ኢትዮጵያ በሪዮ ኦሊምፒክ ዝቅተኛ ውጤት ማሰገንዘቧን ሕወሃት አመነ፣ ምክንያቱን ግን ስለማይነግረን ስግብግብነቱ/ዘረኝነቱ ሃገራችንን እንዴት እንዳዋረደ ኢትዮጵውያን እንጠቁመው!

24 Aug

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)
 


 

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 16 ፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ቡድን በሪዮ ኦሊምፒክ ደካማ የተባለውን ውጤት አስመዝግቧል።

ቡድኑ ወደ ስፍራው ሲያቀና ካስቀመጠው እቅድ አንጻር እጅግ ዝቅተኛ የተባለውን ነው ማሳካት የቻለው።

ኢትዮጵያ በምትታወቅባቸው የረዥም ርቀት የሩጫ ውድድሮችም ማግኘት የተቻለው አንድ የወርቅ ሜዳልያ ብቻ ነው።

በሴቶች 10 ሺህ ሜትር አልማዝ አያና የርቀቱን ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር ያስገኘችው የወርቅ ሜዳልያ ለኢትዮጵያ ብቸኛው የአሸናፊነት ሜዳልያ ነበር።

በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ገንዘቤ ዲባባ እና በወንዶች ማራቶን ፈይሳ ሌሊሳም ከአልማዝ አያና ቀጥሎ ሊጠቀስ የሚችለውን የብር ሜዳልያ አምጥተዋል።

ከዚህ ውጭ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር ጥሩነሽ ዲባባ፣ በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ታምራት ቶላ፣ በሴቶች ማራቶን ማሬ ዲባባ፣ በሴቶች 5 ሺህ አልማዝ አያና እና በወንዶች 5 ሺህ ሜትር ሃጎስ ገብረህይወት የነሃስ ሜዳልያዎችን አስገኝተዋል።

ኢትዮጵያም የሪዮ ተሳትፎዋን በ1 የወርቅ፣ በ2 የብር እና በ5 የነሃስ በአጠቃላይ በስምንት ሜዳልያዎች አጠናቃለች።

ውጤቱን ተከትሎም ከአለም 44ኛ ከአፍሪካ ደግሞ 3ኛ ደረጃን ይዛለች።

 

ምን ይሆን ችግሩ?

የአመራር ዕጦት ነው! ሃገራችን ከመሪዎች ይልቅ ሕወሃት የተሰኘ የወንበዴዎች ድርጅት እንደመዥገር ነክሶ ሰለያዛት ነው! በአሁኑ ወቅትም፣ ይህንን ሆዳም ድርጅት ጥርሱን ሰብሮና ሆዱን ቀዶ ሃገሪቷን ለማላቀቅ ኢትዮጵያውያን በሕይወታቸው ነጻነቷን ለመዋጀት በመዋደቅ ላይ የሚገኙት በዚህ ምክንያት እንጂ በዝርያ እንደሆን ሊታወቅ ይገባል!

ሕወሃት የሚፈልገው ኢትዮጵያን ማክበርና ማስከበር ሳይሆን፣ ዓላማው ገንዘብና ሌሎች ጥቅሞች ማግኘት ነው!

ሕወሃት ውስጥ የተሰባሰቡትን ሰዎች የሚያስተሳስራቸው ጠንካራው ገመድ ትግራዊነታቸው ሳይሆን፡ ሶስት ነገሮች ብቻ ናቸው፦

  (ሀ) በቀበሌና በወረዳ ተሰባስበው በጥቅም ዓላማ በመተሳሰራቸው እርስ በእርስ ቢተማሙም፣ ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሁሉም እንደየአቅሚቲ መዝረፉ ቃለ መሃላቸው ነው!

  (ለ) ሥነ ሥርዓት፡ ሕሊና የሚባል ነገር ስለሚጎድላቸው ምን ይዘረፋል? ምን ጥቅም ይገኛል የሚለውን በጋራ ሰለሚጋሩ፣ ያየናቸው የሕወሃት ባለሥልጣኖቻቸው – ፓትሪያርኮች ጭምር – አፍቅሮተ ገንዘብ፣ ዝሙትና በእግዚአብሒር ስም ክህደትንና ጥፋትን እውነት ለማድረግ ዐይናቸውን በጨው አሽተው ለመጠቃቀም ምለው የተገዘቱ ከMafia የባሰ የፖለቲካ ድርጅት አባላት ናቸው!

  (ሐ) ኢትዮጵያን ይወዳሉ! ይሀ የደም፣ የታሪክና የብሔራዊ ወገናዊነት ጉዳይ ሳይሆን፣ እነርሱን አመነሽንሻ የምትይዝ በመሆኗ ለምቾታቸውና ጥቅሞቻቸው ሲሉ ይፈልጓታል! ሃገራችን ይሏታል -ይህንን የሰማ አንድ ደፋር ኢትዮጵያዊ ፊቱን አጥቁሮ ‘ይህንን ስሰማ፡ ያልወለድኩት አባባ ቢለኝ አፌን…’ብሎ አባባሉን ሳይጨርሰው ተወው!

 

እስቲ እነዚህን በደም፣ በባህሪም ተመሳስለው የኢትዮጵያን ስፖርት አካላት ለዘረፋና ጥቅማ ጥቅሞች ማሰባሰቢያ የተጠቀሙባቸውን ግለሰቦችና ኃላፊነታችውን እንዘርዝርላችሁ:-

  1ኛ፣   አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም   የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚደንት

  2ኛ፣   አቶ ኪሮስ ገብረ ስቀል   የኢትዮጵያ ቴክዋንዶ ማህበር ፕሬዚደንት

  3ኛ፣   አቶ ኪሮስ ሃብቴ   የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ማኅበር ፕሬዚደንት (የሮቤል አባት)

  4ኛ፣   አቶ ተስፋዪ አስገዶም   የኢትዮጵያ የጅ ኳስ ፊደሬሽን ፕሬዚደንት

  5ኛ፣   አቶ ረዘነ በየነ   የኢትዮጵያ ብስክሌት ፊደሬሽን ፕሬዚደንት

  6ኛ፣   አቶ ተክለወይኒ አሰፋ   እግር ኳስ ምክትል ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት

  7ኛ፣   ግማዊት ግርማይ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዋና ጸሃፊ

  8ኛ፣   ግደይ ገብረመድህን የኢትዮጵያ ቼስ ፊደሬሽን ፕሬዚደንት

 

ተዛማጅ ምስክርነቶች:

With crossed arms on the forehead toward the finish line, Rio Marathon Silver Medalist Feyissa Lelisa demands freedom for Ethiopians from TPLF barbaric repression!

Ethiopian swimmer displays a very unathletic paunch for 100 metres… And finishes last by half a lap

ሚሚ ስብሃቱ ሪዮ ከረመች – ለአትሌቶች ገንዘብ የለም ተብለው እንዲቀሩ ሲደረግ

Ethiopian delegation returns from Rio without marathon runner Feyisa Lilesa
 

%d bloggers like this: