ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ የፕላን ዘመን ሁለት ግማሽ ዓመት አፈጻጸምን ዝቅተኛነት ተናገሩ!

24 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2009 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት የማምረቻው ዘርፍ የወጪ ንግዱ ማሳካት የቻለው ከእቅዱ 56.5 በመቶ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ አብተው ገለጹ።

የንግድ ሚኒስቴር የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸሙን በዛሬው እለት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል።

ሚኒስትሩ እንደገለጹት፥ በበጀት ዓመቱ የማምረቻው ዘርፍ ምርትን ወደ ውጭ በመላክ 913.6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ለማግኘት ታቅዷል።

ከዚህ ውስጥ 349 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላሩን በመጀመሪያው ስድስት ወራት ለማግኘት ታቅዶ፥ ማሳካት የተቻለው 198.5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ብቻ መሆኑንም ተናግረዋል።

ከእቅድ አንጻር ገቢው ዝቅተኛ አፈጻጸም ቢያሳይም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት አንጻር ግን የ3.9 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ነው ያሉት።

በዘርፉ የጨርቃ ጨርቅ፣ የቆዳና ቆዳ ውጤት ምርቶች እንዲሁም የስጋ ተዋጽኦዎች የወጪ ንግድ እንቅስቃሴ መቀነሱም ነው የተጠቀሰው።

ያለቀላቸውን ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ለውጭ ገበያ አለማቅረብ፣ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት አለመሸጋገር እንዲሁም በአለም ገበያ የምርቶች ዋጋ መቀዛቀዝም ለገቢው መቀነስ ምክንያት ናቸው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም በአብዛኛው በሃገር ውስጥ ባለሃብቶች የተያዙ ፋብሪካዎች ለሃገር ውስጥ ገበያ ማቅረባቸውም የዘርፉ ችግር ሆኖ ተጠቅሷል።

በዘርፉ የወጪ ንግድ እቅዱን ማሳካት ባይቻልም ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሃገር ውስጥ የመተካት ስራ ውጤት እያሳየ መምጣቱም ነው የተጠቀሰው።

ከዚህ አንጻርም በግንባታው ዘርፍ በሃገር ውስጥ ምርቶች የመጠቀም ሂደት መጎልበቱም ነው የተነሳው።
 

ማስተማመኛ ከሚሹ የተሠጠ ማስተማመኛ

 

 

ታዛቢዎችስ ስለፕላኑ ምን ይላሉ?
 

ተዛማጅ:

  Arkebe’s lies to Bloomberg on continuing double-digit growths terribly delusional & irresponsible

  In a nation heading toward a future of conflict & violence, Hawassa whets TPLF’s appetite: Should Ethiopians expect another Oromia or Gambella SNNPR becoming feeding tube to TPLF political cadres?

  With 45% performance rate in its GTP II target, tourism sector earns only $2.7bil in nine months

  GTP II’s first half-year performance in textile sector disappoints, as did GTP I’s five years

  የግብርና ልማቱ ዘርፍ በዘረፋና ጥፋት ጎዳና – የተለመደው የሕወሃቶች የጋምቤላ ዘረፋና በሃገር ላይ እየተፈጸመ ያለው ጥቃት

  A plundered Ethiopia being forced to cater to TPLF’s whetted appetite: Kombolcha & Mekelle Industrial Parks on rush to roll without let!

  TPLF gets Ethiopian treasury to cooperate with EFFORT in heavily investing a poor & hungry nation’s resources into Tigray’s industrialization

 

%d bloggers like this: