የሃገራችንን ዕጣ ፈንታ ዜጎቿ በግለሰብና በቡድን ሊወስኑ ይገባል፣ የሥልጣን ቋማጮች ሳይሆኑ!

30 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
የአዘጋጁ አስተያየት፡
 
የአንድ ሕዝብ መተሳሰርም ሆነ መለያየት የታሪክና የባህል ጉዳይ በመሆኑ፡ መገንጠልን መከታ የሚያደርጉ ግለሰቦችና ቡድኖች በርጓሮ በር ሥልጣን ፈላጊዎች መሆናቸውን በሚገባ ማስተዋል ይገባል።

ለነገሩ ሕወሃትም ይህንኑ ማለት ይወዳል። የሕወሃት አባባል የሚመነጨው ግን እስከ ክርስቶስ ዳግም ምጽዓት በሥልጣን ጥቂቱን የብኄረሰቡን ሰዎች አስከትሎ ገዥ ሆኖ የመኖሪያ ዕቅድ ስላለው ነው።

ከእንግዲህ የሃገራችን ሉዓላዊነትና አንድነት በጠንካራ መሠረት ላይ ሊያርፍ የሚችለው፡ ሊገነባ የሚገባው በእያንዳንዱ ዜጋና በማኅበራዊ ስብስቦች (ብኄረሰቦች) መሆኑን ለአፍታም ልንዘነጋው አይገባም!
 


 

%d bloggers like this: