዊ ኃይል ይደመሰሳል!
የኢትዮጵያ አንድነት እንደገና ይገነባል!!
ጎንደር ሕብረት

%d bloggers like this: