ሕወሃት በሪዮ ኦሊምፒክ ለተገኘው አሳፋሪ ውጤት በአትሌቶች ጊዜያዊ ኮሚቴ ጥያቄ ሲቀርብበት የመጠየቅ ሕጋዊ መብት የላችሁም ብሎ የቀዣበረው ቅጥፈት! ይሉኝታና ስብዕናችን ምን ሆነ ይሆን?

28 Aug

በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)
 

የኢትዮጵያ አትሌቶች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽንን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ ችግሮችን ሊያጠራ ይገባል የሚል ጥያቄ ባቀረበ ማግሥት፣ ኮሚቴውን ሕጋዊ መብትም ሆነ ውክልና የላችሁም በማለት የሠጠው መልስ ሕወሃት ሃገራችንን የፈለኩትን ላደርጋት እችላለሁ፤ እፈንጭባታለሁ የሚል መሆኑን ጋሃድ አድርጓል፡፡

 
የጊዜያዊ ኮሚቴዉ ሰብሳቢ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ ፌዴሬሽኑ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ ችግሮችን ሊያጠራ ይገባል ማለቱ አስመልክተን አርብ ዘግበን ነበር

በተጨማሪም፡ ኮሚቴው ፌዴሬሽኑ በአንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት ከውሳኔ ላይ ካልደረሰ መሄድ ያለብን ርቀት ድረስ እንሄዳለን፤ ለዚህም ተዘጋጅተናል ቢልም፣ ፌዴሬሽኑ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የኮሚቴውን ጥያቄ ሕጋዊ መሠረት የሌለው በማለት አጣጥሎታል።

ለችግሩ መንስዒ የሆነው የአትሌቶቻችን ውጤት አለመሳካት ብቻ ሳይሆን፡ የልዑካኑ ተልዕኮ ራሱ የሕወሃት አባሎች ሠርግና ምላሽ መደረጉ ዜጎችን አስቆጥቷል። ይሁን እንጂ የተመዘገበውን ውጤት ተከትሎ “የአትሌቶች ጊዜያዊ ኮሚቴ ፌዴሬሽኑ አስቸኳይ ጉባኤ ጠርቶ አዲስ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እንዲዋቀር ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም፤ ኮሚቴው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የመጥራት ሕጋዊ መብት የለውም” ብለዋል የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ አለባቸው ንጉሴ።

በተለይም ደግሞ 84 ብሄረሰቦች ባሉባት ሃገር ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ የኦሎምፒክ ተሳትፎ ታሪክ ውስጥ ከሥር ስማቸው የተዘረዘረው ስምንት የሕወሃት አባሎች፡ ብሔራዊ ልዑካን መርተው እንዲሄዱ መደረጉ፡ ውጤቱ እንደ ሮቤል ዐይነት ዋናተኛ ልኮ ሃገርን መሣለቂያ ከማድረጉ ባሻገር፡ የስፖርት ልዑካን መሪዎቹ በሃገር ገንዘብ የሚበሸበሹበትና የዝሙት አስረሽ ምቺው የሚፈጸምበት ተልዕኮ መሆኑ አሳፋሪና ብሔራዊ ክብርን የሚጎዳ ሆኖአል። እነርሱም፤

1ኛ፣ አቶ ብርሃነ ኪዳነማርያም የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚደንት

2ኛ፣ አቶ ኪሮስ ገብረ ስቀል የኢትዮጵያ ቴክዋንዶ ማህበር ፕሬዚደንት

3ኛ፣ አቶ ኪሮስ ሃብቴ የኢትዮጵያ ውሃ ዋና ማኅበር ፕሬዚደንት (የሮቤል አባት)

4ኛ፣ አቶ ተስፋዪ አስገዶም የኢትዮጵያ የጅ ኳስ ፊደሬሽን ፕሬዚደንት

5ኛ፣ አቶ ረዘነ በየነ የኢትዮጵያ ብስክሌት ፊደሬሽን ፕሬዚደንት

6ኛ፣ አቶ ተክለወይኒ አሰፋ እግር ኳስ ምክትል ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት

7ኛ፣ ግማዊት ግርማይ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዋና ጸሃፊ

8ኛ፣ ግደይ ገብረመድህን የኢትዮጵያ ቼስ ፊደሬሽን ፕሬዚደንት

ብሔራዊ ቁስላችንን በጨው እንደማሸት ያህል፡፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ አለባቸው ንጉሴ በሰጡት መግለጫ – ፋና እንደዘገበው – በሪዮ ኦሎምፒክ አንድ ወርቅ ብቻ መገኘቱ ያነሰ ቢሆንም በአጠቃላይ ስምንት ሜዳልያዎችን መሰብሰባችን ጥሩ ስኬት ነው ማለታቸው፣ ሕወሃት ውጤቱ ዝቅተኛ ነው በማለት ገና ከማለዳው ያጣጣለውን የሚገለብጥ መሆኑ፡ ያለው አስተዳደር በአንድ በኩል ሲያዝ በሌላው ለማምለጥ የሚያደርገው ሙክራ እጅግ አሳፋሪ መሆኑን አሳይቷል።

አቶ አለባቸው ንጉሴ በሪዮ ከዚህ ቀደሞቹ ኦሎምፒኮች በተሻለ በተለያዩ ውድድሮች በርካታ አትሌቶችን አሳትፈናልም ነው ያሉት፤ ይሁንና ከውጤት አንጻር ግን ምን እንዳተረፈ የሚናገሩት ነገር አልነበራቸውም።

ለዚህ ብልግናቸው የሕወሃት ሰዎች ተጠያቂ ልንደረግ አይገባም በማለት የሠጡትን አሳፋሪ ምላሽ፥ የኢትዮጵያ ሕዝብ እበክሮ ሊታገለው ይገባል። በጊዜያዊው ኮሚቴ የቀረበውንም ጥያቄ በመደገፍ የሕወሃትን ወራዳነት ማጋለጥና መታገል ይኖርበታል።

የሕወሃት ተወካይም አሳፋሪውን መልስ ለመሰጠት የተጠቀመባቸውን ነጥቦች በቅርብ ብንመለከት ምን ያህል አናሳ አስተሳሰብ እንደሚገዛቸው እንደሚከተለው እናመላክታለን፦

አንደኛ አቶ አለባቸው ንጉሤ የሰጡት መልስ እንዲህ ይላል፦-

“የኮሚቴው አባላት ለኢትዮጵያ ትልቅ ውለታ እንደሰሩ እናምናለን ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ ነገር ግን [ጊዜያዊ]ኮሚቴው እያቀረበው ያለው ጥያቄ በአትሌት ስለሺ ስህንና መሠረት ደፋር የሚመራውን የአትሌቶች ማኅበር አሳንሶ ማየትን ያመላክታል ብለዋል።” ጊዜያዊ ኮሚቴ ያነሳው ነጥብ ግን ይህ አልነበረም!

 

ሁለተኛ ይህ ፉርሽ እንደሆነባቸው ሲገነዘቡ፡ የአልሞት ባይ ተጋዳይ መከራከሪያ አድርገው የቀረቡበት ነጥብ እንደሚከተለው ‘ተውን እባካችሁ ለጥቂት ጊዜ እንጋጥበት የሚል ይመስላል፡ –

“የሥልጣን ጊዜያችን ህዳር 24 ነው የሚጠናቀቀው። እስከ ህዳር 24 ሳንጠብቅ መስከረም ወይም ጥቅምት ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔ እንጠራለን፤ በድጋሚ ስለመመረጥ እያንዳንዱ በግሉ የሚወስነው ነው” ሲሉም አክለዋል።

 

እንደገና ደግሞ እጥፍጥፍ ይሉና ለወደፊቱ ዕድል ስጡንና እናሻሽላለን ይላሉ እንደሚከተለው፡ –

“በአጠቃላይ በሪዮ የተመዘገበው ውጤት የኢትዮጵያ ህዝብ ከሚጠብቀው አንፃር አነስተኛ መሆኑን እናምናለን፤ ህዝቡን ለመካስም ጥረት እናደርጋለን” ነው ያሉት።

 

ሶስተኛ፣ ነገሩን ደግሞ ድብልቅልቅ አድርገው፣ ሕጋዊ ሥልጣንና ውክልና የለውም ያሉትን ጊዜያዊ የአትሌቶች ኮሚቴ “ጋርም ተቀራርቦ ለመነጋገር በራችን ክፍት ነው” ይላሉ። እውነቱን ነገር አቋማቸው ዝብርቅርቅ ማለቱ ብቻ ሣይሆን፡ ‘የማርያምን ምን የበላ…’ እንደሚባለው አቋማቸው ምን እንኳ እንደሆነ ለማወቅ እጅግ ግራ የሚያጋባ ሆኖአል።

አራተኛ፣ ሕወሃት እንደተለመደው እውነትን በእውነት መከላከል ሲያቅተው ወደ ውንጀላና ስም ማጥፋት ዘመቻ ስለሚሄድ፡ አቶ አለባቸውም የሚከተለውን ከጉዳዩ ጋር ባልተያያዘ ዘባትለዋል፦

“አንዳንድ አትሌቶች በህገወጥ መንገድ ግብር ሳይከፍሉ መኪና ከውጭ ሀገር እንደሚያስገቡ ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል። አትሌቶች በየትኛውም አለም ተወዳድረው ሲያሸንፉ መኪና በነፃ እንዲያስገቡ ይፈቀድላቸዋል።
 

አምስተኛ፣ ነገር ግን ሳያሸንፉ በሀሰተኛ መረጃ መኪና ያስገቡ አትሌቶች ጉዳያቸው በፀረ ሙስና ኮሚሽን እየታየ መሆኑን ነው ፕሬዚደንቱ ያብራሩት። በስፖርቱ ዓለም ምንም ዐይነት ተሳትፎ የሌላቸውን ሰዎች በአትሌቶች ቪዛ ወደ ውጭ ሀገር የሚያዘዋውሩ አካላት ጉዳይም እየተጣራ ነው ብለዋል።”

 

ለነገሩ የሕወሃት ወንጀሎችና የጸረ ሙስና ኮሚሽን የዐይጥ ምስክርነት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ተሠውሮበት እንደማያውቅ በዚሁ እናሳውቃችሁ!

ታዲያ ይህ ሕወሃት እንኳን መደርመስ፣ ገሃነምስ መቃጠል ያንሰዋል የሚል መርቻውን ያቅርብ!
 

ተዛማጅ:

ዘራፊውና ነፍሰ ገዳዩ ሕወሃት ዙርያውን ተወጠረ! የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጠርቶ ችግሮችን ሊያጠራ እንደሚገባ የአትሌቶች ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አሳሰበ! በአንድ ሣምንት ውሳኔ ላይ ካልተደረስ “መሄድ ያለብንን ርቀት ድረስ እንሄዳለን፤ ለዚህም ተዘጋጅተናል!” እንኳን ለዚህ አደረሰን፣ መነቃቃት በኢትዮጵያ!
 

%d bloggers like this: