‘Mother of Corruption’ Azeb Mesfin grabs over 10,000 sq.m land at the heart of Addis Abeba to build her palace at taxpayers’ expense!

6 Nov

By በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)
 

የሕወሃት አመራሮችና አባሎች ሁሉ በቅጥፈት የታወቁ በመሆናቸው፣ አዜብ መሥፍንም ለዘወትር ከሚታወሱበት ነገር ለሃብት ክምችት ላላቸው ፍቅር በመሆኑ፣ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ከተውት ትውስታ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያውቃቸው የፋሽሽቱና ዘረኛው የመለስ ዜናዊ ባለቤት በማለት ብቻ ሣይሆን፣ “የሙስና እናት” ጭምር መሆናቸውን በማረጋገጥ ነው።

ታዲያ ግርግር ለሌባ ይመቻል እንደሚባለው፣ በሕዝባዊ ተቃውሞ ሕወሃት ልቡ ተሰልቦ በጠብ መንጃ የያዘው ሥልጣኑን ላለመልቀቅ የሞት ሽረት ትንቅንቅ በሚያደርግበት ከ2015 ኅዳር ጀምሮ ካለው ጊዜ፡ በተለይም እነዐባይ ፀሐዬን የኢትዮያ ሕዝብ በማስተር ፕላን ዙሪያ አንደኛ ላሰማው ድንፋታ ቀጥሎም ሽምጥጥ አድርጎ “ይቺ ቃል ከየት እንደመጣች አላውቃትም” ባለበት የክህደት ሣምንታት አካባቢ፣ አዜብ መሥፍን እናንተ ተያይዛችሁ ተቀጣጠሉ በማለት የመሬትና የቤተ መንግሥት ዘረፋው ላይ ተቸንክረው ከረሙ።

ሕወሃቶቹ ልክ እንዳልሆነ ቢያምኑም፡ ስለዚህ በአደባባይ መናገር የጥቃት በር እንደሚከፍቱ በማመን፡ እነርሱም ቢሆኑ አዜብ መሥፍንን ውስጥ ለውስጥ እንደሚያሟትና እንደሚጠሏት የሚያሳዩ ብዙ መረጃዎች አሉ።

የመጣው ይምጣ ብለው ኅሊናቸውን የተከተሉ እንደ እነአረጋሽ አዳነ ዐይነት ደግሞ በአደባባይ አዜብን ታዝበው፣ “ለሕዝቡ ስሜትና በትዕዝብት የመገንዘብ ችሎታ እንኳ ደንታ የሌላት ዋሾ” በማለት በመሪው ፓርቲ ዘጠነኛ ኮንግሬስ ወቅት ወበዴው መለስና ምሽቱ አዜብ እንዲሁም ልጆቻቸው ጭምር “በብር 6,500 ብቻ እንተዳደራለን” የማለታቸውን ቅጥፈት ሚያዝያ 2013 ላይ በጥፊ ማለታቸው አይረሳንም!

አዜብ የዓለም ፍጻሜ ሆኖ ክርስቶስ መምጣቱ በቴለቪዥንና ራዲዮ ቢታወጅ እንኳ፣ ‘አንድ ቆጆ ቤት በርካሽ የምትሸጥ ስምቻለሁና “እኔ ልወስዳት ከቻልኩ ዐይቼ ለመመለስ እንደሂድኩ ንገሩልኝ’ ብለው በራችው ላይ መልዕክት ለኢየሱስ የሚለጥፋ ልባቸው በንዋይ ፍቅር የሰከሩ መበለት መሆናቸውን የሚጠራጠር አለ ብሎ መገመት አዳጋች ከሆነ፣ ቴድሮስ አድሃኖምም ምስክርነት የሚሠጥበት እንደሆነ የአዲስ አበባ የአንድ ሰሞን ውሽ ውሽ ይታወስ !

ለማንኛውም፣ ሕግ፣ መንግሥታዊ አሥራር፣ሥርዓትና አመራር በሌለባት ሃገር፣ የዜጎች ቤቶች ለሌች ሕወሃት አባላት የመሬት ዘረፋ በሚፈራርሱባት ሃገር፡ ‘የሙስናዋ እናት’ ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶቻቸውን በመጠቀም፡ በማባበል አንዳንዶቹንም በአንዳንድ ጥቅማ ጥቅም በማደንዘዝ፡ ከአሥር ሺህ ካሬ ሜትር በላይ መውሰዳቸው ብቻ ሣይሆን በሕዝብና በመንግሥት ወጭ ቪላዊ ቤተመንግሥት ሊሠራላቸው – ለዚያውም በግል ንብረትነት መፈራረማቸውን እዚህ ሥር ካለው ኦዲዮው ዜና መገንዘብ ይቻላል።

አዜብ መሥፍን (ፌቡ)

አዜብ መሥፍን (ፌቡ)

ኦሮሞች በመሬት ዘረፋ ምክንያትና በሕወሃት ዘረኝነት በደረሰባቸው የፖለቲካ፡ ኤኮኖሚያዊ ጥቃት ምክንያት ሥርዓቱን ለማፍረስ በወርሃ ኅዳር 2015 በተነሱበትና አያሌ የሕይወት መሥዋዕትነት እየከፈሉ ባሉበት ሰዓት፣ ልባቸው በአፍቅሮተ ንዋይና በሃገር ሽያጭ ድንዝዞ ዐይናቸው የታወረው አዜብ መሥፍን በፌስ ቡካቸው የአናሳ ቡድናቸውን አሰተዋጽዖ በሟሟቅና የዜጎችን ጉዳት በመሠወር፡ “ዴሞክራሲን ለኢትዮጵያ ያጎናጸፈው የሕወሃት ትግልና የትምክህተኞችና ጠባቦች” ቅብጠት በማለት የሠነዘሩት የጥጋብና የብልግና አባባላቸው ከማንም ዜጋ አዕምሮ በቀላሉ የሚተን አይመስለኝም!

የትኛው ሃገር ውስጥ ይሆን የዚህ ዐይነት ውንብድናና ዘረፋ የሚካሄደው። ያለፈው ሰሞን ራሱ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – በረከት ስምዖን በቦርድ ሌቀመንበርነት የሚመራው – ለተፈናቀሉ ትግሬዎች በሕገ ወጥነት ግብር ከፋዩ ሕዝብ ካሣ ክፍያ እንዲከፍል መደረጉ፣ ሕወሃት የከረፋ የዘር ፖለቲካን በሃገሪቱ ፊናንስ ሴክተር ውስጥም ማስፋፋቱ ብዙ አደጋ እንዳለው እንኳ ጠባቡ አመራር ሊገነዘበው ማስተዋል አጥቷል።

በወቅቱ እንደጠቆምኩት፣ ይህ ሁኔታ “ዛሬ ለከሠረው የሕወሃት ፖለቲካም ሆነ ለተቀባዩ ትግሬዎችም አይበጃቸውም! ይህም እንደገና የሕዝብና ቁጣ፡ ቂምና የወደፊቱ ግጭት ጥንስስ ይሆናል! የሚያስዛነው ግን አብሮ በኖረ ሕዝብ መካከል መቃቃርን ይፈጥራል!”

ይባስ አለና ይኸው፡ ዛሬ በተለያየ ሙቀት ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሕዝብና ቁጣ ምንም ያህል አፈናና ጫና ቢጋረጥበትም፣ ታሪክ የሚያስተምረን አዘናጊ የሚመስለውን ማዕበሉን – በተለይም የሕወሃት ዐይነት ሞኛ ሞኝ ጥቃት – የሚያቆመም ኃይል እንደሌለ ነው።

በእነዚህ የሕወሃት ማሃይማናን አጥፊነት እንደ ኢትዮያዊነታችን በሃገራችንና በግለሰብ ዜግነታችን ላይ የደረስውን ውርደት ይህ ሕዝባዊ ቁጣ በተለይም ወጣቱ ሳያስተነፍሰው ክንዱን ያጥፋል ብዬ አላምንም።

ከሆነም የፈረንሣዩን ሥነ መንግሥታዊ ፈላስፋ Joseph de Maistreን 1811 አባባል፣ ማለትም “እያንዳንዱ ሃገርና ሕዝብ የሚገባውን አመራር ያገኛል” የሚለውን በቅርብ መመርመር ይገባናል።
 

ተዛማጅ:

  ከአዜብ መሥፍን መንደር፡ ‘ዴሞክራሲን ለኢትዮጵያ ያጎናጸፈው’ የ17 ዓመቱ የሕወሃት ትግልና የኦሮሞች ቅብጠት – ከፌስቡኳ የተወሰደ!

  Azeb sticks around the palace: Is TPLF using it for power play or EFFORT blackmailing ’em?

  New palace for Azeb Mesfin: The visible tip of the iceberg, the arrogance bleeding our nation, butt of Nigerian joke!

  How Long Should Azeb Mesfin Stay in the Palace? Ezega’s Analysis

  EFFORT’S RAPE OF ETHIOPIA: TPLF makes huge progress in humiliating Ethiopia & Ethiopians, without even sparing itself!

  THE ASPIRING QUEEEN & HER POTTED PLANT OR THE MAID?

  Zami Mille – not in Rwanda during the genocide, but in Ethiopia today!

  Mimi’s ‘lies & damned lies’ on EBC about Feyisa Lelisa’s crossed hands

 

%d bloggers like this: