ለባለሃብትና ገዥዎች ምቹዋ ኢትዮጵያ!በአዲስ አበባ የምግብ ዋስትና መርሃ ግብር የምግብ ዕርዳታ ለማግኘት የተመዘገበው ሕዝብ ቁጥር ከ600 ሺ በላይ መሆኑ ተገለጸ!

13 Mar

ከአዘጋጁ፡


    በባለ ሁለት አሃዝ አዳጊዋ ኢትዮጵያ ውስጥ፣ በሕወሃት አማካይነት የጥቂቶች ‘ባለ ምርጥ ዘሮች’ መክበርና የብዙሃኑ መገፋት፡ የቆሼ ዐይነት አደጋዎችን በውጥረት ለተበላሸው ፖለቲካ ተጨማሪ የደህነነትና ለሃገር ሰላም ጠንቅ እንደሚሆን ጥርጥር ሊኖር አይገባም! ለጊዜው ይህንን በውጭ ዕርዳታ (PSNP) ለማስታመም ይቻል ይሆናል፤ የዘለቄታው ጉዳይ ለሕወሃት ካበቃለት ስንበት ብሏል – ግን የደነደነ ልባቸው እንዳያዩት አድርጓቸዋል እንጂ!

=============

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ ዋስትና መርሃ ግብር ተጠቃሚዎች ልየታ እየተጠናቀቀ መሆኑን የከተማማዋ ምግብ ዋስትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ኤጀንሲ አስታወቀ።

ኤጀንሲው እንዳለው፥ በበጀት ዓመቱ በምግብ ዋስትና መርሃ ግብሩ ከ123 ሺህ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቀዶ እስካሁን ቤት ለቤት በተካሄደ ምዝገባ 600 ሺህ ሰዎች ተመዝግበዋል።

በመርሃ ግብሩ ተጠቃሚ የሚሆኑ ሰዎችም በመጪዎቹ 15 ቀናት ይለያሉ ብሏል ኤጀንሲው።

በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 35 ወረዳዎች ተግባራዊ የሚደረገው ይህ መርሃ ግብር፥ ተደራራቢ የአካል ጉዳት ያለባቸውን፣ አቅመ ደካማ አረጋውያን እና በተለያዩ ምክንያቶች የመስራት አቅም የሌላቸውን 23 ሺህ ሰዎችን በቀጥታ ተጠቃሚ ያደርጋል።

የተቀሩት በማህበረሰብ አቀፍ የልማት ስራዎች ይሰማራሉ ተብሏል።
 

ተዛማጅ:

    Koshe landslide in Addis Ababa kills a number of people; the casualty figure likely to rise

    The Bole/Were Genu Massacre: Murderous TPLF regime shoots 8 Ethiopians & wounds 100 others to clear land for foreign investors

    ‘It’s life and death’: how the growth of Addis Ababa has sparked racial tensions

 

%d bloggers like this: