Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
ኅዳር 8/2016 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በወጣ በወሩ የታሠረችበት ምክንያት፣ ናሆም ግርማ እንደዘገበው፣ ”ኢትዮጵያ ትቅደም አቆርቋዧ ይውደም !!! የሚል ፅሁፍ ፌስቡኳ ላይ በመለጠፍና ሰማያዊ ፓርቲ ከፈረሰ በዃላ መንግሥትን በግልሽ ለመጣል አስበሻል” የሚል እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወረራ ወቅት ፓሪስ ለጀርመኖች ከወደቀ በኋላ ናዚዎቹ ፈረንሣይ ጠላት የሆናቸውን አስተዳደር ከፈረንሣይ ወደ ሞሮኮ ካዛብላንካ አዛውራለች በሚል ሂሣብ እዚያም ማሳደድ ሲጀምሩ፣ የፈረንሣዩ ፖሊስ አዛዥ የአካባቢው ገዥ እንደመሆኑ፡ ጀርመኖች ላይ ጣቃት ሲደርስና እነእገሌን እሠር ሲሉት፡ ለኔ ተውት ይልና ለምክትሎቹ – ማሾፉ መሆኑን በመግባባት – “Round up the usual suspect!” የሚለው ትዝ ይለኛል።
የወይንሸት የአሁኑ አስተሳሰሯ ምክንያት ያንን ቢመስልም፡ ወያኔ ተራ ቂመኛ በመሆኑ፡ እንደ ፈሪ አህያ አንዴ የነከሰውን ‘ጅብ’ – ጥፋት ኖረ አልኖረ – ምን ጊዜም እንደማይለቅ ከማሳየት ባሻገር የዚያ ዐይነት sophistication የለውም! አንድ ሴት ብቻዋን የምታርበደብደው የሕወሃት ወንበዴዎች አስተዳደር ገበናው ምን እንደሚመስል አሳይታናለች!
ሕወሃት የፈለገውን ዐይነት ምክንያትና ክስ ሊደረድር ይችላል – ከክሱ አንጻር ሲታይ ግን ወንጀለኛነቱ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። በመሆኑም ይህም የወንጀሉን ጥልቀትና የውድቀቱን መቃረብ ምልክት አድርጌ ነው የምወስደው!
ወይንሸት፣ ምን አለኝ ላንቺ የሚሆን፣ የኛ አኩሪና አብሪ ኮከብ?
ባይሆን እንኳ ከጥላሁን ገሠሠ “የጠላሽ ይጠላ” “የጎዳሽ ይጎዳ! ይጎዳ! ተፈጥሮ ትውቀሰው…” ላንቺ መሥዋዕትነት ከፍተኛ አክብሮቴን ለመግለጽ አበረክትልሻለሁ!
አረመኔው ሕወሃት እሥር ቤትን የዚህች ወጣት መኖሪያዋ ሊያደርገው ምንም ያልቀረው ስለሆነ፡ ስለወይንሸት ሞላ የሚከተለውን የዘገብኩት ኅዳር 2፣ 2014 ዓ.ም. ነበር፡-
ታዲያ የተባለው የኃይለማርያም ማስፈራሪያ ተግባራዊ ለመሆን ብዙም አልፈጀበትም። አንዋር መስጊድ ውስጥ በተደጋጋሚ የሕወሃት የጸጥታ ስዎች በመግባት፡ ወንዶችንም ሆነ ሴቶች አማንያንን በመተናኮል በፈጠሩት ግብግብ፡ ብዙዎች ተደብሴበዋል። በየወቅቱ የታሠሩትም እስካሁን እንደሚንገላቱና በስበብ አስባቡ እየተውነጀሉ መሆናቸው ይታወቃል።
![ወይንሸት ሞላ [Credit: via Helen Wame]](https://i1.wp.com/ethioforum.org/amharic/wp-content/uploads/2014/07/%E1%8B%88%E1%8B%AD%E1%8A%95%E1%88%B8%E1%89%B5-%E1%88%9E%E1%88%8B1-202x300.jpg?zoom=2)
ወይንሸት ሞላ [Credit: via Helen Wame]
በፖለቲካ ስሜቷ ግን የእስላሞች ትግል ኢትዮጵያውያን ለዴሞክራሲና ለሃይማኖት ነጻነት የሚያደርጉት ትግል አካል ነው ብላ በማመኗ በዕለተ አርብ መስጊድ አካባቢ ቆማ ሁኔታውን መከታተል ትጀምራለች። በሰማያዊ ፓርቲ አባልነቷ ለሚያውቃት የሕወሃት የስለላ ባልደረባ ፖሊሶችን በማስተበበር እንደ እባብ ወጣቷን የፖለቲካ ሰው ቀጠቀጧት። ለተወሰኑ ጊዚያትም እሥር ላይ ከርማለች። በሽብር ፈጠራ ስም የተመሰረተባት ክስ ባለመሠረዙ አሁንም ፍርድ ቤት በመመላለስ ላይ ትገኛለች!

ምነው የዓላሙዲ ተቀጣሪ መስሉ? (Capital Ethiopia)
የኃይለማርያም ነገር አይታወቅም እንጂ፣ ነገር ግን ልበ ድፍንነት ራስ ወዳድነትንና ብሎም ማን አለብኝነት አመላካች ሲሆን፡ እርሳቸው ሃይማኖት የላቸውም እንጂ የሲዖል መንገደኛ ምንዳ መሆኑን ሊገነዘቡት ይገባል!ስለአለቆቻቸው ሰለተዘጋጀው ክፍያ አሁን ብዙም መናገር አያሻኝም።
በቅጥረኝነታቸው የኢትዮጵያን አንጀት አድብነው ለርሳቸውም የሚከፈላቸው ከዚያው ያለነሰ እንደሚሆን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል!