የእሁዱን የአዲስ አበባ ሠልፍ ለሚመክቱና መሥዋዕትነት ለሚከፍሉ የፀጥታ ሠራተኞች ሕወሃት ማካካሻ እንደሚሰጥ አስታወቀ – ዋዜማ ራዲዮ!

20 Aug

የአዘጋጁ አስተያየት፡

    በሕግ ሕዝቡን የማያስተዳድረው፣ ራሱን ለሕግ ተገዥ አድርጎ የማያውቀው የሕወሃት አስተዳደር፡ ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ሲሆንበት፡ የፀጥታ ኃይሉንም ሠልፉን እስከመከትክልኝ፡ ጠላቶቼን እስከ ጨፈጨፍክልኝ ድረስ (የሲቪልና ጦር ወንጀሎችን በመፈጸም ማለት ነው) ብርና ማዕርግ አርከፈክባችኋለሁ ማለቱ ልብ ሊባል ይገባል!

 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሠልፍ እንደሚደረግ መነገሩን ተከትሎ ሕወሃት ሠልፉን በማናቸውም መንገድ ለማምከን እየተዘጋጀ ነው። ነገ እሁድ በአዲስ አበባ በስሥልጣን ላይ ያለውን ሥርዓት ለመቃወም የተጠራው ሠልፍ በተለያየ የሀገሪቱ አካባቢ ሲካሄድ የሰነበተው ተቃውሞ አካል ነው።

በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎች ከፍተኛ የፀጥታ ኃይሎች የሚታዩ ሲሆን በካምፕ የሚገኙ የሠራዊት አባላትን የማሰማራት ዕቅድ መኖሩንም የፖሊስ ምንጮች ተናግረዋል።

የፌደራል ፖሊስ ኮምሽን በበኩሉ በአዲስ አበባም ይሁን በክልሎች የሚደረጉ የተቃውሞ ሠልፎችን በትጋት ለሚመክቱና መሥዋዕትነት ለሚከፍሉ የፖሊስ አባላት ማካካሻና የማዕረግ እንደሚያገኙ እንደተነገራቸው የሠራዊቱ አባላይ ለዋዜማ ገልፀዋል

መንግስት የፀጥታ ኃይሎች ሊያፈግፍጉ አልያም ሕዝቡን ሊደግፉ ይችላሉ የሚል ሥጋት እንዳለበት ጠቋሚ ነው።

በሃገሪቱ የቀጠለውን ሃዝባዊ አመፅ የከትሎ የምዕራባውያን ሃገራት ተከታታይ የጉዞ ገደብ ማስጠንቀቂያ እያወጡ ነው። ዜጎቻቸው ተቃውሞ ባለባቸውና ሊካሄድ በታቀደባቸው አካባቢ እንደይገኙ መክረዋል።

ወራትን ባስቆጠረውና አሁን በተባባሰው አመፅ ሳቢያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ላይ አደጋ ያንዣበበት ሲሆን የውጪ ኢንቨስትመንት መቀዛቀዝ ሊከተል እንደሚችል ስጋታቸውን የሚገልፁ ባለሙያዎች ብዙዎች ናቸው።

በአዲስ አበባ በሚደረገው ሠልፍ ላይ ለመሳተፍ የተዘጋጁ ሁለት ወጣቶች እንደነገሩን ከሆነ ሠልፉን በኃይል ለማቆምና ለመግደል ገዢው ፓርቲ ወደኋላ እንደማይል ተርድተናል ግን ደግሞ ለውጥ ፈላጊ መሆናችንን በተግባር የምንገልፅበት ጊዜ አሁን ነው።

“በገደሉን ቁጥር እንበረታለን፣ መግደል የሕዝብን ጥያቄ ሊያቆመው አይችልም፣ አሁን ጊዜው የለውጥ ነው” ይላል ከዩንቨርሲቲ ከተመረቀ አራት አመት ያስቆጠረውና ሥራ ፈልጎ ማግኘት ያልሆነለት ወጣት።

በተያያዘ ዜና፣ በጎንደር ዛሬ ቅዳሜ ዕለት ነጭ ልብስ በመልበስ በተካሄደ ተቃውሞ ሳቢያ ቢያንስ አንድ ወጣት በፀጥታ ሀይሎች መገደሉን የአካባቢው እማኞች ተናግረዋል። ዕለቱ የቀድሞው መሪ መለስ ዜናዊ አራተኛ ሙት አመት የሚዘከርበት ነበር።
 

ተዛማጅ:

በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገፆች በአዲስ አበባ ነገ ነሃሴ 16 ሰልፍ ይደረጋል የሚል የተሳሳተ መልእክት አየተለለፈ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ፖሊስ አሳሰበ

ለሰላም መጠበቅ ከመንግስት ጎን እንደሚቆሙ የአዲስ አበባ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ተናገሩ

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአፍሪካ ሃገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ ሰጠ

ህብረተሰቡ ፀረ ሰላም እንቅስቃሴዎችን በመከላከል ረገድ እገዛ እያደረገ ነው – የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን

ህወሃት የብሄር ብሄረሰብ እኩልነትን የማይቀበሉ ሃይሎች የሚፈጽሙትን ህገወጥ ተግባር ከመላው ህዝብ ጋር እንደሚታገል አስታወቀ
 

%d bloggers like this: