ዜጎችና የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት በሚሳደዱባት ኢትዮጵያ ሕወሃት ሃገሪቱን ለግሎባል ፈንድ በጨረታ አቀረባት! ለምን?

7 Feb

በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)
 
I. ግሎባል ፈንድና የኢትዮጵያ ትብብር
 
ግሎባል ፈንድ (Global Fund) በመንግሥታት፣ ሲቪል ድርድቶችና (Civil Society) የግል ዘርፍ የሆኑ ድርጅቶች (Private sector) ለስሙ በጋራ ያቋቋሙት ድርጅት ነው። ተልዕኮውም ከድሃና መካከለኝ የዕድገት ደረጃ ላይ የሚገኙ ሃገሮች ውስጥ የሣንባ ነቀርሳን (Tuberculosis – TB)፣ HIV/AIDSንና የወባ በሽታን (Malaria) ለመከላከልና ብሎም ለማጥፋት እ.ኤ.አ. በ2002 ዓ.ም. ጂኒቫ የተመሠረተ በገንዘብም በጣም ፈርጠም ያለ ድርጅት ነው።

ይህንንም ድርጅት ለማቋቋም ጥንስስ ሃሣቡንና መቋቋሚያ ገንዘቡን ካዋጡት መካከል የቢልና መሊሳ ጌትስ ፋውንዴሽን ከግል ድርጅቶች መካከል በግንባር ቀቅምነት ይጠቀሳሉ።

የፈንዱ ተልዕኮም ከድሃና መካከለኛ የዕድገት ደረጃ ላይ ከሚገኙ ሃገሮች ውስጥ የሣንባ ነቀርሳን (Tuberculosis – TB)፣ HIV/Aidsንና የወባ በሽታን ለመከላከልና ብሎም ለማጥፋት የተቋቋመ በገንዘብም ፈርጠም ያለ ድርጅት ነው።

በ2000 ዓ.ም. ኦኪናዋ (ጃፓን) የተካሄደው የቡድን 8 (G8) ጉባዔ ባስተላለፈው ውሳኔ፡

“Only through sustained action and coherent international co-operation to fully mobilise new and existing medical, technical and financial resources, can we strengthen health delivery systems and reach beyond traditional approaches to break the vicious cycle of disease and poverty.” እዚህም ላይ ተመሥርቶ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፎ ነበር፦

  “*   Mobilising additional resources ourselves, and calling on the MDBs to expand their own assistance to the maximum extent possible;

  *   Giving priority to the development of equitable and effective health systems, expanded immunisation, nutrition and micro-nutrients and the prevention and treatment of infectious diseases;

  *   Promoting political leadership through enhanced high-level dialogue designed to raise public awareness in the affected countries;

  *   Committing to support innovative partnerships, including with the NGOs, the private sector and multilateral organisations;

  *   Working to make existing cost-effective interventions, including key drugs, vaccines, treatments and preventive measures more universally available and affordable in developing countries;

  *   Addressing the complex issue of access to medicines in developing countries, and assessing obstacles being faced by developing countries in that regard;

  *   Strengthening cooperation in the area of basic research and development on new drugs, vaccines and other international public health goods.”

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሶስት በሽታዎች ሃገራችን ውስጥ ብዙ ጥፋት አድርሰዋል፤ እያደረሱም ናቸው። በግሌም በበ1990ዎቹ የተማረችና የቅርብ ሥጋና ደሜ የሆነች ወገኔም ለሣንባ ነቀርሣ መሥዋዕት መሆኗ ስለነዚህ በሽታዎች ጎጅነትና ኅብረተሰብ አፍራሽነት በግልጽ ያሳየናል።

በዓለም ዙሪያ የኤድስ በሽታ ከታወቀ ወዲህ 70 ሚሊዮን ሰዎች መለከፋቸውንና ከነዚህም መካከል 35 ሚልዮን መሞታቸውን የዓለም ጤና ጥበቃ መረጃ ያሳያል።

ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው ከ800,000 በላይ የHIV/Aids ተጎሳቃዮች ሲኖሩ፡በ2016 ብቻ 380,000 ኢትዮጵያውያን በዕርዳታ የሚሰጠውን ኤድስ መቋቋሚያ መድኃኒት (antiretroviral therapy) እየወሰዱ ናቸው።

በገራችን ውስጥ ከተላላፊ በሽታዎች (Infectious disesases) ቀጥሎ ሁለተኛው ነፍሰ ገዳይም መሆኑ በዓለም ጤና ጥበቃ ደርጅትና በአሜሪካ የበሽታ መከላከል ማዕከል ዘግቧል።

ለነገሩ መረጃው በሚገባ ስላልተጠናቀረ ነው እንጂ ኢትዮጵያ ውስጥ – አንዴ ካለፈው ዓመት ወዲህ ዜጎች እንደሚሰማቸው ከሆነ፣ አንደኛ ወይንም ሁለተኛው ቅደም ተከተልማውጣት ቢቻልም፣ ምናልባትም ከተላላፊ በሽታዎች፣ ኤድስ ቀጥሎ ከ4,000 በላይ ዜጎች ሕይወት የሚቀጥፈው የመኪና አደጋ ቀዳሚ ክፉ ነፍሰ በላዎች መሆናቸውን ዜጎች ይገምታሉ!

የዓለም ኅብረተሰብ የሕወሃትን አስጸያፊ ባህሪ በቅጡ ቢያውቀውም፡ በጥቅም ልውውጥ ምክንያት በትዕዝብት ዝም ብሎ ከመመልከት ባሻገር ምንም አላደረገም። እነደቢል ጌትስ ዐይነት ሃብታሞች ደግሞ መንግሥታቸውን የሚገፋፉት፣ ጨቋኝ አስትዳደር – እንደ ሕወሃት ዐይነት ማለት ነው – የሚያረገውን አድርጎ ሕዝቡን ቀጥ ለጥ አድርጎ ለእነርሱ ካፒታል መዳበር በሩን እንዲከፍት፣ ሲያስፈልግም እነርሱ የጠሉትን ወገን ተዋግቶ ሰላማቸውን እንዲያስከበርላቸው ብቻ ነው የሚሹት!

ግሎባል ፈንድ ለኢትዮጵያ፡ ለሣንባ ነቀርሣ ሕክምናና መከለከያለኤድስ ሕክምናና ለወባ መከላከያ ብዙ ዕርድታ አበርክቷል፣ ምንም እንኳ የትናንሽና ታላላቆቹ ባለሥልጣኖቹ ሆድ ወዳድነት ለሕዝቡ ከመጣው ዕርዳታ ብዙ እንደቦጨቁ በባዕዳን የተዘገቡ አንዳንድ ማስረጃዎች አሉ።

ለማንኛውም ፈንዱ በየደረጃው ለኢትዮጵያ ያበረከተው የገንዝብ መዋጮ በድምሩ $2,105,322,897 ሲሆን፣ በሕወሃት አስተዳደር እጅ የገባው $1,937,103,678 ነው። ምን ያህሉ ሥራ ላይ ዋለ የሚለው ብዙ አነጋጋሪ ከመሆኑም ባሻገር ቴድሮስ አድሃኖም የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በነበሩበት ሰባት ዓመታት – ሌላው ቢቀር – የሕወሃትን የፕሮፓጋንዳ መሣሪያዎች ፋናና ዋልታ ለማጠናከር የባከነውና የተዘረፈው ገንዘብ ከፍተኛ ነው።

የዚህ ዐይነቱን መሰል ወጭዎች በተለይ የተቦጨቁት ከኤድስና ከጤና ጣቢያ ግንባታ በጀቶች መሆኑ ተደርሶበታል። ብዙ ከተቦጦቦጠው ባሻገር፣ የጤና ጣብያ ምድብ ገንዘብ ብቻ ዛሬ ሕውሃት በግሎባል ፈንድ ኦዲተሮች እንዲመልስ የተጠየቀው ከሰባት ሚልዮን ዶላር በላይ ነው ከሥር የሠፈረው ሠሌዳ እንደሚያመለክተው፦

From Audit Reports and Diagnostic Review issued by the Global Fund’s Office of the Inspector General on 20 April 2012 (Credit: GF)

From Audit Reports and Diagnostic Review issued by the Global Fund’s Office of the Inspector General on 20 April 2012 (Credit: GF)


 

II. ፋና ወጊ በሆነ መንገድ (precedent setting) ለግሎባል ፈንድ ‘የዲፕሎማቲክ ከለላ ደረጃ’መሥጠት ለምን አስፈለገ?

አያሌ መንግሥታዊ የሆኑ፡ ያልሆኑና የግል ድርጅቶች ግብረ ሠናያዊ ዕርዳታ ለማቅረብ በታዳጊ ሃገሮች ውስጥ ይንቀስቀሳሉ። መንግሥታዊ የሆኑ ድርጅቶች በሁለትዮሽ ስምምነት የሚንቀሳቀሱበት ሁኔት በተቀባዩ ሃገር ሕግ መሠረት እንቅስቃሴ ያደርጋሉ። ትላልቆቹ በመንግሥታት በዓለም አቀፍ ደረጃ በቻርተር የተቋቋሙት ደግሞ ዲፕሎማቲክ መብቶች ተሠጥቷቸው (በTreaty) በሃገሮች ውስጥ የቻርተሩን ዓላማ በሚያነጽባርቅ መልኩ ይንቀሳቀሳሉ – ለምሣሌም ያህል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ኤጀንሲዎቹ።

መንግሥታዊ ያልሆኑትም የዚህ ዐይነት ደረጃ ያላቸው እንደ ዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (International Committee of Red Cross _ ICRC) ዐይነቶቹም እዚህ ውስጥ ይካተታሉ።

ከዚህ ባሻገር በውል መንግሥታዊ ላልሆነ ቢቀየጥም ደግሞ አስተዳደሩ የሃብታሞቹን ሃገሮች/ግለሰቦች ጥቅምና ፍልላጎት እንዲያራምድ በሰብዓዊነት የተቋቋመው ግሎባል ፈንድ በዓለም አቀፍ ትብብር ውስጥ ዋነኛ ሚና ተጫዋች መሆኑ፡ ለዘለቄታው የታዳጊ ሃገሮች ላይ ተጽዕኖ አሳዳሪ ያደርገዋል።

ይህም ማለት፡ የቴክኒክ ተራድኦ በቀላሉ የሚያገኙባቸው እንደ ዓለም አቀፍ ጤና ጥበቃ (WHO) ዐይነት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅቶች እንዲዳከሙና የሃገሮቻችን ዐይን ወደ እነርሱ እንዲዞር ያስገድዳል። ዞሮ ዞሮ የግሎባል ፈንድ ዐይነት ድርጅት መጠናከር፣ በኩልነትና በዓለም አቀፍ ትብብር (INTERNATIONAL COOPERATION AND SOLIDARITY) በሃብታም ግለሰቦች›፡ ድርጅቶችና ተባብሪ ሃገሮች መተዳደርን ሊያስከትል ይችላል። ይህንኑ አስመልክቶ The Washington Post (May 12, 2016) በሠነዘረው አስተያየት፣ ትኩረቱን የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት መዳከም ላይ ቢያሳርፍም፡ የችግሩን ምንጭ በደንብ እንደሚከለው ለይቶታል፦

“The WHO’s influence has been declining for some time. New actors and sources of finance such as the Gates Foundation have created a more diffuse global health landscape. Spending on global health increased dramatically since 2000, but much of the funds were channeled through new entities such as the Global Fund to Fight AIDS, Tuberculosis and Malaria — not the WHO.”

የዲፕሎማቲክ መብቶች ዕውቅና ለግሎባል ፈንድ የሠጠችው ሃገር ስዊትዘርላንድ ናት። ይህም የሆነበት ፈንዱ እከተመበት ጂኒቫ ውስጥ እንደሌሎቹ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ለመሠልፍ እንዲችል ለማድረግ ነው ቢባል እንኳ፣ ስዊትዘርላንድ ከ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ ታላቅ ሃገር መሆኗን ለማሳየት የሞክርችበት አንዱ መሣሪያዋ አያሌ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን በጂኒቫ በማሰባሰብ ነበር፤ አሁንም መሆኑን ይኸው ያሳያል።

የኢትዮጵያና የስዊዘርላንድ ልይነት ግን ገሃድ ነው። በዕድገት ደረጃ ብቻ ሳይሆን፣ ስዊትዘርላንድ ዲሞክራሲያዊ ሃገር በመሆኗ፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ጭምር በከተማዋ ቢሮአቸውን ይመሥርታሉ። ኢትዮጵያ ግን በርሕወሃት ምክንያት ፀረ-ዲሞክራሲና ፀረ-ሕዝብ በመሆኗ፡ ድርጅቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ከመክተም ይልቅ ከሩቅ ተመላልሰው በርሃብ በየውቅቱ የሚጎዳውን ሕዝባችንን ለመርዳት እህል፡ መድኃኒቶችና ልብሶችን በመጫን ሲመላለሱ የሚደርስባቸውን ክትትልና ወከባ እናውቀዋለን። የራሱ ጥላ የሚያስደነግጠው ሕወሃት ግን ኢትዮጵያውያንን እንደ ተራ ዜጎችም ሆነ፡ ሕገ መንግሥቱ የሚሠጣችውን መብት ተጠቅመው በሲቪል ማኅበራት ቢደርጁ እንኳ፡ ከመታሠር፡ ከሥራ ከመባረርና ከመገደልም ማምለጥ አልቻሉም!

ታዲያ እንዲህ ፀረ-ሕዝብ የሆነው ሕወሃት የብር ከረጢት ስላየ ብቻ ነው – ለፈንዱ መናኸሪያ እንኳ ሳይሆን፣ ከስዊትዘርላንድ ጋር ተመሣሣይ (ቅጂ) የሆነውን የዲፕሎማቲክ ከለላ ለግሎባል ፈንድ የሚሠጠው? አንድ መንግሥት የዚህ ዐይነት ችሮታ ለሚወደው/ለሚፈቅደው መስጠቱ መብቱ ቢሆንም፣ ሕወሃት ኢትዮጵያውያንና ድርጅቶቻቸው ላይ ከፈጸማቸው ወንጀሎች አንጻር ሲታይ፣ ይህን አበክረው ሊቃወሙት የሚገባ ድርጅት ነው ብዪ አምናለሁ። ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ራሳቸውን ለገንዘብ የሚሸጡ ቢሆኑ ኖሮ፣ ለጭቁን ጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ችቦ የሆነው የአድዋ ድል ታሪካ ሳይሠራ በቀረ ነበር!

በተለይም ለዚህ ዐይነት ዜጎች አሰተሳሰባቸውንና አመለካከቶቻቸውን ሊያሰሙ ባልቻሉበት ሁኔታ፣ ሕወሃት ለግሎባል ፈንድ ዲፕሎማቲክ ደረጃ (DIPLOMATIC IMMUNITY) ለመሰጠት መወሰኑ፣ የራሱን ግለሰባዊ ጥቅሞች በማየት ከመሆኑም በላይ፡ የነገውን ሁነታ ምልክት የሜፈነጥቀውን ግሎባል ፈንድ በዚህ መልክ ማቀፉ አሳዛኝና አሳፋሪ ድርጊት ነው።

የዚህንም ዜና ጥር 14 ቀን 2017 ግሎባል ፈንድ በኢትዮጵያ በነፃነት እንዲንቀሳቀስ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ቀረበ በማለት በተወሰነ ጥልቀት አካሄዱና አቃጥጫውን ሳይመረምር ሪፖርተር ዘግቦታል።

ሪፖርተር ባቀረበው ዜና መሠረት፣ አፋኙና ስለሃገር ሉዓላዊነት ደንታ የሌለው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ኤድስን፣ ሳንባ ነቀርሳንና ወባን ለመዋጋት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው ድርጅት ሀብትን በሚገባ ለመጠቀም፣ ግሎባል ፈንድና እሱ የሚወክላቸው የሥራ ኃላፊው በነፃነት በኢትዮጵያ እንዲንቀሳቀሱ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማው አቅርቧል።

የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ኢትዮጵያ ያደረገችውን ስምምነት ለማፅደቅ ሲሆን፣ ስምምነቱ በኢትዮጵያ ላይ ከሚጥላቸው ግዴታዎች መካከል ግሎባል ፈንድ የሚሰጣቸው አገልግሎቶችና ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ማናቸውም ዕቃዎችን፣ መንግሥት ከማንኛውም ዓይነት ግብር ክፍያ ነፃ ማድረግ ይጠበቅበታል – ሪፖርተር እንደዘገበው።

በሌላ በኩል የግሎባል ፈንድ ሀብትና ንብረት የሆኑ ቁሳቁሶች በየትኛውም ቦታ በማንም ቢያዙ – ሪፖርተር እንደተመለከተው – ድርጅቱ ያለውን በሕግ የመጠየቅ ከለላ ካላነሳ በስተቀር በሕግ ሒደት ከመያዝ ነፃ እንደሚሆኑ፣ እንዲሁም በየትኛውም ሥፍራ የሚገኙ የተቋሙ ንብረቶች ከመፈተሽና ከመወረስ ከለላ ይኖራቸዋል ሪፖርተር በዜና መልክ እንዳቀረበው።

በሌላ በኩል በግሎባል ፈንድ ውስጥ የሚሠሩ የአባል አገሮች ተወካዮች በሥራ ወቅትና በጉዞ፣ እንዲሁም ጉባዔ በሚደረግበት ጊዜ ለስብሰባ ሲንቀሳቀሱ በፖሊስ ከመያዝና ከመታሰር የመጠበቅ መብት ይሰጣል፡፡ በተጨማሪም በሥራ ምክንያት የሚጠቀሙባቸው ንብረቶች እንዳይያዙና እንዳይበረበሩ፣ ሰነዶችና ደብዳቤዎችን በታሸገ ቦርሳ መቀበል እንዲችሉ፣ ሥራቸው ካበቃም በኋላ ቢሆን በሥራ ላይ እያሉ ከሥራቸው ጋር በተገናኘ ላደረጓቸው ንግግሮችና ለጻፏቸው ጽሑፎች ከሕግ ተጠያቂነት ነፃ እንደሚሆኑ ይገልጻል፡፡ እንዲሁም በዚህ ምክንያት ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ በኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤት ሊከለከሉ እንደማይችል ይገልጻል።

የስምምነቱ መፅደቅ ድርጅቱ ለኢትዮጵያ እያበረከተ ከሚገኘው አስተዋጽኦ አንፃር ከድርጅቱ ጋር ይበልጥ ተቀራርቦ ለመሥራትና መልካም ግንኙነት ለመፍጠር አመቺ ሁኔታን እንደሚፈጥር፣ ከረቂቅ አዋጁ ጋር የተያያዘው ሰነድ ይገልጻል።

የረቂቁ የእንግሊዝኛ ቅጂ እንደሚገልጸው ደግሞ ግሎባል ፈንድ በኢትዮጵያ ባንኮች ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የውጭ ምንዛሪ፣ ወርቅና ፈንዶችን መያዝ ይችላል፡፡ በተጨማሪም በየትኛውም አገር ውስጥ ያለውን የውጭ ገንዘብ ወደ ኢትዮጵያ መላክ፣ ወይም በኢትዮጵያ ገንዘብ የመቀየር መብት እንደሚኖረው ያስረዳል – ሪፖርተር እንደዘገበው።

ለሕዝብ መደለያ እንዲሆንም፣ ኢትዮጵያ (ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ይህንን ሙሉ በሙሉ የተቀበለች ቢሆንም አፈጻጸሙ ግን በኢትዮጵያ የፋይናንስ ሕጎች መሠረት እንደሚሆን በመግለጽ ተአቅቦ አድርጋለች።
 

III. ለምን ይህ ሁሉ የሕወሃት ቲአትር?

ምክንያቱ ምን ይሆን ለሚለው፣ ከቢል ጌትስና ከሌሎች አሜሪካዊ ሃብታሞች ጋር ለሚፈጠረው መቀራረብ አስፈላጊ ተብሎ የተዘጋጀ መንገድ ከመሆኑ ባሻገር፣ ተድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅት ድሬክተር ጂኔራል ሆነው እንዲመረጡ ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)የተለመው የኢትዮጵያን ሕዝብ ስሜትና ፍላጎት በንቀት የረገጠ እርምጃ ነው!

መስፍን ፈይሳ (Esat)

መስፍን ፈይሳ (Esat)

ትንሽ የሚያስገርመው ግን አሜሪካም ሆነች ቢል ጌትስ ኤድስን ለማጥፋት ዘመቻ ላይ ነኝ የሚሉ ከሆነ፣ በደሙ ቫየረሱን ተሸክሞ ሌሎች እንዳይለከፉ ለማዳን ሲፍጨረጨር የነበረውን መስፍን ፈይሳን ዶ/ር ቴድሮስ እንደጠላት እንዲባረርና ከሃገር እንዲሸሽ አስደርገው አሜሪካ ውስጥ በስደት እንዲኖር መገደዱ ለምን አልተሰማችውም? የአቶ መስፍን ፈይሳን ኢንተርቬው ለማዳመጥ እዚህ ይጫኑ

ለምንስ ስለዚህ ጥያቄ አልተነሳም? የሕወሃቱ ባለሥልጣን ዲሬክተር ጂነራል ሆነው እንዲቀርቡና ድጋፋቸውን ማግኘታቸው ከላቀ የባዕዳን ቅም ጋር የተያያዘ መሆኑ ምንም አያጠራጥርም!

የሚያስፈራው ግን፣ የእነዚህ የውጭ ባለሃብቶች በአንድ ጊዜ የዓለም ጤና ድርጅትንና ኢትዮጵያን አንድነት ለመውረስ መሻታቸው ይመስለኛል!
 

%d bloggers like this: