ታስረው የተፈቱት ‘ሥልጠና ላይ ከረሙ’ ተባለ፤ ግርፋትና ሰቆቃ ተፈጽሞብናል የሚሉም አሉ! የቱን እንመን? አሁን በአካባቢያቸው የሚደርስባቸው ነገር እንደማይኖርና ተረጋግተው መደበኛ ሕይወታቸውን እንዲቀጥሉ ተነግሯቸዋል! ተግዳሮቶቻቸውን ወይንስ የቱን ይመኑ?

24 Dec

“አይደገምም!” – ጉልበተኛው ተጠቂውን የሚያስገባው ግዴታ! (ኢዜአ ፎቶ)


Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

ከሰሞኑ ሕወሃት አሥር ሺ የሚጠጉ ነጻነታቸውንና መብቶቻቸውን የተገፈፉ ታጋዮችን ቢፈታም፣ ነገሩ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ሆኖ፣ የአምቦ ተማሪዎች ለረዥም ጊዜ የታሠሩ የፖለቲካ እሥረኞች ይፈቱ በማለት ሠልፍ በማድረግ ሲጠይቁ፡ እንደተለመደው የሕወሃት ኮማንዶች ተማሪዎቹን በመክበብ ብዙዎቹን ከቀጠቀጡ በኋል ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ ወጣቶችን ወደ እሥር ወርውረዋቸዋል!

እንደ አዲስ አገርሽቶበት፡ ሃመር ባኮ፥ ኦሮሚያና ጎንደር ውስጥ ብዙ ሰዎች መታሠራቸውና ገደላቸው እየተሰማ ነው!

ለማንኛውም፡ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ተፈጥሮ ከነበረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በሁከት ተጠርጥረው ተይዘው ከነበሩ አብዛኞቹ ወጣት ታሣሪዎችን የኢትዮጵያ መንግሥት ከትናንት በስተያ ለቅቋል። ከእሥር የተፈቱት በስድስት ጥራዝ የታተመና የፖለቲካና ምጣኔ ሃብት ይዘት ያለው ሰነድ ላይ ሥልጠና ተሰጥቷቸው፤ በመንግሥቱ አባባል “ተሃድሶ” አድርገው ወጥተዋል – የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ እንደዘገበው።

በጦላይ የተሃድሶ ማዕከል የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በዚሁ ጊዜ ባስተላለፉት መልዕክት ‘ሠልጣኞች’ ወደ መደበኛ ይወታቸው እንዲመለሱ መንግሥት ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል። ሥራአጥ የሆኑ ወጣቶችም በራሳቸው መንገድ ሥራ እንዲፈጥሩ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው፣ ሠራተኞች ወደ ሥራ ገበታቸው ተማሪዎች ደግሞ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል

ወጣቱ ጥያቄ እንኳ ቢኖረው ሕገ-መንግሥቱ በሚፈቅደው መሠረት የማቅረብና መልስ የማግኘት መብት እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ ሲሉ በአንድ በኩል ያስገርሙኛል። አብዛኛውን ጊዜ ግን ያስቆጡኛል። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የሕግ የበላይነት የማይታሰብባት ሃገር ውስጥ እንዲህ ማለታቸው ማንን ሞኝ ለማድረግ ነው?

ከወራት በፊት በተፈጠረው ሁከትና ግርግር ሕይወት የጠፋ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸው ለዘመናት የተለፋባቸው የሕዝብ ሃብቶችም መውደማቸው አግባብ አለመሆኑን ተናግረዋል። አሁን ታሣሪዎችወደ አካባቢያቸው ሲመለሱ የሚደርስባቸው ነገር እንደማይኖር ገልጸው ተረጋግተው መደበኛ ሕይወታቸውን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ በበኩላቸው በክልሉ የሠፈነውን ሰላም ለማስቀጠል ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ጋር በቅንጅት ሥራዎች ይሠራሉ ብለዋል።

People & Government (The Reporter)

People & Government (The Reporter)

ይህን እንዴት ወደ ተግባር እንደሚተረጉሙ እርሳቸው ብቻ ናቸው የሚያውቁት! ሪፖርተርም ተመሳሳይ ጥያቄ ስላለው ነው መሰለኝ በርዕሰ አንቀጹ ወንበር አለዋውጦ የቀረጸውን ካርቱን አስታውሶኛል! [Click to magnify]

የኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽነር ፀሃይ በላይ እንደገለጹት ጦላይ ተሃድሶ ማዕከል ከገቡ 5,600 ሰልጣኞች መካከል 4,035 ያህሉ በስድስት ዋና ዋና ጉዳዮች ሥልጠና ወስደው ተመርቀዋል። “ሠልጣኞቹ በቆይታቸው በፍፁም አይደገምም፣ የቀለም አብዮት፣ የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት የኢትዮጵያ ህዳሴ” በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና መውስዳቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል
==============

ታስሮ የተለቀቀው ብሎገር በፍቃዱ ኃይሉ ሰለ“ተሃድሶ”ይናገራል


=============
 
ሂሩት ኃይሉ እንደዘገበችው፣ በአምቦ ዩንቨርስቲ ሌክቸረር የነበረው ሥዩም ተሾመ ተገርፎና ተደብድቦ ከእሥር ቢለቀቅም ሥልጠና ላይ ከርሞ ተፈታ ተብሎ እንደሌሎቹ ወገኖቻችን ሁሉ ተለቋል


==============
 
በመጨረሻ የምንተወው አስተያየት፡ ሕወሃት ሕዝብን አክብሮ ማስተዳደር እንደማይችል ለ26 ዓመታት በማያሻማ መንገድ ስላሳየ፣ ምንም ያህል ትያትርና ቅጥፈት አያዋጣውም! የኢትዮጵያ ሕዝብ መብቱንና ጥቃቱን ለይቶ ያውቃል።

ሕወሃትም ለኢትዮጵያ ሕዝብ – ‘የትግራይ ሕዝብ ለወላይታ ምኑ ነው?’ ብሎ ከዚህ በፊት ዝምድናውን እንዳጣጣለው ሁሉ ሕዝቡም ምኔም አይደለህም የሚልበት ደረጃ ላይ ስለሆነ፣ ቢቻል ታሪክ ሠርቶ ማለፍን እንደ ዋነኛ አማራጩ እንዲያየው እንመክራለን – ሲመነዘር 26 ዓምታት ሙሉ የፈፈጸመው ግድያው የትም እንደላደርስው፣ ከእንግዲህም የሚፈጽመው የራሱ የጥፋት ጎዳና እንደሚሆን ሊጠራጠር አይገባም!

ለመሆኑ ያን ቀን ሠልጣኞቹ ተፈተው ወደ የአካባቢያችው ሲደርሱ፡ ኮማንድ ፖስቱን ሳይፈራ የሕዝቡ ደስታና ተቃውሞ የረዚስታንስ ምልክቱን እያሳየ ወደ መሃል መንገድ መንጎዱ ምንም አይነግራችሁምን?

የ1948 ዓ.ም. Universal Declaration of Human Rights እንዲህ ይላል፦

“[I]t is essential, if man is not to be compelled to have recourse, as a last resort, to rebellion against tyranny and oppression, that human rights should be protected by the rule of law”.

 

%d bloggers like this: