የደቭራይ ዩኒቨርሲቲ ቅሌት ከሕወሃት ዕለታዊ ዝቅጠት ጋር ሲነጻጸር!

1 Feb

በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)

ባለፈው ሣምንት በጣም ካስደሰቱኝ ዜናዎች መካከል ካሊፎርኒያ ውስጥ የሚገኘው የደቭራ ዩኒቨርሲቲ (DeVry University) በሃስተኛ ማስታወቂያ ምክንያት ባለፈው ታህሳስ በአሜሪካ ትሬድ ኮሚሽን አማካይነት ክስ መመሥረቱን የተመለከተው ነው።

በኒው ዮርክ የበላይ ሕግ አስከባሪ የሆኑት ኤሪክ ሽናይደርማን እንደሚሉት ከሆነ፣ ዩኒቨርሲቲው የተውነጀለው በሚከተሉት ጉዳዮች ነው፦

“DeVry used misleading claims to lure in students who were simply seeking a college degree, greatly exaggerating job and salary prospects for graduates” said Attorney General Schneiderman. “I’m pleased that this settlement provides much-deserved restitution to students who were misled, and requires DeVry to stop its false advertising.”


ይህም ማለት፣ ዩኒቨርሲቲው ካደረጋቸው ነገሮች አንዱ ዘጠና ከመቶ የሚሆኑት የደቭራይ ምሩቆች በትምህርታቸው መስክና በስድስት ወራት ሥራና ጥሩ ደመወዝ ያገኛሉ የሚለው ይገኝበታል። ይህም ብዙ ተማሪዎች ወደዚያ እንዲጎርፉ ሁኔታ አመቻችቶለት ስለነበር፣ ሕግና ተጠያቂነት ባለበት ሃገር፡ የፌዴራል መንግሥቱ Trade Commission ሕዝቡ በብልጣ ብልጦች እንዳይመዘበር ምርመራ ካደረገ በኋላ ክስ መሥርቶበታል።

ጥር 2017 መጨረሻ ላይ የደቭራይ ዩኒቨርሲቲ የቀረበበት ክሱ ቀርቶ በግልግል $100 ሚሊዮን ካሣ ለመክፈል ተስማምቷል። ከዚህ ገንዘብ ውስጥ $49.5 ሚሊዮን ለተመዘበሩት ተማሪዎች ይከፋፈላል።$50.6 ሚሊዮን ደግሞ ተማሪዎች ለትምህርት የተበደሩትን ብድር ዕዳ እንዲከፍሉ የሚያስችል ፈንድ ይሆናል፣ ኮምሽኑ እንደዘገበው

ዕውነቱን ለመናገር ይህንን ካነበብኩ በኋላ ከፍተኛ ኃዘን ነው የተሰማኝ – የሕወሃት ቀላማጆች በሃገራችን ላይ የሚፈጽሙትን አሳፋሪ ድርጊቶች – እያሰብኩ።

ሕወሃትና ቅጥረኞቹ በሕዝብ መገናኛ እንዴት እንደሚቀላምዱ ስመለከት፡ ባለሥልጣኖቹ ዐይኖቻቸውን በጨው አጥበው በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትሩና የመከላከያ ሚኒስትሩ ማን የበለጠ መዋሸት እንደሚችል ውድድር ላይ ያሉ እስኪመስሉ ድረስ!

ኢትዮጵያ በሕግ የምትተዳደር ሃገር ብትሆን ኖሮ፣ ሕወሃትና ጀሌዎቹ ለፈጸሟቸው ወንጀሎች የሚከፍሉት መቀጫ – በገንዘብ ቢሆን ኖሮ – ቁጥሩ አስትሮኖሚካል ማሰቡም አስቸጋሪ ይሆን ነበር!

የኔ ጥያቄ ግን በውሸትና ቅጥፈት – ከውርደትና ንቀት ውጭ – የትም ሊደረስ እንደማይቻል ለምን ያለፉት ሁለት ዓመታት ሕዝባዊ አመጽና የሕዝብ ንቀት ትምህርት ሊሆን አልቻለም?

Fana foto

Fana foto

ለምሣሌም ያህል፣ በሕወሃት የታፈኑት ከመቶ ሺህ በላይ ወጣቶች መካከል ዛሬ ስለሚፈቱት ሲራጅ ፈርጌሣ ማክሰኞ ሚዲያ ላይ ቀርቦ በሠጠው መግለጫ፣ 11,352 ወጣት ታሣሪዎች ለሃያ ቀናት በሕገ መንግስቱና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ላይ ያላቸው ግንዛቤ እንዲዳብር መደረጉን” ገልጿል።

ለመሆኑ፣ ራሱ ሕወሃት የሚያስተዳድረው አገዛዝ ምን ዐይነት ግንዛቤና ለሕግ ከበሬታ ኖርት ነው ወጣቶቹን ለማስተማር ብቃት ያገኘው? ይህ ለምሣሌ የዜጎች ጥያቄ ነው!

የሚገባንን ያህል ሕጉ ከተከበረ ግን ሕወሃት ዘረኝነቱና ዘረፋው እንጦርጦሮስ ይሰደዋል!

የደቭራይ ዩኒቨርሲቲ ዐይነት ዜና የሕግ በላይነትና ተፈጻሚነት እንደምናውቀው ሃገር ኢትዮጵያውያንን እንዲናፍቀን ያደርገናል! ታዲያ ሕወሃት ሰሞኑን እየተሰማው ያለው የተለመደው ባለግ ባለግ ማለት ሲመጣ፣ ለስካሩ ትንሽ እንደሚበቃው ያሳየናል።

ሃገራችን ያለችበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው!
 

%d bloggers like this: