ዘራፊውና ነፍሰ ገዳዩ ሕወሃት ዙርያውን ተወጠረ!    የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ ችግሮችን ሊያጠራ እንደሚገባ የአትሌቶች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አሳሰበ! በአንድ ሣምንት ውሳኔ ላይ ካልተደረስ “መሄድ ያለብንን ርቀት ድረስ እንሄዳለን፤ ለዚህም ተዘጋጅተናል!”             እንኳን ለዚህ አደረሰን፣ መነቃቃት በኢትዮጵያ!

25 Aug

የቀድሞ ታዋቂ አትሌቶች አትሌት ኃይሌ ገብረእግዚአብሔር፡ አትሌት ገዛኽኝ አበራ፥ አትሌት ገብረ እግዚአብሔር ገብረማርያም፥ አትሌት ሻምበል ቶሎሣ ቆቱን አሠልጣኝ ኮማንደር አበበ መኮንንበቁጣ በግነው ስብሰባ በአንድ ሣምንት ውስጥ ካልተጠራና ውሳኔ ላይ ካልተደረስ “መሄድ ያለብን ርቀት ድረስ እንሄዳለን፤ ለዚህም ተዘጋጅተናል” (Credit Fana)


 

“We want a general meeting of the Ethiopian Athletics Federation within a week to take the appropriate decisions. If not, we would go the distances it would take us to see the results Ethiopia needs. And we are prepared for what it takes!”, says the provisional coordinating committee of Ethiopian athletes.
 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 19፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ ችግሮችን ሊያጠራ ይገባል እንደሚገባ የአትሌቶች ጊዜዊ ኮሚቴ አስተባባሪ አሳሰበ።

ኮሚቴ በዘንድሮው የሪዮ ኦሎምፒክ ሀገራችን ደካማ ውጤት እንደታዝመዘገብ ምክንያት የሆነው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ የአሰራር ክፍተት ነው ብሏል።

ከነባርና ታዋቂ አትሌቶችና አሰልጣኞች የተውጣጣው ጊዜያዊ ኮኒቴ ዛሬ በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም፥ በሪዮ ኦሎምፒክ የተገኘው ውጤት እንዳሳዘነውና ለውጤቱ መጥፋት ዋነኛው ምክንያት የአትሌቶች እና የአሰልጣኞች ምርጫ እንዲሁም የአሰለጣጠን ችግር እንደሆነ ጊዜያዊ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

የጊዜያዊ ኮሚቴዉ ሰብሳቢ አትሌት ሃይሌ ገላሴ ፌዴሬሽኑ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ ችግሮችን ሊያጠራ ይገባል ሲልም በመግለጫው ላይ ተናግሯል።

አሁን ያሉት አመራሮርች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ሀላፊነታቸውን እንዲያነሱ የጠየቀው ኮሚቴው፥ ፌዴሬሽኑ በሙያ ለመምራት ብቃቱ ላላቸው እንዲያስረክብ ጠይቀዋል።

ከክልሎች የተወከሉ የፌዴሬሽኑ አባላትም ለመጡበት ክልል በማሳወቅ ሃላፊነታቸውን በአስቸኳይ እንዲያነሱ ጥሪ አስተላልፏል።

ከክልሎች የሚወከሉም ይሁን ፌዴሬሽኑን በአጠቃላይ የሚመሩ ሰዎች በአትሌቲክስ ውስጥ ያለፉ እና አትሌቲክሱን የሚያውቁ መሆን እንዳለበት ኮሚተ ገልጿል።

በዚህም ክልሎችም ተወከያቸውን በሚልኩበት ጊዜ በአትሌቲክሱ ውስጥ ያለፈ እና ስለ አትሌቲክ በቂ እውቀት ያለው መሆን አለበት ስል ኮሚቴው አሳስቧል።

ጉዳዩ ውስጥ መግንስት መግባት የለበትም፤ መንግስት በዚህ ጉዳይ ጣልቃ ከገባ ሀገሪቱን ከዓለም አቀፍ መድረኮች ሊያሳግድ ይችላል ያለው ኮሚቴው፤ ጉዳዩን እኛው መፍታት አለብን ብሏል።

ሆኖም ግን ፌዴሬሽኑ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ አስሸኳስ ስብሰባ በመጥራት ከውሳኔ ላይ ካልደረሰ መሄድ ያለብን ርቀት ድረስ እንሄዳለን፤ ለዚህም ተዘጋጅተናል ሲል አስጠንቅቋል።

በጉዳዩ ዙሪያ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ምላሽ የጠየቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን፥ መግለጫ እሰጣለው ለጊዜው የምለው የለም ብሏል።
 

%d bloggers like this: