የኦሮሞ የዜና ጣቢያ እንደዘገበው፣ ጸረ-ወያኔ ኢትዮጵያውያን አካባቢዎችን የመቆጣጠር እርምጃዎች እየወሰዱ ነው!

5 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ጥቅምት 2/2016 በማን አለብኝነት ሕወሃት ከ700 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ጥፋት ምክንያት መሆኑ ምን ጊዜም አይዘነጋም። ይህም የሕወሃቶች አረመኔያዊ ተግባር፡ ሃገሪቱን ከዳር እስከዳር አስቆጥቷል።

ከዚህ በፊት ባልታየ ሁኔታ ከተለያዩ ብሄረስቦች የተውጣጡ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በየሥፍራው አጋዚንና አዛዦቻቸውን እንዲሁም የጸረ-ሕዝቡን የሕወሃትን ፖለቲካ በማውገዝ ላይ ናቸው።

በጂማ የሚገኙ የአማራና የኦሮሞ ተማሪዎች፡ በጋራ አመራር ሕወሃትን ለመቃወም ስምምነት ላይ ደርሰዋል። በአካባቢውም እሥር ቤቶች ተቃጥለው – በፖለቲካ ጉዳይ የታሠሩን ጨምሮ – እሥረኞች ተለቀዋል።

በኦሮሚያ በተለያዩ ወረዳዎች ደግሞ፣ ሕወሃት በዘረፋ የመሠረታቸውን ንብረቶች ማወደሙ በሠፊው ተጠናክሮ ረቡዕ ዕለትም ቀጥሎ ውሏል። ዝርዝሩን ኦኤምኤን ካጠናቀረው ቪዲዮው መመልከት ይቻላል። የመንግሥት፣ የሕወሃት ተባባሪ የሆኑ ግለሰቦች ድርጅቶች ማለትም ፋብሪካዎችን ተንቀሳቃሽ ንብረቶች (ትላልቅ መኪናዎች) ከዚህ አላመለጡም።

 
ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ ዋዜማ ራዲዮ ላይ ጃዋር መሃመድ “የኦሮሞ የመብት ትግል በቅርቡ ወደ አዲስ ምዕራፍ ይሸጋገራል…ከአዳዲስ ዕቅዶቹ መካከል የኦሮሚያን የነፃነት ቻርተር ማዘጋጀት ብሎም በሽግግር መንግስት ምስረታ ወቅት የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን ማድረግ ይገኝበታል “ማለቱ አነጋጋሪ ሆኖአል።

ዛሬ እጅግ በሚዘገንን መንገድ በየሥፍራው በሕወሃት ኃይሎችና ካድሬዎች ኢትዮጵያውያን መረሸናቸው ብቻ ሳይሆን፡ ከተማዎችም እየፈራረሱ ናቸው። በሌላ መልኩ ሲታይም፣ ቢያንስ ቢያንስ ትግራይ ውስጥ በየሁለትና ሶስት ወሩ ትምህርት ቤቶች ይቋቋማሉ፤ የጤና ጣቢያዎች ይስፋፋሉ፤ አዳዲስ ፋብሪካዎች ይቋቋማሉ።

በቀረው ኢትዮጵያ ውስጥ ግን በሕወሃት ካድሬዎችና ሠራዊቱ ከተሞቻችን በየሥፍራው እየተመዘበሩና እየተናዱ ናቸው። ባንጻሩ መቀሌ ለነዋሪዎቿ ለትግራውያን ጭምር ተዓምር መሆኗን ትግራዉያን ራሳችው ይናገራሉ። ለዚህም በአማራ ታጋዮች ተዘጋጅቶ በዩቱብ የተለቀቀውን ከዚህ በታች ያለውን ዶኪመንታሪ ቪድዮ ይመልከቱ።


 
ለብዙ ዓመታት ሕወሃት ትግራይን በመስኖ ጭምር እያለማ ባለበት ሁኔታ – የትግራይን ሕዝብ ጥፋተኛ ለማስመሰል ባይሆንም – በትግራይ አሰተዳደር ትዕዛዝ ለትግራይ አክሳዮች የጎንደርን ደን ሲጨፈጭፉና ሲያከስሉ መኖራቸውን የክልሉ አስተዳደር ሣይሆን አሁን በቅርቡ ሕዝባዊ ትግሎ ነው ያቆመው።

በቅርቡም፥ ኢሣት እንደዘገበው፥ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በአንድ ኮለኔል የሚመሩ አንድ ሺህ የሚሆኑ የትግራ ተወላጆች ወርቅ እናወጣለን ብለው በጉልበት (በሕወሃት ድጋፍና አበረታችነት) መሥፈራቸው፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ሕወሃት እስካለ ድረስ የዜጎች ስላምና ደህንነት የተሟላና የተረጋገጠ እንደማይሆን ግልጽ ከሆነ ሰንብቷል።

ለዐባይ ግድብ ሥራ ደኖችን መመንጠር አስፈላጊነቱ ቢታመንበትም፡ በምርጫ ግን የሕወሃት ሰዎች በከሰል እምራችነት እንዲጠቀሙበት መደረጉ ሲታወስ፡ የትግራይን ሕዝብ ጥፋተኛ ለማስመሰል ባይሆንም፡ ይህ ዘረኝነት ውስጣዊ ይዘቱ የሕወሃት ጸረ-ኢትዮጵያዊነትም እንዳለበት መዘንጋት የለበትም።

ከላይ ስለ ጁሃር የጠቀስኩት ድንገተኛና ለብዙዎች አስደንጋጭ መሆኑ በመጠቆም ነው መሰል፡ ጃዋር “ዋዜማ ራዲዮ በቅርቡ ያደርኩትን ንግግር ከ Context ውጪ ወስዶ አነጋጋሪ አድርጎታል” በማለት ምን ማለት እንደፈለገ እንደሚከተለው አብራርቶታል

“1) የኦሮሞ ሲቪክ እና ፖሊቲቻል አመራር በቅርቡ በመሰብሰብ የኦሮሞ ቻርተር ያዘጋጃል። ይህ ሁሉንም ዮሮሞ አመራሮች ሊሳማማ የሚችል አነስተኛ ፕሮግራም ማለት ነው

2) ወያኔ እየወደቀ ስለሆነ ከዚያስ ምን መሆነ አለበት በሚለው የፖሊሲ የስትራቴጂ ጉዳዮች ላይ የሚመክር ኮንፈረንሰ በቅርቡ በኦሮሞ የህግ ባለሟያዎች ማህበር ሎንዶን ላይ ተጠርቷል (( ለመላው ኢትዮጲያም እንዲህ አይነት Social Contact ያስፈልጋል፤ እያንዳንዱ ማህበርሰብ መጀመሪያ በውስጡ እንዲህ አይነት ስምምነት ፈጥሮ ቢቀርብ ይሻላል በማለት ባለፈው ኢትዮትዩብ ባዘጋጀው ፎረም ላይ መናገሬ ይታወስ)

3) የኦሮሞን ህዝብ መብት እና ጥቅም በዘላቂነት ለማስከበር ከፖሊቲካ ፓርቲዎች ወገንተኘት ነጸ የሆነ ወታደራዊ ተቋም መቋቋም አለበት
ይህ አዲስ ንግግር ሳይሆን ላለፉት ብዙ ወራት እና አመታት በኦሮምኛ፣ አማርኛ እና እንጊሊዚኛ ያቀርብኩት ንግግር ነበር። ይህን ስናገርም የንግግሩን ጭብጥ ደጋግሞ ለሰማ ማህበረሰብ ስላነበር ዝርዝር ውስጥ አልገባሁም። ዋዜማ ወይ የትርጉም ችግር ነበረበት ወይም ከኮንቴክስቱ ውጪ ነው የተረዳው መሰለኝ።”

በአሁኑ ወቅት ካለው የበሰበሰ የዘር ፖለቲካ ሃገሪቱን የማለቀቁ ሥራ በአንድ በኩል እንደተጠበቀ ሆኖ ሳለ፡ በሌላ በኩል ደግሞ በዚህች ደሃ ሃገር እነዚህ የሚወድሙት ንብረቶች ወደ ሕዝቡ ተሸጋግረው ሊጠቀምባቸው ሁኔታ እስኪመቻች ድረስ የሚታሠሩበትን በአስተዳደሩም ሆነ ከሕወሃት ጋር ተባባሪ የሆኑት በባለሃብቶች እንዳይጠቀሙበት ተደርጎ ተመዝግበው ሊጠበቁ የሚችሉበት ሁኔታ መፍጠር ቢቻል፣ ለነገየቱ ነጻይቱ ኢትዮጵያ በረከት ይሆናሉ።

የዚህ ዐይነቱ አሠራር፣ በትክክልም በንብረት መውደም ምክንያት ትግሉን እንደ አፍራሽ አድርገው የሚመለክቱትን ወገኖች በማረጋጋት ደጋፊ ሊሆኑ የሚችሉበት ሁኔታ መፍጠር ያስችል ይሆናል።

ሕወሃቶች የተካኑት የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ በመሆኑ፡ የሕዝቡን የፖለቲካ ግብግብ ለማጣጣል የፖለቲካ ቀውሱ በሃገሪቱ ኤኮኖሚ ምንም ዐይነት አፍራሽ ተጸዕኖ አልፈጠረም ይላሉ፣ ሪፖርተር እንደዘገበው። ይህ አባባላቸው ትክክል አይደለም። ኢኮኖሚውን እየጎዳ ነው።

ታጋዩ ሕዝብም በዚህ በእነርሱ አባባል ሳይደለል የሚፈርሰውና የሚቃጠልው ንብረት መዋዕለ ንዋይ የፈሰሰበት ሆኖ ዛሬ ተጠቃሚዎቹ ሕወሃቶችና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ብቻ መሆናቸው ሳይገታን፡ ሕዝቡ አሁንም ሆነ ወደፊት ተጠቃሚ ሊሆንባቸውን ሁኔታ በማሰብ ነጻ ማውጣት ሰለሚቻልበት ማሰብ ይገባል።

ይህ ማለት ትግሉ ይቁም፣ ወይንም የዘራፊዎቹ ንብረት አይያዝ ማለት አይደለም።

%d bloggers like this: