በትግሬነት የተመረጡት ‘የኢትዮጵያ’ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ በሁለት አፍ የቀላመዱበት ዛሬ ሕወሃትን አርበድባጁን የሕዝብ ትግልና የሳቸውን ቅሌት ነገ ታሪክና ትውልድ ምን ያህል ያፍሩባቸው ይሆን?

18 Aug

በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)
 

በምዕመናን መጥፋት ልባቸው የተሰበረው 'የኢትዮጵያ' ኦሮቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ (ፎቶ ሪፖርተር)

ሲኖዱ ባደረሰባቸው ወቀሳና ምዕመናኑ ቤተ ክርስቲያኒቷን ለሕወሃት አባሎች በመተው ምዕመናን መጥፋት ምክንያት ልባቸው ክፉኛ የተሰበረው ‘የኢትዮጵያ’ ኦሮቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ (ፎቶ ሪፖርተር)


 
በኦሮሚያና በአማራ የኢትዮጵያውያን ትግል ተጋግሎ፡ ሕወሃትን ማቃጠል ሲጀምር፣ ቀደም ሲል በሲኖዱ በመወገዝ የመጀመሪያው በመሆናቸው የሚታወቁት ‘የኢትዮጵያ’ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ማትያስና ቤተ ክርሲያኒቷ ናቸው ከሁሉም የከሠሩት። እንዲሁም በግለሰቡ ቅሌት ምክንያት ቤተ ክርስቲያናችን ላይ ትልቅ ጉዳት ደርሷል።

ከዚህ በታች የተለጠፉት መረጃዎች እንደሚያሳዩት፡ ፓትርያርኩ በቴሌቪዥን ቀርበው ነበር ለመብታቸው የሚታገሉትን ዜጎች በማውገዝና በመገዘት የሕወሃት አስተዳደር ለዘመናት እንዲቀጥል ሞክረው ነበር።

 

ታዲያ እንዴት ነው ፓትርያርኩ ሌላ ምላስ አብቅለው በጥቂት ቀናት ልዩነት “የሃገሪቷን ሰላም ለመጠበቅ ወጣቶች ድርሻቸውን እንዲወጡ” የጠየቁት ከሌሎች የኃይማኖት ሰዎች ጋር አብረው የቆሙት?

ወጣቶች ያላቸውን መልካም ሐሳብና ዕቅድ በሰላማዊና በሠለጠነ መንገድ ለሚመለከተው አካል ማቅረብና ምላሹንም በትዕግሥት የመጠበቅ ልምድ እንዲኖር በልበ ሰፊነት መመካከርና መደማመጥ እንደሚገባ፣ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የበላይ ጠባቂዎች አሳሰቡ፡፡

የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ የተቋማቱ የበላይ ጠባቂዎች ዓርብ ነሐሴ 6 ቀን 2008 ዓ.ም. ባወጡት መግለጫ፣ ወጣቶች የአገርና የሃይማኖት ተረካቢና ባለአደራ መሆናቸውን በመገንዘብ የሚጠበቅባቸውን አገራዊ ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት በሚያስችል መልክ ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ አደራ ብለዋል፡፡

ወጣቶች የሚረከቧት አገር በሁለንተናዋ በዕድገትና ብልጽግና ብሩህ ተስፋ ያላት መሆኗን በመገንዘብ፣ ሰላሟን በመጠበቅ ድርሻቸውን እንዲወጡ በአጽንኦት አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም ዘመኑ የመረጃ በመሆኑ በማኅበራዊ ገጾች የሚለቀቁ መረጃዎችን በማጣራት፣ ጠቀሜታቸውንና ገንቢነታቸውን በመመርመር እንዲጠቀሙባቸው ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

በተለያዩ የመንግሥት ሥራዎች ላይ ያሉትም አገርንና ሕዝብን የመምራትና የማስተዳደር ከባድ አደራን በቅንነትና በአገልጋይነት መንፈስ እንዲወጡ፣ ከሕዝቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን የማስተናገድና የመመለስ ጥረታቸውን የበለጠ እንዲጠናከር ቀን ከለሊት መትጋት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም ከመንገድ የወጣ ሁኔታ ሲያጋጥም ግን ሆደ ሰፊ በመሆንና በከፍተኛ ትዕግሥትና ማስተዋል አስፈላጊውን ቁጥጥርና ጥበቃ እንዲያደርጉ የበላይ ጠባቂዎቹ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡

የአገር ሽማግሌዎች፣ የጎሳ መሪዎችና በማኅበረሰቡ ሰፊ ተቀባይነት ያላቸው ወገኖች ሁሉ የአገሪቱ ሰላም እንዲጠበቅ ሕዝብን በማረጋጋትና በመምከር የበኩላቸውን አገራዊ ኃላፊነት እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡

በየደረጃው የሚገኙ የሃይማኖት መሪዎችና አስተማሪዎች የሃይማኖት ተልዕኮ ሰላምን መስበክና በምድሪቱ ላይ ሰላምን ማፅናት በመሆኑ ስለሰላም፣ ስለሰዎች ወንድማማችነት፣ ስለመከባበርና አጠቃላይ የፍቅርንና የርኅራኄ ትምህርቶችን በማስተማርና በማስረፅና አማኞች መልካም ሥነ ምግባርና ሰብዕና እንዲኖራቸው በማድረግ መንፈሳዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አደራ ብለዋል፡፡

ምዕመናንና ምዕመናት ሁሉ ስለአገሪቱ ሰላም እንደየሃይማኖታቸው ተግተው እንዲጸልዩ የሃይማኖቶች የበላይ ጠባቂዎች መንፈሳዊ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ኃላፊዎችና ሠራተኞች በአገሪቱ የተፈጠረው አለመግባባትና ግጭት በሰላማዊ መንገድ መፍትሔ እንዲያገኝ በማድረግ በኩል ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በጥንቃቄና በከፍተኛ ኃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
/ከሪፖርተር የተወሰደ
==================
 

ምዕመናኑ ቤተ ክርስቲያኗን ሸሿት?

ከዚህ በፊት በዚህ አምድ ላይ እንደጠቀስነው፡ አሁን የቀለሉት ‘ፓትርያርክ’፣ በራሳቸው አንደበት፣ አቡነ ማትያስ እንዳሉት:- “ብዙ ቢሊዮኖች ብር አገኘን ግን አማንያን ሸሹን!“– አዲስ አድማስ ባለፈው ጥቅምት እንደጠቀሳቸው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሰበካ ጉባዔ መደራጀት ስትጀምር ገቢዋ በመቶ ሺሕ ብር የነበረ ቢሆን፣ በአሁኑ ጊዜ ወደ ቢሊዮኖች ብር ማደጉን የገለጹት ፓትርያርክ ማቲያስ፣ የምዕመናኗ ቁጥር ግን እየቀነሰ መሆኑን አስታውቀዋል።

ባህር አቋርጦ፣ ድንበር ተሻግሮ፣ እስከ ምድር ጽንፍ ተጉዞ፣ አስተምሮና ያላመነውን አሳምኖ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ማድረጉ ይቅርና በአገር ውስጥ ያሉትን ወገኖች፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አሰባስቦ ምዕመናንን ማባዛት ብዙ እንዳልተሄደበት ፓትርያርኩ አስታውቀዋል፡፡

ቤተ ክርስቲያኗ ትናንትና ስመ ክርስትና ሰጥታ በአባልነት የተቀበለቻቸው ልጆቿ፣ ዛሬ እናት ቤተ ክርስቲያናቸውን እየካዱ ወደ ሌላ ጎራ መቀላቀላቸው እየናረ መምጣቱን ምክንያት ቢያደርጉም፣ ውስጥ አዋቂዎች ደግሞ የእርሳቸው አመራር ደካማነትና ቤተ ክርስቲያኗን የሕወሃት ፈርጣማ ክንዶች የቀለብ ምንጭና የደኅንነቱ መሥሪያ ቤት ደግሞ መጠቀሚያ አድርጓታል ይላሉ!

ቤተ ክርሲትያኗ ውስጥ – እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው ቢሮ ሁሉ – ዙርያቸው እንዲከቧቸው የተደረጉት የደኅንነት ሰዎችም በዋና አማካሪዎቻቸው ስም፡ በዘር የተመለመሉ ናቸው። ቢሆንም ከጠ/ሚሩ የእርሳቸው ይሻላል – በዝርያም ከሕወሃት ጋር አንድ ናቸውና!

ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው አማካሪ ተብሎ ከተቀመጠለት የሕወሃት ተወካይ (አሁን የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር) በቅርብ መመሪያ እየተቀበለ ይሠራ ነበር እንጂ አንዳች ሃሣብ በራሱ አፍልቆ (ደግነቱ እርሱም ስለሌው) ስለማይሠራ ጸጸት ይኖረዋል ተብሎ አይገመትም። ምዕመናኑ ቤተ ክርሲትያኒቷን በብዛት ገንዘቧን ለሚቦጠቡጧት የሕወሃት ሰዎች ለጊዜው ለቀውላቸዋል።
 
=========

 

በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶችና የከተማዋ ነዋሪዎች የታሰሩ ወጣቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ አፈሳውም እንዲቆም ጠየቁ

ነሃሴ 6 ቀን 2008 (ኢሳት ዜና):- የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአንድ ቀን በፊት በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ የሃይማኖት አባቶችን በመሰብሰብ ሃገሪቱ ሰላማዊ እንድትሆን ህብረተሰቡን እንዲመክሩ ጠይቀዋል፡፡ የሃይማኖት አባቶች ለርዕሰ መስተዳድሩ በሰጡት ምላሽ በተለያየ ጊዜ ሕዝቡ የሚያቀርበውን ጥያቄ በይደር ከማቆየት ይልቅ አፋጣኝ የሆነ መልስ መስጠት እንደሚገባ የተናገሩ ሲሆን አሁንም በወልቃይት የአማራ ማንነት ላይ የተነሳውን የሕዝብ ጥያቄ በአስቸኳይ ልትመልሱ ይገባል በማለት አሳስበዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶች “ወደ ሕዝቡ ወርደን ተው! የምንለው ለተጠየቀው የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ ምላሽ ይዛችሁ ስትጠሩን ብቻ ነው” በማለት ያልተጨበጠ ነገር በመያዝ ወደ ህዝቡ ሄደው መጋጨት እንደማይፈልጉ ተናግረዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶች በ1997 ዓም.የነበረውን የህዝቡንና የመንግሰትን ግጭት አስታውሰው በወቅቱ “የሕዝቡን ማንኛውንም ጥያቄ እንመልሳለን ህዝቡን አረጋጉልን” ተብለው ጣልቃ እንዲገቡበገዢው መንግሰት ተጠይቀው የማረጋጋት ስራ ቢሰሩም፤ የገዢው መንግስት ግን ምንም ዓይነት የማስተካከያ ርምጃ ሳይወስድ በመቅረቱ በህዝቡ ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት እንዳሳጣቸው ተናግረዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶች አክለውም ሰሞኑን በጭፍን ሲታፈሱ የነበሩት ልጆቻቸው ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡ ይህን መፈጸም ህብረተሰቡ ወደ ምሬት በመግባት የብቀላ እርምጃዎችን እንዳይወስድ ለማድረግ ትልቅ ጠቀሜታ ስላለው የተባባሰ ነገር ከመፈጠሩ በፊት የክልሉ መንግስት ሊወስድ የሚገባው ዋናው እርምጃ ይህ መሆኑን ተናግረዋል።

በተያያዘ ዜና ትናንት የክልሉ አመራሮች በተለያዩ አዳራሾች የብአዴን ኢህአዴግ አባላትን በማሰባሰብ በወቅታዊ የሃገሪቱ ጉዳይ ላይ አወያይተዋል፡፡የክልል ምክር ቤትን አዳራሽ ጨምሮ በተለያዩ መስሪያ ቤቶችና አዳራሾች በተካሄዱት ስብሰባዎች የተገኙት አባላት በብአዴን ዝምታ ከፍተኛ ቁጭት ላይ መሆናቸውን ሲገልጹ ተሰምተዋል፡፡

“እንደ ብአዴን ያለብንን ችግር ግለጹልን” ተብሎ የተጠየቀው ተሰብሳቢ “ለመሆኑ ብአዴን የሚባል ፓርቲ አለ ወይ?” በማለት መልሰው የጠየቁ ሲሆን ፣ ህዝቡ በህውሃት መገዛት ይበቃናል ብሎ ሲነሳ አመራሩም የሕውሃትን ዕድሜ ለማስቀጠል ከሚሯሯጥ አብሮ በቃኝ ሊል እንደሚገባው በአንክሮ ተናግረዋል፡፡

“ሕዝቡ የሕውሃት አገዛዝ በቃኝ ካለ አብራችሁ ልትታገሉና ራሳችሁን ችላችሁ ልትመሩ ይገባል” በማለት የተናገሩት ተሰብሳቢዎች ፣ ይህን ማድረግ ካልቻሉ ህዝቡ በትግሉ ገፍቶ ራሱን ነጻ እንዲያዎጣ መልቀቅ እንዳለባቸው በአንክሮ ተናግረዋል፡፡

በሁሉም አካባቢ በተሰበሰቡ የፓርቲው አባላት እንደተጠየቀው በሰሞኑ ሰላማዊ ሰልፍ ምክንያት የታሰሩት ከአንድ ሽህ የሚበልጡ ወጣቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱና አሁንም በመሳደድ ላይ ያሉ የከተማዋ ነዋሪዎችን የክልሉ መንግስት ሊታደጋቸው እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡

በስብሰባው በርካታ ጉዳዮች ተነስተው የብአዴን ችግሮች የተነገሩ ሲሆን በሁሉም የስብሰባ ቦታዎች በተገኙ መረጃዎች የብአዴን አመራሮች ሙሉ በሙሉ ወደ ትግሉ እንዲቀላቀሉና ከሕዝብ ጎን በመቆም የህውሃትን ስርዓት “በቃን!” እንዲሉ አባላቱ ጥያቄውን ለአመራሮች አቅርቧል፡፡

በሌላ በኩል በእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተተኩሶባቸው ከባሕር ዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ህክምና ሲሰጣቸው ከነበሩት መካከል ሁለት ወጣቶች ሕይወታቸው አልፏል፡፡ በትላንትናው ዕለት ያረፈው የደብረ ማርቆስ ወጣት አስክሬኑ ወደ ደብረ ማርቆስ በመጓዝ የቀብሩ ስነስርዓት ተፈጽሟል፡፡

የደብረ ማርቆስ ነዋሪዎች በወጣቱ ሞት የተሰማቸውን ሐዘን በቁጭት እየገለጹ ሲሆን፣ ሰሞኑን በሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ባዶ እጃቸውን በመውጣት በባሕር ዳር ወጣቶች ላይ የደረሰው ግድያ እንዲከሰት እንደማይፈቅዱ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ በአጋዚ አልሞ ተኳሸች ጭንቅላቱን ተመቶ ሲያጣጥር የሰነበተው ማንነቱ ያልታወቀው ሌላው ወጣትም በዛሬው እለት ህይወቱ አልፏል፡፡ ወጣቱ በኪሱ የያዘው ምንም አይነት መታወቂያ ባለመኖሩ ማንነቱ ያልተለየ ሲሆን ምንም ዓይነት ቤተሰብ መጥቶ እንዳልጠየቀው የሆስፒታሉ ሃኪሞች ተናግረዋል፡፡

ህይወቱ እስኪያልፍ ድረስ ከሆስፒታሉ ሐኪሞች ኪስ በሚወጣ ገንዘብ ልዩ ልዩ እርዳታ ሲደረግለት የቆየውን ወጣት አስክሬን ለመረከብ የመጣ ቤተሰብ ባለመኖሩ በነገው እለት በከተማ አስተዳደሩ በኩል ግብዓተ መሬቱ ሊከናዎን እንደሚችል ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ተዛማጅ:

የኦርቶዶክስ ገቢ በቢሊዮን ቢቆጠርም የምዕመናኑ ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን ካድሬው ፓትሪያርክ በተሰበረ ልብ ለሕዝብ ይፋ አደረጉ

ቤተ እምነቶች የሰው ሕይወት ጭፍጨፋና የንብረት መውደም እንዲቆም የጠየቁ አስመስለው በኦሮሚያ የእኩልነት ትግል ላይ የተነጣጠረ አቋም አንጸባረቁ!

Ethiopian Orthodox Synod warns patriarch to respect rule of law & institution; rejects plaintiff’s pol. decrees, ‘rules’, solicited-travels

Patriarch’s shame in the Vatican when the Pope rejected condemning Oromo Protests as anti-Christian:

Pope conveys to TPLF patriarch importance of promoting “peaceful coexistence based on reciprocal respect and reconciliation, mutual forgiveness and solidarity”!
 

%d bloggers like this: