11,607 ኢትዮጵያውያን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት በቁጥጥር ሥር ውለዋል ይላል ሕወሃት! ስንት መቶኛዎቹ እንደተገለጹለት የኢትዮጵያ ሕዝብ በእርገጠኝነት አያወቅም!

11 Nov

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

አዲስ አበባ ፣ ኅዳር 2 ፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ 11,607 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ገለጸ።

ቦርዱ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች የሚገኙበትን ማዕከላትና የታሰሩበትን ምክንያት በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ሥር ውለው የሚገኙባቸው ማዕከላት፦

  1. በአዋሽ ማዕከል፦ ከፊንፊኔ ዙሪያ፣ ከሰሜን ሸዋ፣ ከምስራቅ ሸዋ ዞኖች

  ወንድ – 1,172 ሴት 2 ድምር 1,174

  2. በጦላይ ማዕከል፦ ከቄለም ወለጋ፣ ከአርሲ፣ ከምዕራብ አርሲ፣ ከምስራቅ ሸዋ ዞኖች

  ወንድ 4,193 ሴት 136 ድምር 4,329

  3. በዝዋይ አላጌ ማዕከል፦ ከጉጂ፣ ምዕራብ ሀረርጌ፣ ምስራቅ ሀረርጌ፣ ከጉጂ ዞኖች

  ወንድ 2,957 ሴት 91 ድምር 3,048

  4. በዲላና ይርጋለም፦ ከጌዲኦ አካባቢ

  ወንድ 2,104 ሴት 10 ድምር 2,114

  5. በባሕር ዳር ማዕከል፦ ከሰሜን ጎንደር፣ ከደቡብ ጎንደር፣ ከምስራቅ ጎጃም፣ ከአዊ ዞኖች

  ወንድ 441 ሴት 91 ድምር 532

  6. በአዲስ አበባ ማዕከል፦ ከአዲስ አበባ የተያዙ

  ወንድ 393 ሴት 17 ድምር 410

 

ግለሰቦቹ የታሰሩባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች:

  *  ሁከት በመፍጠር፣

  *  ሁከት በማስነሳት

  *  ሽብር በመንዛትና አለመረጋጋት በመፍጠር

  *  የግለሰቦችን ቤት

  *  ሕዝባዊና መንግስታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በማቃጠል

  *  ኢንቨስትመንትን በማውደም፣ የመንግስት

  *  የሕዝብንና የግለሰቦችን ንብረት በመዝረፍና በማቃጠል

  *  ማህበራዊ አገልግሎቶች እንዲቋረጡ በማድረግ

  *  መንገድ በመዝጋትና ተሽከርካሪዎችን በማውደም

  *  በቦምብና በጦር መሣሪያዎች በጸጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት በማድረስና በመግደል ተጠርጥረው መሆኑንም ቦርዱ አመልክቷል።

 

ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማን በመቅደድና በማቃጠል፣ የአሸባሪ ድርጅቶችን ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለብ፣ የአሸባሪ ሀይሎችን የሽብር ቅስቀሳ መዕልክቶችን በማሰራጨት፣ ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ መንገድና በማዘዋወር፣ ለፀረ ሰላም ድርጊት እንዲውል በማድረግ፣ አጥፊዎችን በመደበቅና በመተባበርና ነውጡን በግንባር ቀደምትነት በመምራት ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ እንዳሉም ቦርዱ አስታውቋል።

ታሳሪዎች ከላይ በተገለፁት ማዕከላት የሚገኙ ሲሆን፥ የስም ዝርዝራቸው በየክልሉ መስተዳደር አማካኝነት ለዞኖችና ለወረዳዎች ተልኮ የሚለጠፍ መሆኑን ነው ቦርዱ ያስታወቀው።
 

%d bloggers like this: