ለመሆኑ አዲስ አበባ ከተማ የማናት? ቅጥ ያጣው የሕዋሃቶች ቁማር በመሬት ዙርያ!

1 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

ሰሞኑን ሕወሃቶች አንድ ዘመቻ ጀምረዋል። ለነገሩ እንደማንኛውም የሕወሃት ነገር ሁሉ፣ ቁጥር ላይ የተመሠረተ ነው። ዛሬ ሃገራችን የውጭ ዕዳ ለስኳር ጭምር ተሸክማ ባለችበት ሁኔታ ለምን ስኳር የለም ስንል መልሱ፡ ፕሮጀክቱን የሕወሃት ሰዎች በችሎታ ማነስ አበላሸተውታል። ገንዘቡንም በልተዋል።

ታዲያ ሰሞኑ የጀመሩት ዘመቻ ትግሬዎች አዲስ አበባ ውስጥ እንደሚባለው ሃብታሞች አይደሉም የሚል ላይ ያተኮረ ነው! ፌስቡክ መልዕክት – ለመከፋፍልም የሚሞክረው – ዋናዎቹ ሃብታሞች ጎጃሜዎች ናቸው ይላል።


 

አዲስ አበባ ውስጥ ካሉት ከ130 በላይ ግዙፍ ሆቴሎች 11 ብቻ የትግሬዎች ባለቤቶች ሲኖራቸው፣ 38ቱ ደግሞ በጎጃሞች የተያዙ ናቸው ይላል።

ለነገሩ ማን ይሆን እያሠረ፣ ቤቶች እየደረመሠ መሬት ከጣራና ግርግዳ ሥር የሚነጥቀው፡ እየገደለና እየዘረፈ ሃብት ለራሱና ለወገኖቹ የሚያስተላልፈውና የሚያካብተው ማን ሆነና?

የሚገርመው ነገር ባለፈው ሣምንት መጀመሪያ ላይ ኢንዱስትሪዎች አዲስ አበባ አካባቢ እንዲቋቋሙ 10.5 ቢሊዮን የሚፈጁ ፕሮጀክቶች መዘጋቸታቸውን የሕወሃት ሰዎች መቃወማቸው ነው። ምክንያታቸው ምንድነው? ለምን ትግራይ ውስጥ አይሠሩም በማለት ነው! ትዊቴን ይመልከቱ!

የሚገርመው በሃገር ውስጥ ያከማቸው ሃብት ብቻ ሣይሆን፡ሕወሃት ወደ ውጭ ሃገርም ብዙ ሃብት ማሽሹ ይታወቃል!

ከላይ የተቀመጠው ቪዲዮ ላይ ጠቃሚ መረጃ ያገኛሉ!
 

%d bloggers like this: