በጎንደርና ወሎ ስላለው ሁኔታ የሕወሃት ቅጥፈቶች አንድና ሁለት፤ ተተርኮ የማያልቅ የሃገር ምዝበራ!

16 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

  ሀ. የአማራ ክልል መንግስት ከህዝቡ ጋር ባደረገው ውይይት ሁከትና ህገወጥ ተግባራትን እንዳማይቀበል ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 8፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአማራ ክልል መንግስት ከህዝቡ ጋር ባደረገው የመልካም አስተዳደርና የሰላም ውይይት ሁከትና ህገ ወጥ ተግባራትን እንዳማይቀበል አስታወቀ።

በዚህም ቅዳሜና እሁድ በክልሉ ምዕራባዊ አካባቢ ከዳንግላ እስከ ደጀን በምስራቁ ከወልዲያ እሰከ ደብረ ብርሃን ሊደረጉ የነበሩ ሁከቶች ከሽፈዋል።

የአማራ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ ያልተፈቀዱ ስልፎችን በክልሉ ለማስቀጠል የማህበራዊ ሚዲያዎችን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች በዚህ ሳምንት ቅዳሜና እሁድ ለማካሄድ ጥሪዎችና ጉትጎታዎች ሲካሄዱ ቆይተዋል።
 
____________________________________________________________________________________________________________________________________

  ከላይ የተጠቀስው በአማራ መንግሥት ቃል አቀባይ የቀረበው ደመቀ መኮንን ለፋና የሠጡትን ከዚሀ በታች የሠፈረውን መግለጫ የተከተለ ነው።

____________________________________________________________________________________________________________________________________
 

ህዝቡ ግን እነዚህን ጥሪዎችና ጉትጎታዎች ወደ ጎን በመተው ያለውን ጥያቄ ለማቅረብ እንደወትሮ ሁሉ ሰላማዊ መንገድን መርጧል ብለዋል።

የክልሉ መንግስት ከህዝቡ ጋር ባደረገው ውይይት ላይ ከግጭትና ሁከት ምንም የሚተርፍ ነገር እንደሌለ ተረድቶ መልዕክቱንም አስተላልፏል።

ባለፈው ሳምንት በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች በሁከትና ግጭቱ የጠፋው የሰው ህይወትና ንብረት መደገም እንደሌለበት በውይይቱ አንስቷል።

ሰላማዊ ሁኔታን ማስቀጠል የሁሉም ህብረተሰብ ሃላፊነት በመሆኑ ከመንግስት እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰሩም በውይይቱ ህብረተሰቡ አንስቷል።

መንግስትም ከህዝቡ የተነሱትን የመልካም አስተዳደርና የሰላም ጥያቄዎች በጥሞና አድምጦ በየዘርፉ በመለየት መፍታት አለበት ነው ያለው።

በሰላም ጉዳይ የማይናወጥ አቋም እንዳለው ህዝቡ በተጠራው ህገ ወጥ ስልፍና ሁከት ባለመሳተፍ በተግባር ማሳየቱን አቶ ንጉሱ ገልፀዋል።

መንግስት ከህዝቡ የቀረቡ ጥያቄዎችን እንደየሁኔታው በመለየት ለመፍታት መዘጋጀቱም አስገንዝበዋል።

በሁለቱ ቀናት (ቅዳሜ እና እሁድ) በክልሉ ህዝቡ መደበኛ ስራውን ሲያከናውን መዋሉን የገለጹት አቶ ንጉሱ፥ የክልሉ መንግስትም ለአስተዋዩ ህዝብ ታላቅ አክብሮትና ምስጋና ያቀርባል ብለዋል።
================
 
____________________________________________________________________________________________________________________________________
Agazi Sharp shooterጎንደር ሰላም የወረደ ለማስመሰል ቢሞከርም፡ ሕዝቡ ሃሣቡን ቀይሮ ከሕወሃት ጋር ከተሠለፈ፡ ሕዝቡ ቤቱን ዘግቶ በተቀመጠበት ዕለት እንኳ ምነው የአጋዚ ዓልመው ተኳሾች ምድር አልበቃ ብሏቸው ታዲያ ፎቅና ማማ ሳይቀራቸው መሣሪያዎቻቸውን ደግነው ዋሉ? ሕዝቡ አድማ ላይ ነው ማለት አሳፈራቸው ወይንስ አስፈራቸው?
____________________________________________________________________________________________________________________________________ 

  (ለ) እየተመዘገበ ያለው ፈጣን እድገት ተጠናከሮ እንዲቀጥል ብአዴን የመሪነት ሚናውን ይወጣል – አቶ ደመቀ መኮንን

 
አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 8፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ህዝቡ እያነሳቸው ላሉ ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ በመስጠት በሁሉም ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ፈጣን ልማትና ዕድገት ግለቱን እንደጠበቀ ተጠናከሮ እንዲቀጥል ብአዴን የመሪነት ሚናውን በላቀ ብቃት እንደሚወጣ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ።

በብሄር አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መከካል የሃሳብ ልዩነት ተፈጥሯል የተባለው ወሬም ከእውነት የራቀና መሰረተ ቢስ መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የብአዴን ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ በባህርዳር ከተማ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፥ በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በተከሰተው ግጭት ሳቢያ በጠፋው የሰው ህይወትና በወደመው ንብረት ብአዴን አዝኗል።
 

____________________________________________________________________________________________________________________________________

____________________________________________________________________________________________________________________________________
 

በብአዴን አመራር በክልሉ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች ክልሉ ይታወቅበት ከነበረው ድህነትና ኋላቀርነት በማላቀቅ ወደ ተሻለ የእድገት ከፍታ እንዲወጣና ህዝቡም ከልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ ተችሏል ብለዋል።

በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች በህገ ወጥ መንገድ በተካሄዱ ሰልፎች የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ ንብረት መድሟል ያሉት አቶ ደመቀ፣ ይህ ደግሞ የሰላም ወዳዱ የአማራ ክልል ህዝብ መገለጫ ባህሪ አይደለም ብለዋል።

የአማራ ክልል ህዝብ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታው አሁን ከደረሰበት ደረጃ እንዲደረስ በትጥቅ ትግል ሳይቀር ታላቅ መስዕዋት የከፈለ ባለ ታሪክ ህዝብ መሆኑንም ገልፀዋል።

ህዝቡ በተደራጀ አግባብ እያነሳቸው የሚገኙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለማቃለል ብአዴን ከመቸውም ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ብርቱ ጥረት እያደረገ ነውም ብለዋል።

ህዝብና መንግሥት ተቀራርበውና ተባብረው በመስራት የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማቃለል እያደረጉት ያለውን ጥረት በበለጠ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አቶ ደመቀ ተናግረዋል።

በክልሉ አንዳንድ አከባቢዎች ሰሞኑን የተካሄዱ ህገ-ወጥ ሰልፎች ተቀባይነት የሌላቸውና ፀረ-ሰላምና ፀረ-ልማት ተልዕኮ ባነገቡ አካላት ግፊት የተፈጸሙ መሆናቸውን ህዝቡ ተገንዝቦ የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ ነቅቶ መንቀሳቀስ እንዳለበት አስገንዝበዋል።

 
____________________________________________________________________________________________________________________________________

  ከሕወሃት ባላሥልጣኖች ጋር የጎንደር ሕዝብ ስምምነት ከደረሰ፣ ታዲያ ለምን ይሆን የከቤት አንወጣም አድማ ላይ ሁለተኛ ቀኑን ማሳለፉ? ከላይ የተጠቀስው በአማራ መንግሥት ቃል አቀባይ የቀረበው ደመቀ መኮንን ለፋና የሠጡትን ከዚሀ በታች የሠፈረውን መግለጫ የተከተለ ነው።

____________________________________________________________________________________________________________________________________
 

በተለይ መሰረተ-ቢስ ወሬዎችን በመንዛት ክልላዊና ሀገራዊ አጀንዳዎችን በማንሳት የህዝቡን ሰላም ለማወክና ልማቱን ለማደናቀፍ አልመው የሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላምና ፀረ-ልማት ኃይሎችን ህዝቡ በፅናት እንዲታገቸውም አሳስበዋል።

የድርጅቱ ሊቀመንበር በመግለጫቸው እንዳስገነዘቡት ሁከትና ብጥብጥ ለአማራ ክልል ህዝብ የሚጠቅም ሳይሆን በውስን የሕዝብ ሀብት የተገነቡ የመሰረተ ልማት አውታሮችን የሚያፈራርስና የሚያወድም እኩይ ተግባር ነው።

ህዝብ ለመንግሥት የሚያቀርባቸው ጥያቄዎች በተደራጀ አግባብ ህግንና ስርዓትን መሰረት አድርጎ መሆን እንዳለበት ጠቁመው፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት ሕዝባዊ ውይይቶች በየደረጃው እየተካሄዱ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

መንግሥትም በሀገሪቱ የተጀመረው የሰላም፣ የልማትና የዲሞክራሲ ሥርዓትን የማጠናከርና የህግ የበላይነትን የማረጋገጥ ሥራውን ከህዝብ ጋር ሆኖ አጠናከሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በብሄር አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መከካል የሃሳብ መከፋፈል ተፈጥሯል የተባለው ወሬም ከእውነት የራቀና የተለመደ የማደናገሪያ መሰረተ-ቢስ አሉባልታ እንደሆነም ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።

ብአዴን የካበተ የመምራት ልምድና ብቃት ያለው፣ በህግና ሥርዓት የሚመራ፣ የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅድና መርሃ ግብሮችን ነድፎ የሚተገብር፣ የሕዝቡን ሁለንተናዊ ጥቅም የሚያስቀድምና የድርጅት መርህን ተከትሎ እየሰራ ያለ ጠንካራ ድርጅት ነውም ብለዋል።
 

____________________________________________________________________________________________________________________________________

  ጎንደር ጸጥ ዕረጭ ብላ እሁድ ሙሉ ለሙሉ ቤት የመዋል አድማ ተግባራዊ አድርጋ ዋለች! ሰኞም አድማው እንዲቀጥል በሕዝቡ ጥሪ ተደርጓል!

____________________________________________________________________________________________________________________________________
 

ብአዴን በየወቅቱ ለሚነሱ ጉዳዮች የበሰለና የነጠረ የውስጥ ድርጅት ትግል እያካሄደ፣ የተለያዩ ሃሳቦች በነጻነት እንዲንሸራሸሩ እያደረገ ወደ አንድ ወሳኝ ድምዳሜ የሚደርስ በበሳል ዲሲፕሊን የሚመራ የሕዝብ ድርጀት ነው።

መሆኑም በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች ሰሞኑን በተከሰተው ሁከትና ግርግር ማዕከላዊ ኮሚቴው ተከፋፍሏል የሚባለው ወሬ ከእውነት የራቀ መሆኑን አቶ ደመቀ ተናግረዋል።

እንደዚህ አይነት መሰረተ-ቢስ ወሬዎች ለድርጅቱ አዲስ እንዳልሆኑና የነበሩ፣ ያሉ፣ ወደ ፊትም ሊነሱ እንደሚችሉ ጠቁመው፣ እውነታው ግን ሁሉም ጉዳይ በህግና በሥርዓት ብቻ የሚከናወን መሆኑን አረጋግጠዋል።

ብአዴን በየጊዜው ከድክመቱ ለመማርና ጉድለቱን ለማረም የተዘጋጅ ድርጅት መሆኑን የገለፁት አቶ ደመቀ፥ ህዝቡ ችግሮች ሲያጋጥሙት በውይይትና በመመካከር መፍትሄ ማበጀት እንደሚገባም ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
===============
 

____________________________________________________________________________________________________________________________________

  ባለፈው ኅዳር ኦሮሞች በብዛት የተጨፈጨፉ ጊዜ ሕወሃት ያቋቋማቸውን የሴቶች ማኅበራትና የኃይማኖት መሪዎችን በማሰባሰብ እንዲህ ብላችሁ መግለጫ አውጡ ተብሎ ተመሳሳይ ነገር ተደርጓል። እንዲሁም የኦፒዲኦን ኦሮሞች ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ በማሩሯጥና ለሚዲያ በመናገር ብዙ ተሞክሯል የሕዝቡን መነሳሳት ለማዳፈን። ይኽው እንደምናየው ለሕወሃት ስላልተሳካለት የሕዝቡ ቁጣ በየአቅጣጫው እየተፋፋመ ነው።

  ይህ አሁን ሕወሃት የሚሠራው ሥራ የተበላ ዕቁብ ነው፤

  በኦፒዲኦ ስም ያን ጊዜ መግለጫ ሲሰጡ የነበሩት ግለሰቦች ዛሬ ሥራቸው ላይ የሉም – ከሙክታር ከድርና ጥቂቶች በስተቀር!

____________________________________________________________________________________________________________________________________
 

  ሐ. ፖሊስ የደሴና አካባቢው ህዝብ ህገወጦች የጠሩትን ሰልፍ ባለመቀበል ላሳየው አጋርነት የላቀ አድናቆት እንዳለው ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 8፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደሴ፣ ደቡብ ወሎና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከተሞች የሚገኙ የሕብረተሰብ ክፍሎች ፀረ ሰላም ኃይሎች የጠሩትን ሰልፍ ባለመቀበል ላሳዩት የልማትና የዴሞክራሲ አጋርነት የላቀ አድናቆት አለኝ አለ ፖሊስ።

የደሴ ከተማ ፖሊስ እንደገለጸው ህገወጦች በደሴና በአካባቢው በሚገኙ ከተሞች ህገ ወጥ ሰልፍ እንዲካሄድ በማሕበራዊ ድረ ገጾች የተለያዩ አፍራሽ ቅስቀሳዎች ቢያካሂዱም ሰላም ወዳዱ የአካባቢው ሕዝብ ሰልፍ ባለመውጣት ታላቅነቱን አስመስክሯል።

የከተማው አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ዋና የሥራ ሂደት አስተባባሪ ኮማንደር ከበደ በሽር እንዳሉት፥ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አመራሮች ከሕብረተሰቡ ጋር ግልጽ ውይይት አካሂደዋል።

በዚህም ሕዝቡ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድና በውይይት ለመፍታት ዝግጁነቱን ማሳየቱን ጠቅሰው፥ ይህንንም ሰልፍ ባለመውጣት በተግባር በማረጋገጥ ላሳየው ጨዋነት ያላቸውን ምስጋናና አድናቆት ገልጸዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ያለለት ዘገየም ከማለዳ ጀምሮ በከተማዋ ምንም ዓይነት የጸጥታ ችግር እንዳልነበር አስታውቀዋል፡፡

“ቀደም ሲል ከሕብረተሰቡ ጋር በተደረገ ውይይት ድብቅ አጀንዳ ያላቸው የጥፋት ኃይሎች በሚያስተላልፏቸው የአመጽ ጥሪ በመሳተፍ በሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት እንዲፈጠር ፍላጎት እንደሌለው የገለጸው ሕዝብ በተግባር ሰላም ወዳድነቱን አረጋግጧል” ብለዋል፡፡

ከሕዝቡ ጋር በተደረገው ውይይት የቅሬታ ምንጭ የነበሩ አሰራሮች በግልጽ ተነስተው የጋራ መግባባት ላይ መድረሱ ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ትልቅ ሚና መጫወቱንም ኢንስፔክተሩ ገልጸዋል፡፡

በተያያዘ ዜና በቃሉ ወረዳ በሚገኙ ደጋን፣ ገርባና ሀርቡ ከተሞች ምንም ዓይነት የጸጥታ ችግር እንደሌለ የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ደረጀ ረታ አረጋግጠዋል፡፡

ጠዋት አካባቢ የባጃጅ ትራንስፖርት አገልግሎት በተወሰነ ደረጃ እጥረት ከመከሰቱ ውጭ ለሰላም የሚያሰጋ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳልነበር ጠቁመው፥ ሕብረተሰቡ ከጸጥታ ኃይሉ ጋር ተባብሮ የአካባቢውን ሰላም ለመጠበቅ ለወሰደው ኃላፊነት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በሚገኙት ባቲ፣ ጨፋ፣ ቦራ፣ ሰምበቴና ከሚሴ ከተሞችም እንዲሁ ምንም ዓይነት የጸጥታ ስጋት ሳይፈጠር መዋሉን የገለጹት ደግሞ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጀማል ብሩ ናቸው፡፡

ዋና ኢንስፔክተሩ በተለይ የሃይማኖት አባቶችና እድሮች በፀረ ሰላም ኃይሎች የሚተላለፈው የጥፋት ተልዕኮ እውን እንዳይሆን ላደረጉት እንቅስቃሴ ምስጋናቸውን ገልጸዋል።

በከተሞቹም ከማለዳ ጀምሮ የተለመደው እንቅስቃሴ በሰላማዊ መንገድ ሲካሄድ መቆየቱንም ኢንስፔክተር ጀማል አመልክተዋል፡፡

በደሴ ከተማ አንዳንድ የሸቀጣ ሸቀጥና የኤሌክተሮኒክስ ሱቆች የእረፍት ቀን ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከመዘጋታቸው በስተቀር በከተማዋ የተለመደው ማህበራዊ የግብይት ሂደት መስተዋሉን በአካባቢው የተዘዋወረው የኢዜአ ሪፖርተር አረጋግጧል።
================
 

በደብረ ማርቆስ አካባቢ ሊካሔድ የታሰበው ህገ ወጥ ሰልፍ መምከኑን ፖሊስ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፀረ ሰላም ሀይሎች በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረማርቆስ ከተማ እና አካባቢው እንዲካሄድ የቀሰቀሱትን ህገ ወጥ ሰልፍ ከሰላም ወዳዱ ህብረተሰብ ጋር በመሆን ማምከን እንደቻለ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

የመምሪው ሃላፊ ኮማንደር አሥራት በለጠ ለኢዜአ እንደገለጹት በማህበራዊ ሚዲያ የአካባቢውን ብሎም የሀገሪቱን ሰላም ለማወክ ጸረ ሰላም ሃይሎች እንዲካሄድ የቀሰቀሱት የሁከት ሰልፍ ከጅምሩ መክኗል፡፡

ኮማንደሩ እንዳመለከቱት ዛሬ በደብረ ማርቆስ ከተማ አንዳንድ ወጣቶች በህገ ወጥ መንገድ በቡድንና በተናጥል እየሆኑ ሰልፍ እናካሄዳለን በማለት ሁከት ለማነሣሣት ሙከራ አድረገው ነበር፡፡
____________________________________________________________________________________________________________________________________

  የጸጥታ ኃይሎች ሰላማዊ ሠልፎችን በኃይል ከበተኑ፣ ወጣቱን እሥር ቤት በየክፈለ ሃገሩ ካጎሩ ምንስ ስምምነት ያስፈልጋል ከሕዝቡ ጋር? አይ ሕወሃቶች የምትይዙትን የምትጨብጡትን ማጣታችሁ ገሃድ ሆነ! ቁርጠኛው ሰዓት ሲደርስ ምን ትሆኑ? እይተቃረበች እኮ ናት!

  የቀጣፊነታችሁ ብዛት አዲስ አበባ እስከ ዛሬ ውሃ ጠፍቶ የነበረው በኢልኒኖ ምክንያት ነው ብላችሁ ማውራታችሁ ራሱ ቀናችሁ ስለተቃረባች እቺን ዕለት እየበላን እየጠጣን እናሳልፍ ማለታችሁ ይሆን የዚህ ዐይነት መቀበጣጠር? ይህም ስለሕዝቡ ተቃውሞ ካሰማችሁት ቅጥፈት ተለይቶ የሚታይ አይደለም!

____________________________________________________________________________________________________________________________________
 

ሆኖም የፌዴራልና የክልል አድማ በታኝ ፖሊስ እንዲሁም መደበኛ ፖሊስ ከማህብረሰቡ ጋር በመሆን እንዲበተኑ ማድረግ ተችሏል።

ሆኖም ገን ለማነሣሣት በተደረገ ሙከራም በሰባት ሰዎች ላይ ጉዳይ የደረሰ ሲሆን፥ ከሰባቱ ሰዎች ውስጥ ስድስቱ ንጹሃን ዜጎች እና አንዱ ደግሞ የፖሊስ አባል መሆኑ ተነግሯል።

በአሁኑ ጊዜም ከሰባቱ ሰዎች ውስጥ ስድስቱ የደረሰባቸው ጉጋት አነስተኛ በመሆኑ ወደ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና ተደርጎላቸው ወደ ቤታቸው መመለሳቸው የታወቀ ሲሆን፥ አንዱም ከቆይታ በኋላ ህክምናውን ጨርሶ ወደ ቤቱ ይሄዳል መባሉን ከአማራ መገናኛ ብዙሃን ደርጅት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሽፈራው አየለ በበኩላቸው “ፀረ ሰላም ሀይሎች ሁከት ለመፍጠር የጠሩትን ሰልፍ ህገ-ወጥነት የደብረ ማርቆስና የአካባቢው ህብረተሰብ በመረዳቱ የታሰበው እኩይ ተግባር አለመፈጸሙን ተናግረዋል።

ጠዋት ላይ ሰልፉ ይካሄዳል በሚል በከተማዋ ውስጥ ለተወሰኑ ሰዓታት የትራምስፖርት አገልግሎት ተስተጓግሎ ነበር፤ አሁን ላይ ገን በፊት ወደ ነበረበት ቦታ እየተመለሰ ነውም ተብሏል።

በተለይም በከተማዋ ውስጥ አልፈው ወደ አዲስ አበባ እና ወደ ሌሎች አካባቢዎች የሚሄዱ ተኝከርካሪዎች እንደ ውትሮ እንቅስቃሴያቸውን በማድረግ ላይ መሆናቸውም ነው የተገለጸው።
================
 

ሁከት ለማስፋፋት የተደረገው ሙከራ በቁጥጥር ሥር መዋሉን መንግስት ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 2፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) በአገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ሁከት ለማስፋፋት የተደረገው ሙከራ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ገለፀ።

ጽህፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው በትናንትናው ዕለት በተለያዩ አካባቢዎች ያልተፈቀደ ሰልፍ ለማካሄድ ሙከራ ተደርጓል።

ከቅርብም ከሩቁም ባሉ የውጭ ጠላቶች አስተባባሪነት በማህበራዊ ሚዲያ የሚመራው የአገር ውስጥ የነውጥ ኃይል የህዝብና የመንግስትን ማስጠንቀቂያ ባለመቀበል በትናንትናው ዕለትም ግለሰቦችን አሰባስቦ በአንዳንድ የአገሪቷ አካባቢዎች በህገ-ወጥ መንገድ ሰልፍ ለመውጣት መሞከሩን ነው መግለጫው የጠቆመው።

በኦሮሚያና በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የመንግስትና የግለሰብ ንብረት ሲያወድሙ፣ መንገድ ሲዘጉና በንጹሃን ዜጎችና በጸጥታ ኃይሎች ላይ የሞት አደጋ ሲያደርሱ በመገኘታቸው በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ከተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ግለሰቦችን አሰባስቦ ወደ አዲስ አበባ በማስገባት ሁከቱን ለማስፋፋት ሲሞክሩም በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ነዋሪ በሆነው ህዝብ ጠቋሚነት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጿል።

በሁከቱ ከተሰማሩ ከእነኚህ ወገኖች ጋር በውጭ ካሉ የሁከትና የጥፋት ኃይሎች ስምሪት እንደወሰዱ የሚያረጋግጡ በርካታ ቁሳቁሶች ተይዘዋል።

የአሸባሪ ቡድን ባንዲራዎች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ስለቶች፣ የእጅ ቦምቦች፣ የአክራሪው የካዋርጂያ እንቅስቃሴ የቅስቀሳ ጽሁፎችና ባነሮችም እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ነው ያለው መግለጫው።

ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ በሚያዘው መሰረትም አጥፊዎቹን ወደ ህግ በማቅረብ ተጠያቂ የማድረግ ዝግጅት መጀመሩን ጽህፈት ቤቱ ጠቁሟል።

በቀጣይም ቢሆን የአገራችን የልማት፣ የሰላምና የህዳሴ ጉዞ ጥፋቷን በሚፈልግ ኃይል እንዲደናቀፍ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት አይፈቅዱም።

በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በጀመሩት ልክ ከመንግስት ጋር መሥራታቸውን እንዲቀጥሉ የኢፌዴሪ መንግስት ጥሪውን ያስተላልፋል።

በሁከት ፈጣሪዎቹ ሳቢያ ህይወታቸውን ላጡ ሰላማዊ ዜጎችና የጸጥታ ኃይሎች እንዲሁም ንብረታቸው ለወደመባቸው ዜጎች መንግስት የተሰማውን ሐዘን መግለፁን የኢዜአ ዘገባ ጠቁሟል።
 
=================

በአንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን በውይይት መፍታት ይገባል – የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 6 ፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አንዳንድ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ በውይይት መፍታት እንደሚገባ የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሳሰበ።

ከሰሞኑ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች በተቀሰቀሰው ሁከትና ግርግር በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ የሚታወቅ ነው።

የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤም ይህን በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰውን ሁከትና ግርግር አስመልክቶ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል።

አለመግባባቱ የወለደው ሁከትና ግርግር ሰላም ወዳዱን የህብረተሰብ ክፍል የእለት ተእለት እንቅስቃሴውን የሚያስተጎጉል እንደሆነም ነው በመግለጫው የተነሳው።

የጉባኤው የበላይ ጠባቂ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያሪክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ፥ ህዝቡ የሚያነሳቸው ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ ቀርበው በውይይት እና ምክክር ምላሽ ቢያገኙ መልካም መሆኑን ተናግረዋል።

ምዕመኑ በየቤተ እምነቱ ለሀገሪቱ ሰላም ተግቶ ሊጸልይ ይገባል ያሉት ብፁዕነታቸው፥ በሰውና በንብረት ላይ በደረሰው ድንገተኛ አደጋም በሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ስም የተሰማቸውን ልባዊ ሀዘን ገልጸዋል።
 
____________________________________________________________________________________________________________________________________

  ከዚህ ቀደም ብሎ ካድሬው ፓትርያርክ መላ ክርስቲያን የሕወሃት ተቃዋሚዎችን በእምነት ሊኖረው የሚገባውን እግዚአብሔርን ትቶ በፖለቲካ መሣሪያነቱ በውግዘት አስፈራርቶ ገዝቶ አልነበረምን? መረጃውን ከታች ይመልከቱ!

____________________________________________________________________________________________________________________________________
 

የጉባኤውን መግለጫ ያቀረቡት የጉባኤው የቦርድ አባል አባ ሀይለማሪያም መለሰ፥ የጉባኤው አባላትና የሀገሪቱ የሀይማኖት መሪዎች የሀገሪቱና የህዝቡ ሰላም በእጅጉ ያሳስበናል ብለዋል።

ምዕመኑም በመከባበር ላይ የተመሰረተ የአብሮነት እሴቶችን ማጎልበት እንደሚገባው ጠቅሰው፥ የየቤተ እምነቱ የሀይማኖት መሪዎችና ሰባኪያነ ወንጌልም ሰላምን አብዝተው ሊሰብኩ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ለሀገርና ለወገን የሚበጁ ጥያቄዎችን ማንሳት መሰልጠን ነው ያሉት አባ ሃይለማሪያም፥ ምላሹን በልበ ሰፊነትና በትዕግስት መጠበቅ ተገቢነት አለው ሲሉም ምክራቸውን አስተላልፈዋል።

አያይዘውም በተለያዩ የመንግስት የስራ ሀላፊነት ላይ የተቀመጡ ግለሰቦች የተጣለባቸውን፥ ሀገርና ህዝብን የመምራት ከባድ አደራ በአገልጋይነት መንፈስ መወጣት እንደሚገባቸውም አንስተዋል።

ጉባኤው የሀገር ሽማግሌዎች፣ የጎሳ መሪዎችና በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው ወገኖች ሁሉ፥ ህዝብን በማረጋጋትና በመምከር ሀገራዊና ሀይማኖታዊ ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አስገንዝቧል።

በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገጾች የሚነዙ ሀሰተኛ ወሬዎችን ህዝቡ አምኖ ከመቀበሉ አስቀድሞ መመርመር ይገባዋልም ብሏል።
==================
 

በዘራቸው የተመረጡት ካድሬው ፓትሪያርክ ለኢትዮጵያውያን መጨፍጨፍ ግድ ሳይኖራቸው፡ ሕወሃት እንዳይገለበጥ ውግዘትን መሣሪያ አድርገው ቀረቡ

አማራና ኦሮሚያ ክልሎች በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱት ግጭቶች የሰው ሕይወት ማለፉንና የንብረት ውድመት መድረሱን አስመልክቶ፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ ጸሎተ ምህላ እንዲይዙና የሰላም ትምህርት ተጠናክሮ እንዲካሄድ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማክሰኞ ነሐሴ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ጥሪዋን አቀረበች፡፡

ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ በክልሎቹ ተከስቶ ያለውን ግጭት፣ ውዝግብና ሁከት ቆም ብሎ ማስተዋል እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ የተፈጠሩ ችግሮች ሁሉ በሕጋዊ መንገድ፣ በወንድማማችነት መንፈስና በውይይት እንዲፈቱም አሳስበዋል፡፡

በዋናነት የተፈጠሩ ችግሮች ይፈቱ ዘንድ በመላው ዓለም ያሉ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ፣ አሁን ተይዞ ባለው የፆም ሱባኤ (የፍልሰታ ፆም) በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎትና ምህላ፣ እንዲሁም የሰላም ትምህርት ተጠናክሮ እንዲደረግና እንዲካሄድ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙ አዛውንት፣ ምሁራን፣ አባወራዎችና እማወራዎች፣ ወጣቶችን በመምከርና በማስተማር ከሕይወት መጥፋትና ከሀብት ውድመት እንዲታደጉ ጠይቀዋል፡፡

ፓትርያርኩ ሁሉም ወገኖች አሉን የሚሏቸውን ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ፣ በውይይትና በምክክር በሰላማዊ መንገድ መፍታት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ ሰሞኑን በተፈጠሩ ግጭቶች ሕይወታቸውን ላጡና ንብረታቸው ለወደመባቸው ዜጐች ቤተ ክርስቲያን ጥልቅ ሐዘን እንደገባት አክለዋል፡፡
 

በሪዮ ኦሎምፒክ እነ ሮቤል ኪሮስና አቶ ኪሮስ ሃብቴ ያደረሱብን ውርደት፤ የዘር ስፖርት!


 

%d bloggers like this: