በኦፌኮ ሊቀመንበር ዶክተር መረራ ጉዲና ላይ ሕወሃት በሕገ ቢስ የቀልድ ፍርድ ቤቱ ሁለት ክሶች መሠረተባቸው

3 Mar

በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)
 

በሕውሃት የዜና ማሠራጫ ፋና ዛሬ ከቀትር በኋካ እንደተዘገበው፣ ክሱ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ነው የቀረበባቸው። የክሱም ይዘቶች የሚከተሉት ሁለቱ ናቸው፦

    (ሀ) “የኦፌኮ አመራርነታቸውን እና የፖለቲካ ድርጅቱን እንደ ሽፋን ተጠቅመው የፖለቲካዊ፣ የሃይማኖታዊ ወይም የአይዶሎጂ አላማን ለማራመድ በማሰብ በመንግስት ላይ ተፅዕኖን በማሳደር የሃገሪቱን ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማናጋትና ለማፈራረስ በማቀድ ተቀሳቅሰዋል”

    (ለ) “በ2008 ዓ.ም በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ አካባቢ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን የአምቦ ካራ የመንገድ ግንባታ በመቆራረጥ፣ ካምፕ በማቃጠል፣ በተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች ላይ ከ2,957,000 ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት እንዲወድም አስደርገዋል”


በመሆኑም ለአያሌ ወራት የኢትዮጵያውያንን ሕይወት እንደቅጠል ሲያረግፍ የከረመውና በፊሪ ዱላ በሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋች ሽፋን የሃገርና የሕዝብ አፈናውን ቀጥሎ እያለ፡ ሕወሃት ክተር መረራ ጉዲናን
“በኦሮሚያ ክልል በቡራዩ ከተማ ከ42 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ ንብረቶች ላይ ጉዳት እና ውድመው እንዲደርስ በማስደረግ፤ በደቡብ ምዕራብ ሽዋ ዞን ወሊሶ፣ አመያ፣ ጎሮ፣ ቶሌ፣ ኢሉ፣ ቀርሳ፣ ወንጪ ወረዳዎች ግምታቸው 17 ሚሊየን 352 ሺህ 482 ብር የሚሆኑ በቀበሌ መስተዳደር፣ የግለሰብ መኖሪያ ቤቶች፣ በኢንቨስትመንት ስራ የተሰማሩ የአበባ ድርጆቶች፣ የአትክልት ማምረቻ እና የተለያዩ ንብረቶች እንዲወድሙ እና ጉዳት እንዲደርስ አስደርገዋል” በሚል ክስ አቃቤ ህሕግ ወንጅሏቸዋል።

Dr. Merera Gudina

Dr. Merera Gudina

ተከሳሹ ዶክተር መረራ ጉዲና በመስከረም 24 ቀን 2009 ዓ.ም በኢሬቻ አከባበር ስነ ስርአት ላይ የመንግስት ታጣቂዎች በኦሮሞ ህዝብ ላይ በወሰዱት ግድያ 678 ሰዎች ተገድለዋል በማለት የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦ ኤም ኤን) ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ የሁከት ጥሪ ማስተላለፋቸውንም ክሱ ያስረዳል።

በተጨማሪም፡ ተከሳሹ በመስከረም 24 ቀን 2009 ዓ.ም በኢሬቻ አከባበር ስነ ሥራዓት ላይ የመንግሥት ታጣቂዎች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ በወሰዱት እርምጃ 678 ሰዎች ተገድለዋል በማለት የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦ ኤም ኤን) ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ የሁከት ጥሪ አስተላልፈዋል የሚል ክስም ታክሎበታል።

የሚያስገርመው ነገር፡ ዶክተር መረራ ጉዲና ሰው ከመሆን ይልቅ ወደ መተረየስነታ ጥይትነት ተለወጥው፣ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ሁከት እና ብጥብጥ እንዲነሳ ትግሉን እናስቀጥላለን በማለት ባደረጉት የሁከት ጥሪ ከመስከረም 2009 ዓ.ም በኋላ የሰላማዊ ሰዎች ሕይወት መጥፋት እና ከባድ የአካል ጉዳት መድረስ እንዲሁም በመንግስት ተቋማት ከ215,468,000 ሺህ ብር በላይ ንብረት ውድመትና መንግሥታዊ ባልሆኑ ተቋማት ከ1.168 ቢሊየን ሚሊየን ብር በላይ የንብረት ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውም ክሱ ይጠቅሳል።

ከዚህ በተጨማሪ፡ በተባበሩት አረብ ኢሜሬትስ ከሚገኙ ከአንዳንድ የኦነግ ደጋፊዎች ለብጥብጥ ማከናወኛ የተሰበሰበ ገንዘብ በኦፌኮ ፓርቲ የፋይናንስ ኃላፊ በኩል እንዲላክ ፍቃደኝነታቸውን ገልጸዋል የሚለውም በአቃቤ ሕግ ክስ ተጠቅሷል።

ዶክተር መረራ የተወነጀሉትና ክሱ የተመሠረተባቸው ቀድም ብሎ በሕወት ተቀነባብሮና ተዘጋጅቶ ነው። ይህም ገሃድ የሆነው ፋና ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ተከሳሹ ከአሜሪካ ጉብኝታችው መልስ በተሳተፉበት ወቅት በፓርላማ የሚገኘው የሕወሃት ተወካይ አስመላሽ ወልደ ሥላሴ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመጣሳቸው እሥር ቤት መውረድ የገባቸዋል ማለቱ ይታወሳል!

ዋናው ማስረጃው ኅዳር 2/2009 ዓ.ም በብራሰልስ በአሸባሪነት ከተፈረጀው ግንቦት ሰባት ቡድን መሪና ከሁለተኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ነጋ ጋር ተገናኝተው በመወያየታቸው ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር የተያያዙ ግዴታዎችን በመተላለፍ እና የሽብር ተልዕኮ መስጠትና መደገፍ ወንጀል ሆኖ መቅረቡን የአቃቤ ሕጉ ክስ ያሳያል።

የሽብርተኛ ቡድን በመደገፍና በማነሳሳት በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን የሽብር ወንጀልም ክስ ቀርቦባቸዋል።

ዶክተር መረራ ጉዲና ዛሬ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን፥ በጠበቃቸው አማካኝነት ክሱ ላይ መቃወሚያ እንዳላቸው ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱም በመቃወሚያው ላይ የአቃቤ ህግ ምላሽን ለመስማት ለየካቲት 30 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

እኔን ሁልጊዜ የሚገርመኝ፡ በሕወሃት አስተዳደር ላይ ከፍተአኝ የወንጀለኝነት ችካል የመታብት አትሌት ፈይሣ ሌሊሳ ሲሆን፡ ግንባሩ ሰሚ እንደማያገኝም ስለክሚያውቅ፡ ከእነዚህ ግለሰቦች ጋር አብሮ መኖሩ ቢታወቅም – መንግሥት ሳይሆን አውቆ አበድነቱን በሚያሳይ መንገድ – ሕወሃት የአትሌቱን ስም በፍጹም አያነሣም። ከሣምንታት በፊት ባለቤቱንና ልጆቹን ወደአሪዞና እንደላከለት ይታወሳል!

እንደድሪቶ ተደራራቢ በሚመስል መልኩ በተጻፈው የፋና ዜና፡ የዶክተር መረራ ክስ የሽብርተኛ ቡድን መደገፍና ማነሳሳት ዋናው ወንጀላቸውና በወንጀል ተሳታፌነት ተደርጎ ቀርቧል።

ተከሳሹ ዶክተር መረራ ጉዲና በዛሬው ዕለት ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት በጠበቃቸው አማካኝነት ክሱ ላይ መቃወሚያ እንዳላቸው አሰምተዋል።

ፍርድ ቤቱም በመቃወሚያው ላይ የአቃቤ ሕግ ምላሽን ለመስማት ለየካቲት 30 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሠጥቷል።
 

%d bloggers like this: