በአስቸኳይ ጊዜ ሕግ ስም አያሌ ዜጎች በሕወሃት እየታፈኑ እየተገደሉ ነው! የወጣቱን መንፈስ ግን አልሰበረውም!

13 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

በምስራቅ ሸዋ ዞን ሁከት ፈጣሪዎችን ለህግ የማቅረብ ተግባር እየተከናወነ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በምስራቅ ሸዋ ዞን ባለፈው ሳምንት ሁከት በመፍጠር ውድመት ያደረሱ ግለሰቦችን ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ለህግ የማቅረብ ተግባር እየተከናወነ መሆኑ ተነግሯል።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደረጀ ሙላት ለኢዜአ እንደገለጹት፥ በዞኑ 10 ወረዳዎችና አንድ የከተማ አስተዳደር የሚገኝ ሲሆን ከአንድ ወረዳ በስተቀር በሁሉም ላይ ከአነስተኛ እስከ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል።

በዞኑ የእርዳታ እህል የጫኑ ተሽከርካሪዎች፣ የአስተዳደር ጽህፈት ቤቶች፣ በመንገድ ስራ ላይ የነበሩ ማሽነሪዎች፣ ሆቴሎች፣
የግለሰብ መኖሪያ ቤቶችና የተለያዩ ዘመናዊ የእርሻ ልማቶችና ሌሎችም መሰረተ ልማቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በአሁኑ ወቅትም በዞኑ ሰላምና መረጋጋት የሰፈነ ሲሆን ይህንኑ አጠናክሮ ለማስቀጠል ከህብረተሰቡ ጋር እየተሰራ ነው።

ከዚህ ጎን ለጎን እነዚህን ሁከት ፈጣሪ ግለሰቦችም ለህግ የማቅረብ ስራ ከህዝቡጋር በመሆን እየተካሄደ ይገኛል።
==============
 

17 individuals charged for recruiting, training members after receiving money from OLF leaders

Addis Ababa, October 12, 2016 (FBC) –17 individuals suspected of recruiting and training members for the Oromo Liberation Front (OLF), a group designated as a terrorist organization by the House of People’s Representatives, have been charged.

The suspected individuals, including first defendant Diribsa Damte and second defendant Segni Dugassa are residents of Addis Ababa city, Bishoftu, Sebeta, Jigjiga and other towns in Oromia Regional State.

According to the charges filed against them, they tried to recruit and train members for OLF after becoming members of the Front and by making telephone contact and receiving money from senior heads of the Front living in the United States.

They were also charged for trying to change Ethiopia’s government by armed struggle as well as to demolish the country’s Constitution, political, economic and social institutions by recruiting members and organizing them locally.
===============
 

በአርሲ ነጌሌ ወረዳ ሁከት በመፍጠር በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱ የጥፋት ሀይል አባላትን ህዝቡ እያጋለጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምእራብ አርሲ ዞን አርሲ ነጌሌ ወረዳ ሁከት በመፍጠር በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱ የጥፋት ሃይል አባላትን ህዝቡ እያጋለጠ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅትም አካባቢው ወደ መረጋጋትና ሰላም የተመለሰ መሆኑን ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በስፍራው ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

ምእራብ አርሲ ዞን አርሲ ነጌሌ ወረዳ በሰሞንኛ ሁከት ተጠቂ ከሆኑ አካባቢዎች አንዷ ነች።

በወረዳዋ ሁከት ፈጣሪ ሀይሎች ከፍተኛ የሆነ ውድመት ያደረሱ ሲሆን፥ ከነዚህ ውስጥ ሶስት ወረዳዎችን ተጠቃሚ የሚያደርገው የውሃ ፕሮጀክት ይገኝበታል።

የውሃ ፕሮጀክቱ እስክ 300 ሚሊየን ብር በሚጠጋ ወጪ የተገነባ ሲሆን፥ በቃጠሎው ሊዘረጉ የተዘጋጁ ቱቦዎች፣ የፕሮጄክቱ ማስፈጸሚያ ቢሮዎችና ተሽከርካሪዎች ወድመዋል።

አካባቢው ከፍተኛ የሆነ የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ጥያቄ ሲቀርብ የበረ ነው፤ ነገር ግን እነዚህ የጥፋት ሀይሎች ለህብረተሰቡ የተሰራውን የውሃ ፕሮጀክት እንዳልነበር አድርገው አውድመውታል።

ቁጥራቸው በርከት ያሉ የህብዝ ማመላለሻ አውቶብሶች፣ የንግድ ተሽከርካሪዎች እና የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች ሁከት ፈጣሪዎቹ ባደረሱት ጥቃት ሙሉ በሙሉ ተቃጥለዋል።

እንዲሁም ከአርሲ ነገሌ ከተማ ውጭ በሚገኙ ሌሎች ቀበሌዎች ላይ የደረሰው ጥቃት ተጠቃሽ ነው።

በአርሲ ነገሌ ወረዳ ውስጥ ከሚገኙ 39 ቀበሌዎች ውስጥ በሁከት ፈጣሪ ሀይሎች 20 ቀበሌዎች ሙሉ በሙሉ ከነሰነዳቸው የወደሙ ሲሆን፥ በአሁኑ ጊዜ ቀበሌዎቹ ለህብረተሰቡ የሚሰጡትን አገልግሎት ለማቆም ተገደዋል።

በአካባቢው ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ ሁለት የጤና ኬላዎች በሁከት ፈጣሪ ሀይሎች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።

ከዚህ በተጨማሪም 17 የማዳበሪያ መጋዝኖች፣ 17 የሸማቾች ማህበር መጋዝኖች እና ሌሎች የመንግስት ተቋማት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

በአሁኑ ጊዜ በሁከቱ የተሳተፉ ሀይሎች በህብረተሰቡ እየተያዙ መሆኑም የወረዳው አስተዳዳሪዎች ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

በቀጣይም እንዚህ አካላት ላይ አስፈላጉው ማጣራት ተደርጎ ለህግ እንዲቀርቡ ይደረጋል ሲሉም ነግረውናል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከመታወጁ በኋላ በአሁኑ ጊዜ በአካባቢው አንጻራዊ እና የተረጋጋ ሰላምዋን እያገኘት መምጣቷን የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ባልደረባ በአካባቢው ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

በስፍራው ወደ ሀዋሳ፣ አዲስ አበባ እና ሌሎች አካባቢዎች የሚንቀሳቀሰሱ ተሽከርካሪዎችም ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዎች ተመልሰዋል።
================
 

More killings

#OromoRevolution ALARM: The regime is now resorting to on spot execution of those they arrest. In Arsi Sadiqa district, a member of the opposition Oromo Federalist Congress, Alemu Kenna was arrested and executed in front of family and neighbors.
================
 

Robbery and rape under the cover of state of emergency

#OromoRevolution State of Emergency to facilitate robbery? Reports from across Oromia reveal that the Agazi army is breaking into homes that appear well kept and then take any thing valuable they can see; jewelry, money, souvenirs, and even goats and cows. They stop people in car and on foot and take their cellphones and wallets. Is this to further frustrate people or the regime cannot pay the soldiers so they let them on go on looting like the medieval time armies?
================
 

The bravery and over all response of the youth is fascinating: Arba Minch University, despite the TPLF ‘marshal law’!

================
 

11 persons killed in East Arsi

#OromoRevolution The Agazi army today killed 11 people in Jawi village, Roobe district in East Arsi. Most of the victims are said to be women who tried to intervened using the traditional siinqee stick to prevent a clash between the soldiers and protesters. The soldiers sprayed bullet on them despite the women clearly showing them the stick and white sheet as sign of peace. Well I am not shocked since Irreechaa we know whats most sacred to us is scary to them.
===============
 

%d bloggers like this: