አዲሱን ትውልድ በታሪኩ ስለማነጽ ከተወዳጁ አርቲስት ሚካኤል ሚሊዮን ጋር የተደረገ አስደሳች ቃለ መጠይቅ

6 Mar

በክፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)

በአፍራሽና ሆዳም ኃይሎች ድንቁርና ኢትዮጵያ በዘር በመከፋፈልና በተለያዩ ችግሮች ልትቆስል፡ ልትጎሳቆል ትችላለች፤ ነገር ግን በሕዝቧ መተሳሰር ምክንያት ለእኩል ያገባኛል ባይነት ተጠቃሚነት የዴሞክራዊና የነጻነት ትግሏን አንድ እንደሆነች ትቀጥላለች!

 
ሚካኤል መኮንንን የተዋወቅሁት በቅርቡ የኢትዮጵያን ፊልሞች መመልከት ከጀመርኩ ወዲህ ነው! እርሱንና አዚዛ መሃመድን ያገኘኋዋቸው “መስሁት” በተሰኘው ግሩም ኢትዮጵያዊ የፊልም ሥራቸው ነው። ከዚያ ፊልም ወዲህ በየቀኑ ቢያንስ አንድ የኢትዮጵያ ፊልም ሳላይ እንዳልተኛና ጓደኞቼም እንዲያዩ እያበረታታሁ ነኝ!

በተለይም የመስሁት የመጨረሻው ክፍል ባህልን አክብሮ፣ በአባትየው ቤት የነበረው ውይይትና የሠርጉ ክንውን፣ ቤቲ ከቤተሰቧ በቀጥታ ወደሚካኤል ሚስትነና እንዲሁም የብሩክ እናት ልጅነት የምታደርገው ሽግግር እጅግ ኢትዮጵያዊነትን የተላበሰ በመሆኑ እጅግ አኩርቶኛል!

በጎን ሳሮንም ከዋስዬ ጋር የነበራት ጭውውት፣ ሙክክ ያለው የልባቸው ስሜትና ውጤቱ እንዲሁም በሁለቱ ሚስቶች በኩል የነበረው ወዳጅነት የቤተሰብ ምሰሶ ወደ መሆን ስላሸጋገራት በጣም አስደስቶኛል!በወቅቱ መስሁት ምን እንደሆነ ትርጉሙን ባልገነዘበውም፡ ፊልሙን እንዲያይ ሳበረታታው የነበረ ግለሰብ ነው በድንገት በግዕዝ “መከራ” (የቤቲ) መሆኑን ያስጨበጠኝ!

ሚካኤል! እግዚአብሔር ይባርክህ ወጣቱን ከታሪክና የስብዕና ድህነት ‘ማዳን’ ላይ በማተኮርህ!
 

%d bloggers like this: