አምስቱ የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሕወሃትን ለመጣል የወቅቱ አንኳር ትኩረቶች

8 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

ከዚህ በታች የሠፈሩት አምስት የድርጊት አቅጣጫዎች በቀጥታ ሙሉ ለሙሉ ቃል በቃል የተወሰደ ባይሆንም፣ ፍሬ ነገሮቹን በደንብ ያስጨባል ብለን እናምናለን።
==============
 

አምስቱ አንኳር ትኩረቶችz

ሀ. ጠላታችን ዛሬ ሃገሪቱ ፊት ለተጋረጠው ችግር ሰላማዊ መፍትሄ የመሻት ፍላጎት ስለሌለው፣ በሕዝቡ ወገኖች በኩል የተያያዝነው የፖለቲካ ትግል መሆኑን ሳንዘነጋ፣ የሕወሃትን የጉልበት አካሄድ ማምከን የምንችል መሆናችንን በተግባር ማሳየት አለብን

ለ. በየአካባቢው የተመሠረቱ የሕዝባዊ እምቢተኝነት ኮሚቴዎች በየጊዜው በሚለዋወጥ የትግል ስልት እየተመሩ፣ በወያኔ/ኢሕአዴግና ቡችሎቻቸው ንብረቶች፡ የአፈናና የመገናኛ መዋቅሮች፣ የገንዘብ ምንጮችና በአጠቃልይ በሥርዓቱ ላይ የኤኮኖሚና ሥነ ልቦና ጫን በሚፈጥሩ ዒላምዎች ላይ ማነጣጠር አለብን። በመላው ሃገሪቱ ክፍል የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ተናበው በተመሳሳይ ጊዜ እንዲካሄዱ ማድረግ ያስፈልጋል። ይህም ትግሉ መላው ሃገራችንን እንዲያዳርስና ጠላትምከፋፍሎ እንዳይመታ ለመከላከል ያስችላል።

ሐ. በሁሉም አካባቢዎች ወታደሮች፡ ፖሊሶችና የሥርዓቱ አገልጋዮች የነበሩ ግልሰቦች ሥርዓቱን እንዲከዱ ማበርታታና ሲመጡም በክብር ተቀብሎ ለትግሉ አስተዋጽኦ የሚደርጉበትን ሁኔታ ማመቻቸት ያስፍልጋል።


 
መ. ወያኔና አጋሮቹ እርስ በእርስ ከፋፍለው ሊያዋጉን በየጊዜው ስለሚሞክሩ፣ በሕዝቡ ወገኖች በኩል የሰለማዊ ትግል ደጋፊዎች እንጄ እርስ በእርስ የማንባላ መሆናችንን ለማሳየት ትግላችን የሚያተኩረው በሰላማዊ ሕዝብ ላይ እንዳልሆነ በተግባር ማሳየት ይኖርብናል።

ሠ. ከወያኔ በኋላ የሚመጣው የግለሰቦች ለውጥ ሳይሆን የሥርዓት በመሆኑ፣ በሕንጻ ሥራ ብቻ ሳይሆን የሚገለጸው በአስተሳሰብና በመንፈስም የተሸጋገረ እንደሆነ ማሳየት ያስፈልጋል። ለዚህም የዴሞክራሲ ኃይሎችና ሲቪክ ድርጅቶች የጋራ አመላከት፣ የተቀናጀ አመራርና ድርጅታዊ መዋቅር መፈጠር ስለሚያስፈልግ፣ ይህንኑ በተመለከተ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በቅርብ እየተሠራ ስለሆነ በቅርብ ዕውን ይደረጋል።
 

ተዛማጅ (?)

An Oromo Leadership Convention: The Oromo National Charter of Freedom, Justice and Human Rights
 

%d bloggers like this: