ትግራይ በአዲገዛኢ ቋሚ ኤክስፖ ሰበብ ሕወሃት ከሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የታሪካዊ ቅርሶች ዘረፋ በትዕዛዝ ጀምሯል!

28 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
ሂሩት ኃይሉ ገጽ የተዋስነው
 

/hiruthailu

/hiruthailu

Hirut Hailu (FB picture)

Hirut Hailu (FB picture)

“ሂሩት ኃይሉ እባላለሁ ። ሰሞኑን የትግራይ ክልል መንግስት ለብአዴን ተላላኪዎቹ በጻፈው ደብዳቤ ላይ በአማራ ክልል ውስጥ የሚገኙ ታሪካዊ ቅርሶች በሙሉ ተሰብስብሰው ወደ ትግራይ እንዲላኩለት አዝዟል። ከዚህ በፊት በርካታ የአማራ ሕዝብ ታሪካዊ ቅርሶች መዘረፋቸውና ማንም ተጠያቂ ሳይኖረው መቅረቱ ይታወሳል። አሁንም በብአዴን በኩል ሊሰበሰብ የታሰበው ታሪካዊ ቅርሶቻችን ወደ ትግራይ የመላክ ዘመቻ የአማራውን ሕዝብ መብት የሚጋፋ በመሆኑ እነዚህ ቅርሶች ከነባር ቦታቸው መነሳት እንደሌለባቸው አምናለሁ ። ስለሆነም ይሄንን ሕገ ወጥ የቅርስ ዘረፋ በጽኑ እቃወማለሁ ። የአማራ ሕዝብ መብት ይከበር ። ቅርሶቻችን ይከበሩ!!!”
 

የአዘጋጁ አስተያየት፡

  በዲሞክራሲያዊ ሃገሮች – መተማመንና የጋራ እሴትን ለጋራ ጥቅም እንዲሁም ለሃገር ደኅንነት ለማዋል የሚያስችል ሁኔታ በመኖሩ፥ የዚህ ዐይነቱ ትብብርና አሠራር አዲስ ነገር አይደለም።

  ነገር ግን ሕወሃት ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሌሎቹ የኢትዮጵያ ክፍሎችና በድርጅቱ መካከል ያለው ግንኘነት – ባለፉት 26 ዓመታት እንደተመለከተው ከሆነ – የገዥና የተገዥ፣ ተፈናቃይና ተዘራፊ – በአጭሩ ከባሪያ ፈንጋይ ጋር የሚኖር ግንኙነት ዐይነት/ትሥሥር በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በፈቃዱ ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሳ ቅርሶቹን ለገዥዎቹ በፈቃዱ የሚያስተላልፈበት ሁኔታ ተግባራዊ ሊሆን ከቶውንም ሊታሰብ ቀርቶ ሊገመት እንኳ ይዘገንናል።

  ከሁሉም የከፋው ደግሞ – ሕወሃት የበላይ ገዥ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተረጋጭና ተሳዳጅ፡ እነርሱ የዘመኑ ባለሃብቶች፡ ኢትዮጵያውያን በርሃብና ጥማት ተቆራማጆች በሆኑበት ዘመን ውስጥ – ሕዝባችን አንጀቱ በግኖ በተነሳሳበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት፣ ሕውሃት ይህንን መጠየቁ የድፍረት ድፍረት ነው! የምን ገጸ በረከት ነው የሚቀርብለት?

  ጀግናው ሕዝባችን አንገቱን መድፋት እንደፈሪና ሞኝነት ቢታይበትም፣ የሕውሃት ደባውና ንቀት አልገባውም ማለት እኮ አይደለም! ለዚህም ነው አማሮችንና ኦሮሞችን አስተቃቅፎ ማዕከል በማደረግ – ሌሎችም እየተንቀሳቀሱ ነው – እኩልነትን፡ ሰብዓዊ ነጻነትንና ዲሞክራሲን የተጎናጸፈ የኢትዮጵያውያን የዘንድሮው ተጋዳይነት ገሃድ የሆነው!

  ሂሩት ኃይሉ!

  ይህንን በሚመለከት የጻፍሽውና የጀመርሽውን ትግል አደንቃለሁ፤ እደግፋለሁ! በምክር ደረጃ ግን ይህ አማራ ላይ ብቻ ከሚያተኩር መላው ኢትዮጵያ-ተኮር ቢሆንና እንዲሆን እማጸንሻለሁ። በድርጊት ደረጃ እያንዳንዱ ክልል በደብዳቤ ስለተጠየቀ (የአክሱም ባህልና ኃውልት ለወላይታ ምኑ ነው ያሉትን ቅሌት ዘንግተው፣ ሁሉንም ነው የሚጠይቁት ብዬ በመገመት)፣ ከተደረገም ዞሮ ዞሮ በክልል ደረጃ የሚከናወን ስለሆነ፣ እያንዳንዱ ክልል በተናጠል ስለሚወስን (በሕወሃት ተወካዮች አማካይነት ቢሆንም)፣ የሃገር ጉዳይ ባደረግሽው ዘመቻሽን ይበልጥ እንዴት ብዙዎችን ለመድረስ በቻልሽ!

  ሂሩት አሁንም የሚያዋጣንና ለሕዝባችን የጥንካሬ ምንጭ የሚሆነው ኢትዮጵያን አስበን መሥራታችን ነው! ሕወሃት ዛሬ ይህንን በደብዳቤ ያድርገው እንጂ ሰንበት ብሎ ደግሞ ውስጥ ለውስጥ በድርጅት ደረጃ ትዕዛዝ ያደርገዋል! የሕዝብ ተቃውሞ ስላለ ለዚህም ነው ሃገር አቀፍ ማድረጉ የሜጠቅመው።

  ማርክሲዝም ሌኒንዝም/ማኦይዝም በዓለም ላይ ከፈጸሟቸው ስህተቶች አንዱ ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነትና የፓርቲ መመሪያዎች የበላይነት/ተከባሪነት ለእንደ ሕወሃት ዐይነት አፋኝ የወንበዴዎች ስብስብ ምቹ ሆኖ የመገኘታቸውም መርገም ቀደም ብለው ለማየት አለመቻላቸው ይመስለኛል!

  ለዚህ ነው ሰብስብና ጠንቀቅ ብለን ሃገራችን ፊት በተጋረጡና በሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ የጋራነትንና የትግል ትስስርን ጥቅም ችላ ማለት የማይገባን!

 

%d bloggers like this: