የደርግ ታሪክ ጃንሆይ ባሉት መልኩ ፍጻሜው ታየ፤ ሕወሃትም ጣር ላይ ሆኖ በሚፈጽማቸው ወንጀሎች (የጦር ጭምር) የሙት ጉዞው እየተፋጠነ ነው!

11 Aug

በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)
 
እንደ ሌሎቹ ሃገሮች ታድለን ቢሆን ኖሮ የአንድም ሕይወት መጥፋት እጅግ መሪር ሆኖ፥ ብዙ በተሰማን ነበር፣ እንኳን ይህን ያህል ዜጎቻችን በግፍ ተጨፍጭፈው።

የዚህ ዐይነቱ ሁኔታ፥ ማለትም ለሰው ሕይወት ከበሬታ በጠፋበት ሁኔታ ውስጥ፡ ይኸው ሃገራችን ውስጥ በተለይ በኦሮምያና አማራ ክልሎች በወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለው ጭካኔ የተሞላው የሕዝብ ጭፍጨፋ አደገኛ ደረጃ ከመድረሱም በላይ፥ ከሕግ አንጻርም ወደ አደገኛ ደረጃ የጦር ወንጀልነት የመሸጋገር ምልክትም በብዙ አካባቢዎች አሳይቷል። በሶሻል ሚዲያም ጥቆማው ተካሂዷል።

ይህ የሕወሃቶች አረመኔያዊ የዝሕብ ጭፍጨፋ (ቪደዮው ላይ የዱላ ቅጥቀጣና እርግጫ ቢሆንም፡ ያ ሁሉ ቅጥቀጣ ለጊዘው ባይገድልም ከእሥር የሚፈቱ ሰዎች ላይ እንደሚታየው ከሆነ ለዘለቄታ የሚቆይ ጉዳት አለው)፤ ጥሩነቱ የነገሩ ሶሻል ሚዲያዎች መቀረጽና መደበኛ ሚዲያውም ከወትሮው ውጭ በትዝብት መተቸቱ ጠቀሜታ አለው (excessive use of force)። በዚህ ዐይነት መልክ ከተመለከቱት መካከል ዋሽንግቶን ፖስትና ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ፣ ሃፍ ፖስት ወዘተ ይገኙበታል።

ምንም እንኳ የውጭ መንግሥታት ቀልበው ያደለቡት የሕወሃት አስተዳደር ይህንን ሁሉ ወንጀል እነርሱን ተገን አድርጎ ሲፈጽም ድምጻቸው ቢጠፋም – አንድ ሁለት ግኝቶችን አሳይቷል። አንደኛው የኢትዮጵያውያን ቈርጠኝነት ከወትሮው ለየት ባለ ሁኔታ ግንባሬን ለጥይት ያለ ይመስላል። ሁለት፣ ይህ ቈርጠኝነትም – እንደታየውና በሕዝባዊ መነሳሳቱ ጭምር – ሌላውም የኅብረተሰብ አካላት ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ በመጠኑም ቢሆን ገፋፊ ሆኖአል። ይህም የሚያረጋገጠው – ገና ብዙ መሥዋዕትነት የሚጠይቅ ቢሆንም – ይህ ለሕወሃት አስተዳደር የውድቀቱ ወሳኙ ምዕራፍ መሆኑን ነው።

ሕወሃት ኃላፊነት የሚሰማው ኃይል ቢሆን ኖር፡ ይህ ችግር የተፈጠረው በአመራሬ ደካማነት፡ ብቃት ማነስና ሃሣቤና እጄም ያልጠራ፡ ኃይል ላይ ብቻ መተማመኔ ልክ አልነበረም ብሉ ትክክለኛ የኅብረተሰቡን ፍላጎት ተቀብያለሁ ማለት ነበረበት! ደግነቱ ሕዝቡ በኦሮሚያም ሆነ በአማራ የባለጋራውን ማንነት ሰለሚያውቅ፥ የሚተካኝን አካል አስመርጬ ዞር እላለሁ እንዲል አይጠብቀውም! ስለሆነም ኢትዮጵያውያን ለአደገኛ ጊዜ ራሳቸውን ማዘጋጀት ይኖርባቸዋል!

Credit: Eduardo Byrono

Credit: Eduardo Byrono


 

የኢትዮጵያ ሁኔታ አነገላዋዊነት

በሰው ዘር ላይ ወንጀል የመፈጸም ይዘት ስላለው፡ የአሁኑ የኢትዮጵያ ሁኔታ በብዙ አካባቢዎችም ግራ መግባትን ፈጥሯል – – ኒው ዮርክ የተባብሩት መንግሥታት ጽሕፈት ቤት ጭምር፡።

ነሐሴ 6 እና 7 ቅዳሜና እሁድ ኢትዮጵያ በሕወሃት ትዕዛዝ በብዙ አካባቢዎች ኢትዮጵያ ብዙ ልጆቿ ላይ ምን እየተፈጸመ እንደሆነ ጥያቄዎች ተነስተዋል። ለምሳሌም ያህል በተባበሩት መንግሥታት ጽሕፈት ቤት በምሣ ሰዓት አካባቢ ለጋዜጠኞች የዋና ጸሐፊው ቃል አቀባይ በዚህ ላይ ሳይዘጋጅ ቀርቦ እንዴት ሰዎች እንዲህ በግፍ በጉልበተኛ ሲጨፈጨፉ ዋና ጸሐፊው አንዳችም አስተያየት አልሠነዘሩም ተብሎ ንትርክ ተነስቶ ውል የሌለው ልውውጥ መካሄዱን ላይ ካለው ቪዲዮ መመልከት ይቻላል (ወደ መጨረሻው)።

ሆኖም ቃል አቀባዩ ምንም የሚለው ነገር ስላልነበረው፣ አንዱን አንስቶ ሌላውን ሲጥል፡ በመሃል ላይ ሌላ ጋዜጠኛ ጉዳዮን ወደ ሲሪያ ጥያቄ ሲያዞር የዕለቱ ገላጭ የነበረው ምክትል ቃል አቀባዩ Farhan Haq በልቡ ተመስገን ማለቱ ያንን ጥያቄ በእንጥልጥል ትቶ ወደ ሲሪያው ርዕስ ሂዶ የቀረበት ሁኔታ ይመስክር ነበር።

ነገር ግን፥ ወዲያው ሰኞ ማምሻውን ነሐሴ 9/2016 UN DISPATCH በሚል የዜናዎች ቋት ውስጥ ብዛታችው ከፍተኛ የሆነ ኢትዮጵያውያን በገዥው አስተዳደር ወታደሮች ተጨፈጨፉ የሚል መልዕክት ይዞ 97 ሰዎች መገደላቸድውን A MASSACRE IN ETHIOPIAበሚል አሰቷል። ይህ የተባለው ወንጀል በኢትዮጵያውያን ላይ መፈጸሙ በተባበሩት መንግሥታት ተቀባይነት አግኝቶ፣ በUNDISPATCH – በድርጅቱ በታተመ ገጽ ላይ የሠፈረው ጽሁፍ ውስጥ (አምኔስቲ ኢንተርናሽናል ያዘጋጀው ሆኖ) የሚከተለው ይገኝበታል፦

የውንጀላው ይዘትም የሚከተለው ነወ፦

“At least 97 people were killed and hundreds more injured when Ethiopian security forces fired live bullets at peaceful protesters across Oromia region and in parts of Amhara over the weekend, according to credible sources who spoke to Amnesty International.

Thousands of protesters turned out in Oromia and Amhara calling for political reform, justice and the rule of law. The worst bloodshed – which may amount to extrajudicial killings – took place in the northern city of Bahir Dar where at least 30 people were killed in one day.

“The security forces’ response was heavy-handed, but unsurprising. Ethiopian forces have systematically used excessive force in their mistaken attempts to silence dissenting voices,” said Michelle Kagari, Amnesty International’s Deputy Regional Director for East Africa, the Horn and the Great Lakes.

“These crimes must be promptly, impartially and effectively investigated and all those suspected of criminal responsibility must be brought to justice in fair trials before ordinary civilian courts without recourse to death penalty.

Information obtained by Amnesty International shows that police fired live bullets at protesters in Bahir Dar on 7 August, killing at least 30. Live fire was also used in Gondar on 6 August, claiming at least seven lives.”

ዋናው ጥያቄ እንዴት አንድ መንግሥት ሕዝቡን ሰላማዊ ሠልፍ አደርጋችሁ ብሎ ወንድ ሴት አዋቂ ሕጻናት ሳይለይ በቀጥታ ግንባር ግንባራቸውን በጥይት የመጨፍጨፍ መብት እንዴት ይኖረዋል የሚለው በተነሱት ጥያቄዎች ስሜት ላይ ተንጸባርቋል።

ይህም ተቀጣጥሎ የሕወሃት የሕዝብ ጭፍጨፋ አሳስቦናል በማለት ረቡዕ ዕለት የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽነር Zeid Ra’ad Al Hussein ግድያው ዘግናኝ በመሆኑ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎችና መርማሪዎች በተለይም ምሬት ባለባቸው ክልሎች ሁኔታው ምን እንደሚመስል ምርመራና ግምገማቸውን እንዲያካሄዱ ሕወሃት እንዲስማማ ጥሪ አድርገዋል። እስከዚያ ድረስ ግን ተቃውሞ በማድረጋቸው ብቻ የታሠሩት ግለሰቦች “በአስቸኳይ እንዲፈቱ” ጠይቀዋል።

በዚሁ ዓምድ ነሐሴ 17/2016 “Is Ethiopia about to crack?” በተሰኘው ጽሁፌ እንዳመለከትኩት፣ የድርጅቱ የሰብ ዓዊ መብቶች ዋናው ኮሚሽነር አል ሁሴን በትምህርታቸው የሕግ ሰውና ወታደር እንደመሆናቸው፡ ዛሬም ሆነ ክዚያ በፊት የተፈጸሙት ሰላማዊ ሠልፈኞች ላይ የመተኮስ ተግባር ግልጽ ዓለም አቀፍ ወንጀል መሆኑን ነው፡ ያለማመንታት ድምጻቸውን ለማሰማት የተገደዱት።

በተጨማሪም፡ እንደተለመድው የፕሬስ መግለጫ ወረቀት በትነው ዝም ሊሉ ይችሉ ነበር። ሁኔታው ግን ክዚያ የከፋ በመሆኑ፥ ራሳቸውን በዚያ ከመወሰን ይልቅ የሮይተርስን ጋዜጠኛ ጠርተው አመለካከታቸውን ማካፈላቸው – ዜናው በፍጥነት እንዲሠራጭና አሜሪካም ሆነች ሌሎች የምዕራብ ሃገሮች ከግብጽ የታህሪር አደባባይ ሰመመናቸው አሸናፊውን ወገን ተመልክተው ሲገለበጡ፡ የተመድ ባልሥልጣን ያንን ጠንካራ አቋም በግልጽ መያዝ ከሰመመኑ ሲወጡ መደመንደርደሪያ እንደሚሆናቸው ስሌት ያለበት እንደሆነ ገምታለሁ።

ከጌታቸው ረዳ ካኽሳይ በፊት – የተገለጸው አይጋ ፎረም በሚያስተባብራችው አባላት በኩል UNHCHR አንባብያን አይግረማችሁና፡ በአይጋ ፎረም አማክይነት የሕወሃት አባላት መንግሥታቸው ከተባበሩት መንግሥታት ጋር እንዳይተባበር የሚል ነው የመጀመሪያው የሕወሃቶች ተቃውሞ። ይህም መጀመሪያ የተገለጽውነበር።

ነገርን ነገር ያነሳዋልና፥ ቅዳሜ ዕለት ነሐሴ 6/2016 ኦሮሚያ ውስጥ ያ ሁሉ ሕዝብ ሲጨፈጨፍ፡ የሕወሃት መኳንንት፡ ምሁራኖቻቸው ጭምር፡ ለማቾቹ ኃዘን ሊሰማቸርው ቀርቶ፡ ይህ ሁኒታ ሃገራችንን ወደ ጥፋት ጎዳና መውሰስዱ እንኳ ምንም አልተሰማቸውም።

Credit: Aigaforum

Credit: Aigaforum

ሕወሃታውያን ትግሬዎች በዋሽንግቶን ዲ.ሲ.ማሪዮት ዎርድማን ፓርክ ሆቴል ዓመታዊ ፈንጠዝያቸው ላይ ነበሩ። አዎ ለሣቅም ለደስታም፥ ለሃዘንም ጊዜ ሊሠጠው ይገባል። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ግን የሚፈነጥዙት የተወሰኑ፡ የሚያነቡት ደግሞ አብዛኛው ሕዝብ መሆኑ ኅብረተሰባችን ምን ያህል በቁሙ እየሞተ መሆኑን የሚያመለክት ነው።

ይህ ምን ማለት ነው? በኢትዮጵያውያን አመለካከት፡ ወንጀል ፈጽሜ ሉዓላዊነት ስም ከተ.መ.ድ. ጋር አልተባበርም ማለት አይቻልም – ዓለም አቀፍ ሕግ አለና። ከሁሉም የከፋ ግን ይህችን በባዕዳን ምጽዋት የምትደዳር ሃገር ይጎዳታል። እነስሜን ኮሪያ ወይንም ሳዑዲ አረቢያ እንተባበርም ቢሉ ከኢትዮጵያ የተሻለ አንጀት መደገፊያና ውሳጥዊ ትብብር አላቸው። ሕወሃት ግን ምን ላይና ማን ላይ ተማምኖ ነው እንደዚህ ያለ ዕርምጃ የሚወስደው?

ከምርጫው በኋላ አሁን አይገርመኝም! ከሁሉም የከፋና አይሆንም ስንል ኢትዮጵያ የጸጥታው ምክር ቤት አባል ሆናለች። ይህ እኮ ኃላፊነቷን ለመወጣት አለመቻሏን በማመልከት ምክር ቤቱን ለወቀሳና መሳለቂያነት አሳልፎ ይሰጠዋል። ድርጅቱንም ዓለም አቀፍ ግዴታውን ለመወጣት፡ ኢትዮጵያ ሸክም ትሆንበታለች በማለት ነበር – በተለይም አፍሪካ ውስጥ ባሉት ኃላፊነቶቹ ላይ!

ከሁሉም የከፋ ደግሞ ሃገሪቷ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አባል ናት! ሌላው አሳፋሪው ነገር ደግሞ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አባል ሆና በድጋሚ ተመርጣ በማገልገል ላይ መሆኗ የዓለም አቀፍ ኅብረተሰቡን ግዴታውን አለመወጣት የሚያሳይ ነው!

ኢትዮጵያውያን የዜጎቻችንን መገደልና ሬሳዎቻችንን አንሰተን መቅበር እንጂ፡ ስንት እንደተገደሉብን እንኳ የምናውቅበት መንገድ የለንም! ስለሆነም፡ የውጭ ሰዎች መቶ ሲሉን ተቀብለን መቶ ነው እንላለን። በኦሮሚያ አካባቢ ለደረስው የሰው ሕይወት ጥፋት የኦሮሚያ ሚዲያ ማዕከል ሰኞ ዕለት 150 ያህል ሰዎች መሞታቸውን አሳውቆ ነበር። ሰኞ ማምሻውን ያንን አንብቤ ትዊት ሳደርገው ራሴን ነበር የጠላሁት። ቁጥሩ በየሰዓቱ እየተለዋወጠ ነው!

ሕወሃትም መግደል እንጂ የገደላቸውን ዜጎቻችን ቁጥር አይውቅም! ሕወሃትም ላይ ሕዝቡ አመኔታ ስለሌው፡ ይህን ያህል ሰዎች ነው የገደልኩት ቢልም ኢትዮጵያውያን ጠበቅ አድርገን የምናውቀው ቀርቶ፡ ከእንግዲህ የዓለም ኅብረተሰብም አያምነውም! አሁን በጠቅላላ በነሐሴ 6/7 የሣምንት መጨረሻ የተጨፈጨፉት ዜጎች ቁጥር ከ110-150 ሊደርስ እንደሚችል ይገመታል። ራሱ የሙታኖቻችንን ቁጥር ለማወቅ አለመቻሉ ራሱን የቻለ መርገምት ነው!
ኢትዮጵያ አሁንም አያሌ ጀግኖች አሏት

ይህንን ሁሉ በደል በኢትዮጵያ ስም የሚፋረደው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው! ትክክለኛው የመጀመሪያው ፍርድ ከሕዝብ የሚመጣውና በሕዝብ የሚሠጠው በመሆኑ፡ እነዚህንም በየደረጃው መረጃ እያሰባሰብን ይኖርብናል። ለምሣሌም ያህል፡ ነሐሴ 8/2016 ጥዋት እንደሚሰማው አስደሳች ዜና ከሆነ፥ ሕዝቡ፡ ራሱንና የራሱን በመከላከል፡ ታሳሪዎች በነፍሰ ገዳዩ ሕወሃት ሥቃይ ሳይፈጸምባቸውና በግፍ ከመረሸናቸው በፊት በኦሮሚያም በአማራም እሥር ቤቶችን እየሰባበረ በግፍ በሕወሃት ጭለማ ቤት የተወረወሩትን ነጻ እያወጣቸው መሆኑ ይሰማል።

ከዚያ በኋላም እነዚህ ተግባሮች ቀጥለዋል፥ ነሐሴ 18/2017 በጎንደር!

እንዲሁም በጥጋብና በሕወሃት መመሪያ በሰላም ተሠልፈው በድምጽ ተቃውሞ ብቻ ባሰሙት ዜጎች ላይ ተኩስ ከፍተው ወጣቶቻችንን በአማራም ሆነ በኦሮሚያ ሲገድሉ የነበሩ የሕወሃት ጠባቂዎችም በሕዝቡ ተታፍነው ታግተው ከሚገኙት በተጨማሪ፣ የዜጎቻችንን ሕይወት መቅጠፊያ ለሕይወት መሣሪያ ስለነበሩ ሕይወቶቻቸውን የተነጠቁ ወታደሮችም ቁጥር በሁለቱ ክፍላተ ሃገራት እየጨመረ ነው – ለማንም ዜጋና ሃገር ይህ የማይሆንበት ሁኔታ በኖረ በተሻለ መሆኑ ቢታወቅም!

ቅዳሜ ዕለት ያ ሁሉ ግድያ በየሥፍራው ኦሮሚያ ውስጥ በሕወሃት ሲፈጸምና ሃገራችን ስታነባ፡ እሳቱ በጣም እየተንቦገቦገ ነው! ይህም ግዑዝ እሳት ያላንዳች ማወላዳት ያገኘውን ሁሉ ነው የሚበላው – ነጻነት እንፈልጋለን፥ በሕወሃት መገላመጥ፡ መገረፍ፡ መረገጥና መመዝበር ይብቃን ያሉትም፥ ሥርዓቱንም ለማቆየት የተላኩት ፖሊሶችና ወታደሮችም አልተረፉም። በዚህችም ሰማይና ምድር ቀስ በቀስ እየተገለባበጠ ባለባት ኢትዮጵያ ሃገራችን ውስጥም ትልቅ የሚያኮራ የሞራል ብቃት ያላቸውም ሰዎች (ፖሊሶችና ወታደሮች – ከአጋዚ በስተቀር) በየከተማዎቹ መሿለኪያን የየመንደሩ የጉራንጉር ግንባሮች ታይተዋል።

በቀርሳ/አርሲ ኦሮሞ ፌዴራል ፖሊስ ጢቤሶ ዣይ (Tibesso Xaji) በሰላም ቆመው የተቃውሞ ድምጻቸውን ባነሱ ወጣቶች ላይ የፌዴራል ፖሊስ ኮማንደሩ ተኩሱ ብሎ ትዕዛዝ ሲሰጥ፡ ድንጋይ ያለወሩ፣ ጦር ያልሰበቁ ዜጎች ላይ ለምን ተኩሳለሁ በማለት መሣሪያውን እንደማይጠቀም ለኮማንደሩ ሲነግረው፡ ያገኘው ምላሽ ተይዞና ታስሮ መመርመር ሳይሆን፡ በሥፍራው በኮማንደሩ ጥይት መገደል ነበር።

The body of an Oromo police officer killed by Agazi commandos, allegedly for crime of collaboration, when he tried to help a wounded woman (FB/JM)

The body of an Oromo police officer killed by Agazi commandos, allegedly for crime of collaboration, when he tried to help a wounded woman (FB/JM)

በወለጋም/ነቀምት የፖሊስ ኮማንዶ የቆሰለች ሴት ለመርዳት ሄዶ ከወደቀችበት ድግፎ ስላነሳት “ከጠላት ጋር ተባባሪ” ተደርጎ በአጋዚ ኮማንዶ ስለ መገደሉ አንብበናል! ይህ በፎተግራፉ ላይ የሚታየው ሬሣ በግፍ በሕወሃት የተረሸነ ጀግና ኦሮሞ ፖሊስ ፎቶ ነው!

%d bloggers like this: