የግብርና ልማቱ ዘርፍ በዘረፋና ጥፋት ጎዳና – የተለመደው የሕወሃቶች የጋምቤላ ዘረፋና በሃገር ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት

21 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
ኢትዮጵያ ውስጥ በሥልጣን ላይ የተቆናጠጠው ቡድን ግለስቦችን በዜግነታቸው ሣይሆን፡ በዘራቸው እየለካና እየመደበ ማን አንደኛ ደረጃ ተጠቃሚ እንደሚሆን የራሱን የደምና አጥንት መለኪያ መሥርቶ፡ ሃገራችንን ከፋፍሎ በተለይም ለመሬት ዘረፋ ካጋለጣት ሰንብቷል! ግንባር ቀደም ተበዳይና ብዙ ደም የፈሰሰባት ጋምቤላ በዚህ ማዕበል ምክንያት ብዙ ዜጎችን አጥታለች፤ ብዙ ዜጎችም ተሰደዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ጋምቤላ ሕዝቡ ተራቁቶ፡ በለም መሬቷና ምርቶቿ ተጠቃሚ የሆኑት የአካባቢው ተወላጆች ሳይሆኑ፣ በሕወሃት የሠፈሩት፡ መሬት እየተተለመ የተጣቸው፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክም የሕዝብን ገንዘብ የረጨባቸውና አካባቢውን በሕወሃት ወታደር ተቆጣጥረው የባላይ ባለቤት የሆኑት ትግሬዎች ናቸው። በዚህ ጉዳይ ላይ ለዓመታት ብዙ ተብሏል።

ከሰሞኑ እጅግ አስገራሚው ዜና ግን፣ እነዚህ ይህ ሁሉ የተመቻቸውላችው አንድ ቁጥር ዜጎች፡ የጋምቤላ ተወላጆች አንድ ቁጥር ተበዳዮቹ ሆነው ሳለ፥ አንገታቸውን ደፍተው እየተራቡም ‘በባርነት’ እየተረገጡ ባለበት ሁኔታ፡ በአንድ ጀንበር ለምን ቢሊዮነሮች አልሆነም የሚሉት የጋምቤላ ባለሃብት የሆኑት ትግሬዎች ራሳቸውን ተበዳይ በማስመሰል ያቀረቡ አቤቱታ በመላ ኢትዮጵያውያን ላይ የተቃጣ ብልግና የተመላውና እጅግ ዘግናኝ ነው።

ሌላውን ኢትዮጵያዊ እነፓሊስ ኮሚሽነር ይህደጎ ሥዮምና እነ ግርማይ ከበደ አዲስ አበባ ውስጥ በየቀበሌው ሕዝቡ አናት ላይ ቤቱን እያፈረሱበት በክፋት ስንት ከተፈጸመባቸውና የዜጎች ሕይወቶችም እየጠፉ ባሉባት ሃገር ውስጥ፡ ጋምቤላ ያሉት ሕወሃት አንቀባሮ የሚንከባከባቸው – መጨረሻቸው ምን እንኳ እንደሚሆን የማያውቁት – ትግራዊ ባለሃብቶች በአድሎ ስንት ከተደረገላቸው በኋላ ኅዳር 14/2009 በተጻፈ ጯሂ አቤቱታ አዘል ደብዳቤ (ገጽ 7) እንዲህ ይላሉ፡

“በተወሰኑ የፌደራል ሚኒስትር መስራ ብቶች ያሉ ለስርዓቱ ወገንተኝነት የሌላቸው [በእነርሱ የኮድ ቋንቋ ትግሬዎች ያልሆኑ ማለት ይሆን?] በወፍራም ወንበር ተቀምጠው ልማቱ ሳይሆን የአልሚው የብሄር ማንነት የሚገዳቸው ባለሥልጥናት በደስታ እያስተናገደን የነበረው የጋምቤላ መንግስት እየተጫኑእ በሄክታር 30 ብር የነበረው የመሬት ግብር በአንድ ጊዜ ወደ 111 ብር ከፍ እንዲልና አቅማችን ተዳክሞ እንደንወጣ አሲረውብናል።”!

የዚያ አሳዝኝነትና አሳፋሪነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሳያንሰው፡ የሕወሃት አስተዳደር ደግሞ የጋምቤላን ሕዝብ ለባርነትና ዘረፋ አጋልጦ ዘመናትን ካስቆጠረና የሃገሪቱን ሕዝብ ሃብትና ንብረት ካባከነ በኋላ፣ “በጋምቤላ ክልል ለሰፋፊ እርሻዎች ከተሰጠ 630 ሺህ ሄክታር መሬት ውስጥ ወደ ልማት መግባት ከነበረበት መሬት ወደ ሥራ የገባው ከ15 በመቶ አይበልጥም” ማለቱ ተጠያቂነት የሌለው አሠራር ለኢትዮጵያ ወደፊቷ እጅግ አስፈሪ መሆኑን ያመላክታል።

ወያኔ በዘር ላይ በተመሠረተ ፖለቲካው ምክንያት፣ ‘የኔ’ የሚላቸውን አባሎቹን ጥቅም እንደሚያስቀድም ባለፉት 26 ዓመታት በተግባር ሲያሳይ ኖሯል። ይህንን የሚያደርገው በእውነትም ‘የኔ’ የሚላቸውንም ክልብና በጥሩ አመራር ለመጥቀም ታስቦ ሳይሆን፣ ሌሎችን በመጉዳት (በመዝረፍ) ዘላለማዊ የሕወሃትን የበላይነት በትግራይ ስም ለማስረጽ በማሰብ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ለእነርሱ አደርጋለሁ የሚለው በመጠኑ ቢሳካለትም፣ ሁኔታው ኅብረተሰብ ባስከተለው የመበከል ቀውስ ምክንያት ዛሬ የራሱንም ሕልውና አደጋ ላይ ጥሎት እንመለከታለን።

ኢትዮጵያ በዓለም ብዙ የተለፈፈበት ዕድገቷም ልማት ጠብ ከማይልባቸው ምክንያቶች ዋናው ይኼው ነው። ስለሆነም፣ ዕድገት ዛሬ በዜጎች ልማትና ብልጽግና ላይ ባለመመሥረቱ ምክንያት፣ ሕወሃትም የሞኝ ብልጥነቱን ክፉኛ ባጋለጠ ሁኔታ የከተማና አካባቢ መንገዶችን በማስፋፋትና በአንዳንድ ከተሞች ትላልቅ በእነርሱ ቱባ የሲቪልና ወታደራዊ መሪዎች ባለቤትነት የተያዙ ሕንጻዎችን በመገንባት ኢትዮጵያ ውስጥ ልማት አለ ለማለት ማስቻሉ ብዙ ቢሰማም፣ በተጻራሪው የድህነት መንሰራፋትን እያሳየ መጥቷል።

ድህነት መስፋፋቱን የሚነግሩት ሃቀኛ ዜጎች፣ የተባበሩት መንግሥታትና የባዕዳን የልማት ምርምር ማዕከሎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ፥ ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ ከቻድና ኒዤር ብቻ በላይ ናት ሲባል የነበረው፥ ዛሬ አፍሪካ ውስጥ ቻድ ዕድገቷ በመጨመሩ፡ የኢትዮጵያ የበላይነት ከኒዤርና ከደቡብ ደቡብ ሱዳን መሆኑን የOxford Poverty and Human Development Initiative (OPHI) ጥናት በ2016 ከዚህ በታች በሠፈረው ዘገባው ተመልክቷል!

Source: OPHI

Source: OPHI

[Click to mangify]

በኢትዮጵያ የአምስቱ ዓመታት የልማት ዘመን (GTP I 2011-2016) ሃገሪቷ ወደኋላ ማሽቆልቆሏን የተተለሙት ዕቅዶች አንዳቸውም አለመሳካታቸው ኅዳር 2015 ላይ ሕወሃት ራሱ ለማመን መገደዱን እናስታውሳለን! የሃገሪቱ የውጭ ወደጆችም ቢሆኑ ዕድገት ዜጎች በሙሉ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው በከበሩበት ሁኔታ ውስጥ ብቻ ነው የሚለውን ሕወሃት እንዲገነዘብ ብዙ ጥረት ቢያደርጉም፡ ጆሮ ዳባ ልበስ ያለ አስተዳደር ሃገራችንን የአፍሪካ ጭራ አድርጓታል!

ዛሬ በሰው ሃብት ልማት ኢትዮጵያ በ174ኛ ደረጃ ከቻድና ከኒጄር በላይ ብቻ ትገኛለች። ሆኖም በድህነቷ ጥልቅነት፡ ኢትዮጵያ ከእነዚህ ሃገሮች በታች መሆኗን የልማት ድርጅቱ (UNDP), Table 2.4 ላይ አመልክቷል።

የተባበሩት መንግሥታት የንግድና የልማት ድርጅት (UNCTAD) ስሞኑን ባወጣው ዘገባ ኢትዮጵያ – ከአንደኛውና ሁለተኛው የልማት ዘመን (2011-2016፤ 2016-2020 GTP II) ፕላኗ ቅዠት ውጭ – ኢትዮጵያ በልማት ዝቅተኛ ከሆኑት ሃገሮች መካክል ከ2024 በኋላም ወደ መካከለኛ በልማት ከተራመዱት ሃገሮች መካከል እንደማትገኝ አስረግጧል!

ይህ የወያኔዎች ምዝበራና ቅዠት ያስከተለው በመሆኑ፣ ዜጎች ይህንን የሃገራችንን በቁም መሞት በጥብቅ ልናስብበት ይገባል! የተጀመረው የሕዝብ አመጽና ትግል ሊፋፋም ይገባል!

አይግረማችሁና፣ የሕወሃት ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን መሬት ከተከፋፈሉ በኋላ ከማክሰኞ ታህሳስ 20/2016 ጀምሮ፣ እያንዳንዱ ክልል የራሱ መሬት ኃላፊ ነው በማለት ፌደራል መንግሥት በሞግዚትነት ማስተደደሩን ማቆሙን አስታውቋል! ሕወሃት ዘረፋውን በሌላ መልክ ያጧጡፋል ማለት ነው!

የጋምቤላ ሕዋቶችም የቀድሞው የሕውሃት አባል የኢትዮጵያ ልማት ባንክም ከሥልጣኑ እነደብረጽዮን ገብረሚካኤል ወስነዋል!
 

%d bloggers like this: