ከፍተኛ ገንዘብ ፈሶበት የሃገር ተስፋ የነበረውን የጣና በለስን ፕሮጄክት ሕወሃት እንዴት ሌላው ወልቃይት ጠገዴ እንዳደረገ!

1 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
በይርጋዓለም አምባቸው
 
በወታደራዊው ደርግ ዘመን መንግስት በ1978 ተጀምሮ ወንበዴዎች እስከመጡበት 1983 ቆይቷል። ይህ ትልቅ ፕሮጀክት በጎጃም ክፍለሃገር በመተከል አውራጃ የሚገኝ ሲሆን 1600 ስኬር ኪሎሜትር ያጠቃልላል ሲጠናቀቅም ከ80 ሺህ በላይ የሆኑ ህዝቦችን እንዲጠቅም ሆኖ የተጀመረ አገራዊ ፋይዳ ያለው ፕሮጀችት ነበር።

የጣና በለስ ፕሮጀክት ዋና ገጽታው ከሞላ ጎደል ይሄን ይመስል ነበር
1.   35 ሜትር ከፍታ ያለውና ከፍተኛ የሆነ የውሃ መጠን የሚይዝ በጣም
    ትልቅ ግድብ
2.   በየቀኑ 4500 ሜትር ኪውብ ፍሳሽ የሚያስወግድ ፕላንት
3.   225 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው እርስበርስ የተገናኙ መንገዶች
4.   27 ድልድዮች
5.   60 ኪ.ሜ የሚሸፍን የገጠር መንገዶች
6.   50 ኪ.ሜ የሚሸፍን የተፋሰስ ጉድጓዶች ቀላል መንገዶች እና ውሃ
    ማቆሪያዎች
7.   2 ኪ.ሜ የሚሸፍን የቀላል አውሮፕላኖች ማረፊያና መንደርደሪያ
8.   50 መንደሮች
9.   132 አልጋዎች ያሉት ሆስፒታል
10.   23 ሺህ ሄክታር የሚሸፍን የእርሻ መሬት
11.   22 ሺህ ሜትር ስኴር ቦታ ላይ ያረፈ የእርሻ ምርቶች ማከማቺያ
   መጋዝኖች
12.   የአግሮ ኢንዳስትሪ ማቀነባበሪያ የሩዝ መፈልፈያ ፣የምርጥ ዘር
    መምረጫና ዳቦ መጋገሪያ
13.   የከብት የፍየልና የዶሮ ማርቢያ
14.   በወር 6 ኪሎሜትር የሚሸፍን ቱቦና ታንከር የሚያመርት ፋብሪካ
15.   15 ሺህ ሜትር ስኴር የሚሸፍን 2 የፕሮጀክቱ ማዕከል በጣና በለስና በአዲስ አበባ ውስጥ ነበረው።

ከፎቶዎች እንደምትመለከቱት ስራው በከፊል ተጠናቆ ወደ ምርት በመግባት ለተጠቃሚዎች ማድረስ ችሎ ነበር ሆኖም ግን የወቅቱ የአገሪቱ ፕሬዚደንት “ሁሉም ነገር ወደ ጦር ግንባር” ሲሉ የሰሙት ወንበዴዎች ከድል በዃላ እነሱ ደግሞ በተራቸው “ሁሉም ነገር ወደመቀሌ” በማለት እንደ ጠላት ንብረት ሁሉንም ነገር ዘረፉት።የውጭ ጠላት ያወደመው እንጂ የሚመስለው በእነዚህ አገራዊ ወንበዴዎች የፈረሰ አይመስልም::ጣና በለስን የማየት እድል የገጠማቸው ሰዎች ሁሉ እንደዛ ሆኖ መቅረቱን ሲያስቡ ያለቅሳሉ።

ወንበዴዎች ጣና በለስን በመዝረፍ ሱር ኮንስትራክሽንን በማቋቋም ያንን ሁሉ ህልም ባዶ አስቀሩት።ሰው እንዴት ተስፋን ይሰርቃል? ሰው እንዴት የህዝብን ነገ ሆን ብሎ ይቀማል?የወያኔ ሱር ኮንስትራክሽን ለመመስረት 80 ሺ የአማራ ህዝብ መስዋት መሆን ነበረበት? ያን ሁሉ በደል ችለን በኖርን አሁን ደግሞ ሌላ በደል በወያኔ ተጠነሰሰ 75% የጣና በለስ ፕሮጀክት በዲሳ ለሚባል የቱርክ ድርጅት ተሰጠ ይለናል የወያኔው መንግስት።በዚህም ምክንያት ፕሮጀክቱ ያቅፋቸው ለዘመናት መሬቱ ላይ የኖሩ አባዉራዎች እንደ መሬት ወራሪ ተቆጥረው በግዳጅ እንዲነሱ እየተደረገ ነው።

አሁን ግን ወራጅ አለ!! ከዚህ በዃላ የአማራን መሬት እንደናትህ እንጀራ ቆርሰህ የምትሰጠበት ጊዜ ላይ አይደለህም። እንዲያውም ጥያቄያችን ተቀይሯል።ሱር ኮንስትራክሽን ፈርሶ ጣና በለስ ይሰራል።ሱር ኮንስትራክሽን የጣና በለስ ንብረት ነውና ይመለስ!

የአማራው ጉዳይ ያገባናል የምትሉ ሰዎች ለቱርኩ ባዲሳ ይሄንን የመሬት ቅርምት እንዲያቆም በተለያየ የመገናኛ ዘዴዎች ልትነግሩት ይገባችዃል።አለበለዛ መላው የአማራ ህዝብ ለወልቃይት ጠገዴ እንደተነሳው ሁሉ ለጣና በለስም ይነሳል።

ሱር ኮንስትራክሽን የጣና በለስ ነው ይመለስ!!!
/Mesfin Zewdie
 

%d bloggers like this: