በሕወሃት ትዕዛዝ ከ5 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የኬሚካል ኢንድስትሪዎች ኮምፕሌክስ ትግራይ ሊገነባ ነው፤ ሕወሃት ወይስ ኢትዮጵያ ተጠቃሚው?

11 Nov

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

አዲስ አበባ፣ ኅዳር 1፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከ5 ቢሊየን ብር በላይ የሚወጣበትና የኬሚካል ግብአቶችን ፍላጎት ያሟላል የተባለ የኬሚካል ኢንድስትሪዎች ኮምፕሌክስ ሊገነባ ነው።

የሚቋቋመው ማእከልም የኬሚካል ግብዓቶችን የሚያመርቱ ዘጠኝ ኢንዱስትሪዎች ይኖሩታል።

የኬሚካል ኢንድስትሪዎች ኮምፕሌክስን ለማቋቋም በተደረገው ቅድመ ጥናት ለሚመረቱት ኬሚካሎች ግብዓት የሚሆን የካልሽየም ካርቦኔት ክምችት በመቀሌ መገኘቱ ተነግሯል።

በአቅራቢያው ደግሞ ከአፍዴራ ከሚገኘው ጨው ክሎሪን በማውጣት በቀላሉ ግብአቱን ማግኘት እንደሚቻል ተረጋግጧል።

የኬሚካልና ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ኢንድስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ሀላላ፥ በሀገሪቱ የኬሚካል ኢንድስትሪን ሊያሳድግ የሚችል ኮምፕሌክስ ለማቋቋም ከትግራይ ልማትና ከቻይና ኩባንያ ጋር ከስምምነት ላይ መደረሱን ይናገራሉ።

የኬሚካል ኢንድስትሪዎች ኮምፕሌክሱ ከ5 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ እንደሚደረግበት የተናገሩት ዳይሬክተሩ፥ በውስጡ ዘጠኝ ኢንደስትሪዎችን የሚይዝ መሆኑንም ገልጸዋል።

እያንዳንዱ ኢንደስትሪ የተለያዩ አይነትና መጠን ያላቸውን ኬሚካሎችን ማምረት የሚችሉ ናቸው ሲሉም አቶ ሳሙኤል አብራርተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ እንደሚሉት፥ በዚህ ረገድ ሀገሪቱ ከውጭ ለማስገባት የምታወጣውን ወጪና የሚወስደውን ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ማስቀረት ይችላል።

ለኬሚካል ኢንድስትሪ ኮምፕሌክስ ግንባታ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጠናቆለታል የተባለ ሲሆን፥ አሁን ላይ የዲዛይን ስራው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

በመጨረሻው የምህንድስና ጥናት ላይ ያለው ኮምፕሌክሱ፥ በያዝነው አመት እስከ መጨረሻ ወራት ድረስ ተጠናቆ ግንባታው ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።

የኬሚካል ኢንድስትሪ ኮምፕሌክስ ግንባታም እስከ ሶስት ዓመት የሚሆን ጊዜን ይጠይቃል ተብሏል።

አቶ ሳሙኤል፥ ግንባታው ተጠናቆ ወደ ምርት ሲገባ የሀገር ውስጥ የኬሚካል ፍላጎትን ያቃልላል ብለዋል።

ከዚህ በተጓዳኝ በግንባታ ሂደትና ከግንባታ በኋላ ለበርካታ ሰዎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል የመፍጠር አቅም እንዳለውም ዋና ዳይሬክተሩ ነግረውናል።
 

ተዛማጅ:

TPLF hits jackpot on the chemical inputs front, a seal to its future supremacy – with meagre resources of Ethiopia’s treasury
 

%d bloggers like this: