በዱባይ Burj Al Arab Jumeirah ሆቴል ሕወሃት የምስረታ በዓሉን ያከብራል! በጥልቅ መታደስ ይሉሻል ይህ ነው!

23 Feb
    አዘጋጁ፡

    በዓለም ውስጥ 15ቱ ውድ ሆቴሎች አንዱ ተብሎ ተዘግቧል!
     

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የካቲት ፲፭ ቀን ፳፻፱ ዓ/ም (ኢሳት ዜና):- በሕወሃት ኩባንያ ሙሉ ድጋፍ እና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ትብብር ሕወሃት የተመሰረተበትን 42ኛ አመት የልደት በዓል በአለማችን እጅግ ዘመናዊና ውድ በሚባለው ቡርጂ አል አራብ ጁሚራህ ሆቴል ውስጥ ከአርብ እስከ እሁድ እንደሚያከብር የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።

በልዩ ትእዛዝ በተዘጋጁ አምስት አውሮፕላኖች የሕወሃት መስራች አባላትና ባለስልጣኖች እንዲሁም ወጣት የሕወሃት ደህንነቶች፣ ባለሃብቶችና ጠንካራ አባላት ከዛሬ ረቡዕ ጀምሮ ወደ ዱባይ በረራ ያደርጋሉ።

እንግዶቹ ዘመናዊ በሚባሉት Abidos Hotel፣ Apartment Dubailand፣ Saffron Boutique Hotel እና Fortune Karama Hotel መኝታ የተያዘላቸው ሲሆን፣ በቆይታቸው ሙሉ ወጪያቸው በድርጅታቸው ኩባንያ ይሸፈንላቸዋል።

ሕወሃት ሕዝብ በተራበበትና ከፍተኛ ችግር ላይ በወደቀበት በዚህ ወቅት በአሉን በውጭ አገር ለማክበር የመረጠው፣ ከሕዝብ አይን ለመሸሽና ከትችት ለመዳን ሲባል መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።

በርካታ የህወሃት ባለስልጣናት ድርጅታቸው በዓሉን በውጭ ለማክበር ማሰቡን በአድናቆት ተመልክተውታል። “በያመቱ በአገር ውስጥ ከሚደረገው አሰልቺ በአል የተለየ ዝግጅት ማዘጋጀቱ፣ ለነጻነቱም ለምቾቱም ጥሩ ነው” ሲል አንድ ተጋባዥ እንግዳ አድናቆቱን ለኢሳት ዘጋቢ ገልጿል።

በዓለማችን የናጠጡ ሃብታሞችና ታዋቂ ሰዎች በሚስተናገዱበት ሆቴል ሕወሃት ለሙዚቃ ዝግጅቱ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ያወጣል።

በሌላ በኩል በደቡብ፣ ኦሮምያና ሶማሊያ ክልሎች የረሃቡ ሁኔታ እጅግ አስከፊ ሆኖ መቀጠሉን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
 

Related:

The Middle East’s most opulent hotel rooms

(CNN)Want to drop 80% of the average U.S. annual income in one night?

Or maybe get some shuteye where Bill Clinton and Pavarotti have previously laid their heads (on separate occasions)?

The Middle East’s most opulent hotel suites can deliver.

With acres of gold leaf and chandeliers at every turn, there’s opulence and decor to make Liberace blush.

Throw in Jacuzzis, cinemas, butlers and fine dining, and those cavernous 12,000-square-foot chambers can soon fill up.

Sure the prices are high, but the money buys jaw-dropping views over sights including the Bosphorus, the Gulf of Oman and the world’s tallest building.

And who knows, the hotels might even throw in a toothbrush for guests who forget theirs.

Read the rest from CNN.
 

%d bloggers like this: